Monday, August 5, 2013

አሰቃቂው ድብደባና የኢቲቪ የግዳጅቀረፃ በሚድሮክ ኮንስትራክሽን ግቢ ውስጥ!

አሰቃቂው ድብደባና የኢቲቪ የግዳጅቀረፃ በሚድሮክ 

ኮንስትራክሽን ግቢ ውስጥ!



እለተ #አርብ #ሐምሌ26 2005 ዓ.ም #በፍልውሀ መስጅድ ሊካሄድ የነበረው 

ተቃውሞ ቢሰረዝም አንዳች ወንጀል ሊፈፅሙ የተዘጋጁት የወያኔ አመራር 

በዋናዋናዎቹ የአዲስ አበባ ቦታዎች ፌደራልፖሊስ በማስፈር ከተማዋን የጦር 

ቀጠና አስመስልዋት ነበር።ፍልውሀ መስጅድ አካባቢ የሰፈሩት ፌደራል ፖሊሶችና 

የወያኔ ደህንነቶች ግን ተቃውሞው ባይኖርም የታዘዙትን ተልእኮ ለመፈፀም 

ችለዋል።ነገሩ እንዲህ ነው የወያኔ ደህንነቶች መስጊድ ውስጥ በመግባት ሆን ብለው

አምባጓሮ አስነሱ ከዛ በተጠንቀቅ ይጠብቁ የነበሩት ፌደራል ፖሊሶች ያገኙትን

 ሰው መደብደብ ተያያዙ ድብደባውን ያካሄዱት በተጠናና በተቀናጀ ሁኔታ ነበር

የተወሰኑት ሲደባደቡ የተወሰኑት ለአሰቡት ግብአት ይሆነናል ብለው ያሰቧቸውን

ወጣቶች በመያዝ ፍልውሀ መስጅድ ፊትለፊት ወደሚገኘው የሚድሮክ ኮንስትራክሽን

ዋና ፅ/ቤት ግቢ ውስጥ በመግባት ማሰር ጀመሩ በግምት ከ150 -200 የሚሆኑ

ወጣት ወንዶቹንና ሴቶችን አስረው ከያዙ በኋላ የሚድሮክ ሰራተኞች ከግቢ

እንዳይወጡ በማዘዝ የወጡትም እንዳይገቡ መመሪያ በማስተላለፍ ሁኔታ በታሳሪዎቹ

 ላይ ድብደባ ይፈፀም ገባ እጅግ በርካታዎቹ 

ደማቸው ፈሰሰ በጣም የተጎዱት በቃሬዛ እየወጡ በአምቡላንስ 

ተወሰዱ።ከጭካኔያዊው ድብደባ በኋላ አስቀድመው በደህንነቶች የተዘጋጁ 

መፈክሮች በግድ እንዲይዙ እየተደረገ የኢቲቪ ካሜራማኖች እንዲቀርፁ ተደረገ 

ከመፈከሮቹ አንዱ የአንድነትፓርቲ መሪ ቃል "የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት" 

የሚለው ይገኝበታል በዱላ ብዛት መፈክር ይዘው የተቀረፁ ቢኖሩም አንቀረፅም 

ያሉም ነበሩ በተለይ አንድ ወጣት እምቢ በማለቱ እጅግ የከፋ ድብደባ 

ደረሰበት።ይህ ፋሽስታዊ አሰቃቂ ድብደባና የኢቲቪ ቀረፃ ከተካሄደ በኋላ 9፡20 

አካባቢ በዱላ የተጎሳቆሉት ወጣቶች በመኪና እየተጫኑ ከግቢው ወጡ።እነርሱ 

ከወጡ በኋላ የፈሰሰው ደማቸው በሚድሮክ ኮንስትራክሽን ዋና ፅ/ቤት ግቢ ውስጥ 

ይታይ ነበር።

No comments:

Post a Comment