Friday, July 12, 2013

በገዛ ሀገራች ኢትዮጵያ ስደት እስክመቼ?

በገዛ ሀገራች ኢትዮጵያ ስደት እስክመቼ?
 ትውልድ በፍርሃት ድብታ ውስጥ ወድቆ፤ ራዕዩንና ህልሙን በማሳካት ፈንታ እንደ እስፖንጅ የመጠጠውን ብቻ እንዲተፋ ሲፈረድበት፤ በ1997 ዓ.ም በገዥው ፓርቲ ድባቅ የተመቱ የነፃው ፕሬስ አባላትና ጋዜጦቻቸው እንደጨው እንዲበተኑ ከተደረገ በኋላ፤ በጠቅላላ ‹‹ብሄራዊ መደንዘዝ›› እና ‹‹ብሄራዊ ዝምታ›› የነፃነት ቁንጮ በሆነችው ኢትዮጵያ ‹‹ለምን?

 
ሃገራችን የነፃነት አውድ በመሆን የምትታወቀውን ያህል በረሃብ ስሟ የጠቆረውን ያህል አሁን ደግሞ በስደት የምትታወቅ ሆናልሃለች፡ ፡ ኢትዮጵያውያን ከሃገራቸው ነቅለው ለመውጣት ልባቸው የቆመ ይመስላል፡፡ በአራቱም አቅጣጫ ከቦሌ በአውሮፕላን ጀምሮ እንደሸቀጥ በኮንቴነር ታሽገው እየተመሙ የሚገኙት የእኔና የአንተ ወንድምና እህቶች ናቸው፡፡
ለመሰደድ ምክንያት እንዳለ አውቃለሁ፡ ፡ ወደውም አይደለም፡፡ ቢያንስ የስደቱን መልክ የፖለቲካ ስደተኛ፣ የኢኮኖሚ ስደተኛ፣ ቅምጥል ኑሮ ፈላጊ ስደተኛ ብዬ በሦስት ልከፍልልህ እቸላለሁ፡ ፡ ገዢህ ፓርቲ ስልጣን ከያዘ በኋላ የስደተኝነት ዘርፉንም አሳድጎልሃል፡፡ የፖለቲካ ስደተኞችን ጋዜጠኞች ተቀላቀሏቸው፡፡ በተለይ ከ1997 ዓ.ም ምርጫ በኋላ አውራ ፓርቲና አውራ አምባገነን የሆነው ገዢ ፓርቲህ የሚቀናቀኑትንና የሚተቹትን ከአጠገቡ በረቀቀ ስልት ያስወግዳል፡ ፡ እንደ ቀድሞው ደርግ ሽጉጡን ከጎኑ መዥረጥ አድርጎ ግንባርህን አይልህም፡፡ ህግ የሚመስል ነገር ይጠቅስና ወደ ጓሮ ይጥልሃል፡፡ ከፈለገም ማንም ሳያይ ይገድልህና ከእናትህ ጋር ሆኖ እንባውን እያዘራ ሬሳህን ይፈልጋል፡፡
ይሄን የኢህአዴግ መስመር የተረዱ ጋዜጠኞችም ‹‹ጃስ!›› ሲባሉ በርግገው ሃገር ለቀው ተሰደዋል፡፡ ከነዚህም መካለከል ሊጠቀሱ ሚችሉት የ‹‹አዲስ ነገር ጋዜጣ›› ጋዜጠኞችና የአውራምባ ታይምስ ባለቤት ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ናቸው፡፡ ሁለቱም ጋዜጠኞች ድንገት ከአደባባይ የጠፉት እንደ ፍትሕ ‹‹በቃችሁ! ውጡ!›› ተብለው አይደለም፡፡ ‹‹ኢህአዴግ እኛን ሊያስር አስቧል›› በማለት ድንገት ሃገር ጥለው ተሰደዋል፡፡ ብዙችም እስርቤት‹‹ከመግባት መውጣት!›› ብሎን ከኢትዮጵያ ብዙ ሺ ማይል እር ተሰደ፡፡ ከመጋፈጥ ይልቅ መሰደድን መምረጣቸውን አከብርላቸዋለሁ፡፡ ኢህአዴግም ከማሰርና ከማሳደድ የማይቦዝን፤ የሃሳብ የበላይነትን የማይቀበል እንደሆነ እረዳለሁ፡፡ ዋናው ጥያቄ ይህን ማስቆም የምንችለው እንዴት ነው? የሚለው ይመስለኛል፡፡ እንቅፋቱን በማስወገድ ወይስ እንቅፋቱን በመሸሽ? በዚህ ጥያቄ መሰረት እንቅፋቱን የሸሹት ለወጣቱ ጥሩ ምሳሌ መሆን አይችሉም

የዚህ ወጣት ትውልድም ይሄን መርህ በመከተል በስደተኝነት የተቃኘውን ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ማንሳት አለበ እያልኩህ ነው፡፡ ለሁላችንም የምትበቃ ሰፊ ሃገር እንዳለችን ታውቃለ፡፡ አሁን እንቅፋት የሆነብ ስርዓቱ ነው፡፡ ስርዓቱ እንዳሻ በነፃነት እያሰብ እንድትኖር አይፈቅድልህም ስለዚህ ነፃነት አለበት ወደምለው ሃገር እሰደዳለ፡፡ አያችሁ! ሳንሰደድ እዛ መጋፈጥ ብንችል ለውጥ ማምጣት አይከብደንም፡፡ እስቲ አናበው  ከዚህ በፊት የተሰደዱ ውድ ጋዜጠኞች ሃሳቡን ተጋርተውት ቢሆን ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?

ከዚህ በኋላ ‹‹እምቢ አንሰደድም!›› በሚለው ከተስማማን እንድንሰደድ የሚያደርገንን አካል መታገል ነው፡፡ እንቅፋት የሆነህን ስርዓት መታገል ነው፡፡ ታግለህም ዓላማን የምታሳካበት ስርዓት መመስረት፡፡ ዋናው መፍትሄ ይሄው ነው፡፡

ፍርሃት የሚባለውን ክፉ ወረርሽኝ አሽቀን ጥለ ብዙ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ልንፍ ልንወያይ፦ሃቀኝነትና ቁርጠኝነት ከሃገር ፍቅር ጋር ደባልቀ ልንነሳ ትንሽዋን ትልቅ ለውጥ ልናመጣ ለቆምንለት አላማ አርአያ ልነሆንይገባል።ዋናው መፍትሄ ይሄው ነው፡፡

ከአንድናት ኢትዮጵያ ብሎግ

ኢትዮጵያ ክብር ለዘላለም ትኑር!

No comments:

Post a Comment