የግፍና የሰቆቃ ወህኒ ቤቶች
በሀገራችን በሚገኙ
እስር ቤቶች ማለትም ድሬደዋ፣
ቃሊቲ፣
ቂሊንጦ፣
ሸዋሮቢት፣
ዝዋይ የፌደራል እስር
ቤቶች ተብለው ሲጠቀሱ ከነዚህ ውጪ የክልል
እስር ቤቶችና በበርካታ የክልል ከተሞች፣ በመሀል
አዲስ አበባ በሚገኙ ቪላዎች፣ በደህንነት ተቋሞችና ወታደራዊ ካምፖች ውስጥ ጭምር
ስውር እስር ቤቶች ተወቋቁመዋል፡፡
በደርግ
ዘመነ መንግስት የተመሰረቱ በርካታ የሸቀጣሸቀጥና የእህል
ማከማቻ
መጋዘኖችን ኢህአዴግ ወደ ስውር እስር
ቤትነት
ቀይሯቸዋል፡፡
የራሱን ችግር
ሳይፈታ
ሰላም አስከባሪ ነኝ፤ የሚለው
ወያኔ/ኢህአዴግ ገበናው ሲፈተሸ ራሱ ፀረ
ሠላም ነው፡፡ ወጣቱን ኃይል ማሰር ተቀዳሚ
የስርዓቱ
አምባገነናዊነት
ማሳያ ቢሆንም ይበልጥ የስርአቱን አስከፊነትና
አደገኝነት
የሚያረጋግጠው አባትና ልጆችን እንዲሁም ወንድማማቾችን፣
ባልና ሚስትን፣
የአንድ
ቤተሰብ
አባላትን
፣ በዘር ምክንያት
አድኖ በጭካኔ የሚያስርና ለዕድሜ ልክ እስር
የሚወረውር
አምባገነን
ስርዓት
ነው፡፡
የሚፈፅማቸውን
ድርጊቶች
ለተመለከተ
ይህ ስርዓት የዘር
ማጥፋት
ድርጊት
እየፈፀመ
መሆኑም ግልጽ ይሆንለታል፡፡ ለዚህ
እኩይ ተግባሩ ቀድሞ
ፈርዶ ለይምሰል
የሚያቀርባቸው
የክስ መዝገቦች የሚዘረዘሩት ክሶች፡ የሀገርን ግዛትና አንድነትን መንካት ሽብርተኛ ኦነግ፣ ግንቦት 7 ምናምን በሚል ነው፡፡
ይህን በአሁኑ
ጊዜ “ሀገራችን ሠላም ነው፤ ዕድገት
እያስመዝገብን
ነው፡፡
ኢህአዴግ
በምስራቅ አፍሪካ ተደማጭ ነው” እያለ ከሚነግረን የተለየነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ 22
ዓመታት ሙሉ ታፍኖ እየተገዛ
ነው፡፡
መብቴን
ሲል ተለጣፊ ስም
እየተሰጠው
ወደ እስር ቤት የሚወረወረው
ወጣት ቁጥሩ እጅግ ብዙ
ነው፡፡
አገር ጥሎ የሚሰደደውም የትየለሌ
ነው፡፡
ዲሞክራሲያችን
ለአፍሪካ
ምሳሌ ሆነ፤ እከሌ የሚባል
ፈረንጅ
ምስክርነቱን
ሰጠ ወዘተ” በማለት የራሱን
ጉድ ደብቆ ባዶ የፕሮፓጋንዳ
ጩህቱን ይጮሀል፡፡ ይህን ባዶ ፕሮፓጋንዳ
ማየት የፈለገ ሌላ ማስረጃ
ሳያስፈልገው
ሀገራችን
ሠላምነች ወይ?
የተረጋጋ
ፖለቲካ
አለ ወይ? ብሎ ቢጠይቅ መልሱ ከኢቴቪ፣ ወይም
ከአቶ በረከት ሳይሆን
የገሀዱ
ሀቅ ሀገሪቷ ወዴት እየሄደች
እንደሆነ
ለማየት
ኢትዮጵያ
ውስጥ ያሉትን እስር
ቤቶችን
መፈተሸ
በቂ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ድብቅ
እስር ቤቶች ከሕዝብ ለምን
ተደበቁ? ምንስ
እየተሠራባቸው
ነው? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ በቅርቡ ለአውሮፓ ህብራት ለማሳየት ፈራ::
የተለየ የፖለቲካ
አመለካከት
ያላቸው
ዜጎች ከመላው ሀገሪቷ
ተለቃቅመው
የሚታጐሩት በነዚሁ ሚስጢራዊ
እስር ቤቶች ውስጥ ነው፡፡ እውነት በነዚህ እስር ቤቶች የሚሰቃዩት
ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ሰዎች ለብሔራቸው
ሥጋት፣
ለአገራቸው ሽብርተኛና ወንጀለኛ ሆነው ነው የታሰሩት?
ወይስ ለብሔራቸው መብትና
ጥቅም ለራሳቸው ነፃነት ሲታገሉ? ሀቁ
ለኢህአዴግ
ዘረኛና
አምባገነናዊ አገዛዝ ሥርዓት ሥጋት ስለሆኑ ብቻ
ነው፡፡
በእኔ እምነት የፖለቲካ
እስረኞች
ናቸው፡፡
ከብዙ በጥቂቱ ህያው ምስክሮች
ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ
ሀገራችን ለዕድገቷም ሆነ ለውድቀቷ እነዚህ
ህዝቦቿ ናቸው፡፡ ስለዚ ለምን ይህ
ሁሉ የፖለቲካ እስረኛ ዜናው ለህዝብ
እንዳይሰማ
ተደረገ?
ይህ ለህዝብ አንዳይሰማ ወያኔ/ኢህአዴግ የህዝብን ስሜት ለማስቀየር ሲምፖዚየም፣
ዐውደ ጥናት፣ የልማት ስብሰባ፣
ወጣት ሊግ፣ ሴት ሊግ
እያለ ህዝብን ያደናግራል፡፡
መሠረታዊ
ፍላጐት
እንኳ ሟሟላት አቅቶታል፡፡
በሰፊው
በገበያ
ላይ ይገኙ የነበሩት
ዘይትና
ስኳር እንኳን ኮንትሮባንድ ሆነው ነጋዴዎችን
በአፈና
እያሳሰሩ
ናቸው፡፡
ኢህአዴግ ብዥታ ለመፍጠር ፕሮፓጋንዳ
ሊነዛ ይችላል፡፡ ግን ሀቁን
እስር ቤቶች አፍ አውጥተው
ይናገራሉ፡፡
የወያኔ
መንግስት
ወንድም
የሆነው
የሊቢያ መሪ ጋዳፊ ከዚህ
የበለጠ
ምን ግፍ ሠራ? ሌሎች አፍሪካ ሀገሮች ከአፍሪካ ቀንድ የተሻለ ዴሞክራሲ ስርዓት ዘርግተው ህዝባቸውን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ አፍሪቃ ቀንድ ግን ሰብአዊና
ዲሞክራሲ
ስርዓት በፍፁም ያልዘረጉ ጨፍጫፊዎች የነገሱባት ናት፡ ፡
ቀጠናው
ለረዥም
ዓመታት
በመንግስትነት የተቀመጡ አምባገነን መሪዎች ያሉበት ነው፡፡ ስለዚህ ከጋዳፊ
ምንም የሚለያቸው ነገር የለም፡፡ ይገላሉ፣
አካለ ጐደሎ ያደርጋሉ፣ ያስራሉ፣
በባዶ ፕሮፓጋንዳ ህዝባቸውን
ይዋሻሉ፡፡ ሌላው ድብቁ የስቃይ
ቦታ ጦር ኃይሎች ጀርባ የደርግ ደህንነት የነበረው ግቢ ነው፡፡ ይህ
ግቢ በከተማችን እንደወጡ
የሚጠፉ
ዜጐች አፋልጉኝ ፎቶ የሚወጣባቸው
ዜጐቻችን
የሚታጐሩበት ዘግናኝ ቦታ ነው :፡ እዚህ ቦታ
ሲገቡ ወደየት ቦታ እንደ
ተወሰዱ
እንዳያውቁ
አይንዎትን እተያዙበት መኪና ውስጥ ይታሰራሉ፡፡
እዛ ግቢ ውስጥ
ለረዥም
ዓመታትም
ሊታሰሩ
ይችላሉ፡፡
የሰው ልጅ ስጋው ተበጣጥሶ
የሚወድቅበት፣ በጋለ ብረት የሚቃጠልበት፣
ወንድ ልጅ እንደ እንስሳ
የሚኮላሽበት፣
ጥፍሩ የሚነቀልበት፣ እንደ እንስሳ
እንዲመገብ
የሚገደድበት፣
የስቃይ ቦታ ነው፡፡ እዚህ
እስር ቤት እስከ ሁለት ዓመት ታስረው
ከቆዩ በኋላ ቅብብሎሹ ይቀጥላል፡፡ ወዴት? ካሉ ወደ
ማዕከላዊ
ይላኩና
እንደ አዲስ ምርመራው
ማዕከላዊ
ይቀጥላል፡፡
በዚህ የማሰቃያ ስፍራ የወንድ ብልት የዘር ፍሬ በስቴፕለር
ይጣበቃል፡፡
ውሃ ኮዳ ይታሰርበታል፡፡
ሌሎች ተዘርዝረው የማያልቁ እጅግ ዘግናኝ
የግፍ ድርጊቶችማ ይፈፀማሉ፡፡
በአጠቃላይ ግን
በፈጠራ ዶክመንተሪ ፊልም ባዶ ፕሮፓጋንዳ
መለፈፍ ከደርግ ውድቀት የአለመማር ውጤት ነው፡፡ “ምንም
የፖለቲካ
እስረኛ
የለንም፡፡
ሀገሪቷ
ሠላም ነች፡፡ የተረጋጋ
ፖለቲካ
አለ” እየተባልን እስከመቼ እንታለላለን? አሁን
ዜጐች በየወህኒ ቤቱ ታጉረው ያሉትን
የክስ መአት እያወቁ ህዝብን
መዋሸት እስከመቼ?
ሰሞኑን ኢህአዴግ በሁሉም የሀገሪቷ እስር ቤቶች አዳዲስ የሙስሊሙን ጋዜጠኞች እና
መሪዎች እስር ቤቶች እያስገባ
ይገኛል፡፡
ይህንን
መካድ አይቻልም፡፡ እስር ቤቶች
አፍ አውጥተዋል፤ ይህን የውሸት ድራማውን በማጋለጥ የሁላችንም ሀላፊነትታችን እንወጣ ፡፡
ከአንድናት ኢትዮጵያ ብሎግ
ኢትዮጵያ
በክብር ለዘላለም ትኑር!

No comments:
Post a Comment