ኢቲቪና ሬዲዮ ፋና እየተወዛገቡ ነው (ማንኛቸው ይሆኑ ታማኝ ዋሾዎች )
ቅዳሜ እለት ህወሃት መራሹ የኢሃዴግ መከላከከያ ሰራዊትና ፌዴራል ፖሊሶች በአርሲ ኮፈሌ ንፁሃን ሙስሊሞች ላይ በከፈቱት የእሩምታ ተኩስ ከ11(እስኪረጋገጥ እንጂ ቁጥሩ ከዚህም ይልቃል ) በላይ ንፁሃን ሰዎችን እንደገደሉ ይታወቃል ፡፡ ታዲያ ይህን አረመኒያዊ ጭፍጨፋ ታማኞቹ የህወሃት\ኢሃዴግ ሚዲያዎች የሆኑት ሬዲዮ ፋና እና ኢቲቪ አስገራሚ የዘገቡት ሲሆን ጉዳዩ አንድ ሆኖ ሳለ ሁለቱም ግን አስቂኝ አዘጋገብ ዘግበዋል ፡፡
ኢቲቪ በትላንት ማታ ዘገባው " 3 አሸባሪዎች ሲገደሉ 7 የፀጥታ ሀይሎች ቆስለዋል " ሲለን አብሯቸው ታግሎ የመጣው ሬዲዮ ፋና ደግሞ አንድነት ፓርቲ ትላንት በባህር ዳር ያደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ሲዘግብ እግረ መንገዱን አያይዞ " በምዕራብ አርሲ ዞን ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ፀረ ሰላም ቡድኖች ትናንት በፈጠሩት ሁከትና ብጥብጥ ፥ የ3 የፖሊስ አባላት ህይወት ማለፉና በ11 ንጹሐን ዜጎች ላይጉዳት ደርሷል " ብሎናል ፡፡ ቆይ ቆይ ግን እኛ የትኛውን ውሸት እንመን ? ደግሞ ውሸትም ይታመናል እንዴ ብላችሁ እንዳትሞግቱኝ)
የሆኖ ሆኖ ሁኔታቸውን ስታዘብ እኔ ነኝ ለድርጅቴ ታማኝ ዋሾ አይነት ግብግብ ውስጥ የገቡ ይመስለኛል ፡፡ ግን ግን ማንኛቸው ይሆኑ ታማኝ ዋሾዎች ?

No comments:
Post a Comment