Friday, August 9, 2013

ይሕ ቀን እንግዲህ የደሰታ የጾም መፍቻ ነው እንጂ የተለያዩ መፈክሮችና የተለያዩ ሁከታዋች ሚነሱበት ቀን መሆን አልነበረነትም:: ሰለዚሕ መንግሰት እንድዲሕ ማድረግ ያለበትን ተገዶ እሰካደረገ ድረስ የመንግሰት ሰራው ነውና የፀጥታ ሐይል ሰረውን ነው ያካሄደው ግዜውና ሁኔታን ቦታን ያልተጠበቀ ጥያቄ ያልጠበቀ አካሄድ ሰለተኬደ የተወሰደው እርምጃ እኔ ቤግሌ ትክክል ነው የምለው ::

ይሕ በአሁኑ ሰአት የሚካሄደው ጥያቄ እኔ እርግጠኛ ነኝ የሐይማኖት ጥያቄ አይደለም:: በብዙ መልኩ እንደምናየው የተለያዩ ፓርቲዎች የፕለቲካ ፓርቲዎች ለምንድነው ሕዝበ ሙሰሊሙን መሳሪያ የሚያደርጉት? አንድ ሰው ከጮኸ 100 ወጣቶች ወይም ሺ ወጣቶች አብረውት ይጮሀሉ ምክንያቱን ሳይረዱ ሳይገነዘቡ የዛሬ በአል የኢድ ፈጥር በአል ነው እንጂ በዚሕ አሰታኮ አሳቦና የፓለቲካ ጥያቄ የሚነሳበት ፕለቲከኞችም ሙሰሊሙን ፈረስ አርገው የሚጋልቡብት መሆን የለበትም::

በመጨረሻም እነዚህን ሐይሎች በመከላከል ከሙሰሊሙ ማሕብረተሰብ ከፍተኛ አሰተዋጾ ይጠበቅበታል ለሃገሪቷ ሰላም አደጋ ከሆኑ አከላትም እራሱን ሊጠብቅ ይገባዋል ብለዋል ::

የሚከተለው አሰተያየት ነው :-

የፕለቲካ ትያቄ የተባለውም እንደሆን "ኮሚቴዎቻችን ይፈቱልን እና መንግሰት በሐይማኖታችን ጣልቃ እይግባብን" እንጂ "እሰክንደር ነጋ ይፈታ" የሚል ሰምተንም አናውቅም :: ሌሎች ፕለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትያቄ ነው :: ፕለቲካ የሚባለው ሰውን መብቱን እንዳይጠይቅና አፍ መቆለፊያ ነው:: እኛም ደጋግመን ሰምተነዋል ::

አንድ ሰው ሲጮህ ሺ ይጮሃል ........ጉዳዩ ሳይገባው ማለት ምን ማለት ነው? ይሄ ተቃውሞ ሲጀመር በደምብ እናሰታውሳለን በአንድ ሰው እንዳልተጀመረም እናውቃለን ነገሩ እንኳን እያደገ እንጂ እየቀነሰ አይደለም :: ይህ የሚያሳየው ትግሉ የገባው እየተቀላቀለ መምጣቱን ነው :: ባለማወቅ ለተባለው አመት አልፎት ወደ ሁለተኛ አመቱ እየተቃረበ ነውና እሰካሁን ለምን እንደሚቃወም የማያውቅ ያለ አይመሰለንም ::ኧረ ጎበዝ ትላንት አይደለም የተወለድነው ::

በሰላም ተጠናቀቀ ያተባለው ይሕን ይመሰል ነበር ::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!

No comments:

Post a Comment