Saturday, July 20, 2013

እስረኛው የኢህአዴግ “ዴሞክራሲ”

         እስረኛው ኢህአዴግዴሞክራሲ
የምርጫውውጤትቢያንስ ባለፉት ሰባት ዓመታት በዴሞክራሲው መስክ የተከናወኑትን ድርጊቶች አጠቃሎ ያመለክተናል። ከዚያ አንጻር ዓመታቱ ለእውነተኛ ዴሞክራሲዊ ሽግግር የተከፈቱ የተስፋ በሮች፣ የሕግ እና የተቋም ካባ ባጠለቁ ጸረ ነጻነትና ጸረ ዴሞክራሲያዊ አሠራሮች እየተዘጉ የተመለከትንባቸው ከመሆን አላመለጡም። ይህም ኢትዮጵያውያን ኢሕአዴግን ደገፉም አልደገፉም የሚተዳደሩበት ሥርዓት ተስፋ ያደረጉት ዓይነት የሽግግር ሂደት ከመሆን እየራቀ መሄዱን የሚገነዘቡበት ነው። በተለይም ሽግግሩከስሟልወይምከከሰመ ሰንብቷልአለዚያምከጅምሩም ከዚህ ወደተለየ መዳረሻ አያመራም ነበርበማለት ለሚከራከሩ ሰዎ ከባለቤቱ የተሰጠ ማረጋገጫ ዓይነት ነው። በዚህ ሂደትሽግግሩአዲስኢሕአዴጋዊቅርጽ እየያዘ መምጣቱን የሚመለከቱትአዲሱመንገድ ብቸኛው አማራጭ እንደሆነ ለማመን የታደሉ ወይም የተገደዱ ብቻ ናቸው።
በእርግጥም እንደ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር በአሸናፊዎች ይሁንታ ብቻ በሚጀመርባቸው ማኅበረሰቦች ሂደቱ ከፍተኛ ፈተና እንደሚጠብቀው የታወቀ ነው። የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሽግግር የተጀመረው በደርግ መውደቅ እና በኢሕአዴግ ፈቃድ ነው።በዚህ ለኢሕአዴግ ምስጋና በተገባው ነበር። ይሁንና ያለፉት 22 ዓመታት፤ በተለይም ደግሞ ሰባቱ የቅርብ ዓመታት የኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ሽግግር አንዱ ጋሬጣ ኢሕአዴግ ራሱ መሆኑን እየመሰከሩ ይመስላል። የባለፈ ምርጫ “22 ዓመት ወደኋላበማለት ማለፍየውጤቱንዘላቂ ጣጣ አሳንሶ ማየትን ሊያስከትል ይችላል። ይህ መርጫ 22 ዓመት ወደ ኋላ ብቻ አይደለም፤ 22 ዓመትወደፊትምነው። ኢሕአዴግ ለመጪዎቹ 22 ዓመታት የደገሰልንንዴሞክሬዚ” (Democrazy) ለመረዳት መልካም መነሻ ነው። ፖል ኮሊየርዴሞክሬዚያለው በአንድ መሪ ስብእና ዙሪያ የሚገነባ የአንድ ቡድን/ስብስብ አምባገነናዊና ስግብግብ ሥርዓት መሠረቱ የተጣለ ሆኗል። አሁን በቃላት ሲሽሞነሞን የከረመው የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሽግግር ወደ ሌላ ምዕራፍ መሸጋገሩ በይፋ ታውጇል ማለት ይቻላል። አዲሱ ሽግግር የአንድ ፓርቲ ፍጽም አምባገነንነት ወደሰፈነበት፣ ለዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች የተሟላ ተግባራዊ እውቅና ወደማይሰጥ አዲስ ዓይነት ሥርዓት የሚደረግ ይመስላል።
 ከኢሕአዴግ ጋራ በኢኮኖሚያዊ ጥቅም ወይም በፍርሃት ላልተሳሰሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ (የፖለቲካ አቋም፣ ብሔር፣ የኢኮኖሚ አቅም፣ የእውቀት ደረጃ ሳይለይ) የሚያስተላልፈው መልእክት ግልጽ ነው፤ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሽግግር ይዘት፣ ጥራት እና ፍጥነት የሚወሰነው በአንድ አካል ብቻ ነው። አበቃ። የዘንድሮው ምርጫውጤትትልቁ ኪሳራም ይህ ይመስለኛል፤ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የባለ ድርሻ አካላትን (ኢሕአዴግ በሚያቀርባቸው ውሎች ለመደራደር ፈቃደኛ የሆኑት ጭምር) ፍላጎት እና ሐሳብ በማቀራረብ እያስተናገደ የሚጓዝ ሳይሆን ኢሕአዴግ እየሰፈረ የሚቸረው፣ የአንድ ፓርቲ አምባገነን ሥርዓት ግንባታ መባቻ ብቻ ተደርጓል። በአጭሩ ሲገለጽም የዴሞክራሲ ሽግግራችን የአንድ ቡድን አመለካከት እስረኛ ተደርጓል። ይህም በሂደት እንደታዘብነው የሽግግሩን ዴሞክራሲያዊ ጭላንጭል መለያዎች ጭምር በማጥፋት ላይ የሚገኝ ነው። አደጋው በኢኮኖሚው ዘርፍ በተመዘገቡ ውጤቶች እና በአደባባይ ማስመሰያዎች የተሸፈነ ቢመስልም ከእይታ መሰወር የሚችልበትብ ደረጃ አልፏል። ይህም በተለይ ምርጫ 97 “በድንገትፈጥሮት የነበረው የተፋጠነ ሽግግር ተስፋ በኢሕአዴግ ኢትዮጵያአጋጣሚ ብቻእንደነበር የሚያረዳ ዜና ነው።
ኢሕአዴግ ሕዝብ ከዚህ እውነት እንዲቀስመው የሚፈልገው ትምህርት ግልጽ ነው፤እኔ እላለሁ-ይሆናልም!”ይህ መልእክት በቃልም በተግባርም፤ በግልጽም በስውርም፤ በጉልበትም በሰላምም እየተደባለቀ የሚተላለፍለትአቅመ ቢስኅብረተሰብ ቢያንስ በአፋጣኝ ብዙ መፈናፈኛ አያገኝም። ቢያንስ ለጊዜው አድርግ የሚባለውን ሁሉ ያደርጋል፤ የበለጠ ታማኝ ሆኖ ለመታየት ይሞክራል፤ እየሆነለት/እየሆነበት ያለውን ሁሉ እንደ ትልቅ ጸጋ የሚቆጥረው መስሎ ይታያል ዘመኑን ለመዋጀት ከዚህ የተሻለ መንገድ እስኪያገኝ ይጠብቃል።
ከአንድናት ኢትዮጵያ ብሎግ


ኢትዮጵያ ክብር ለዘላለም ትኑር!

No comments:

Post a Comment