Friday, July 19, 2013

የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት

የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት
የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት የሆነው ገዥዉ ፓርቲ ወያኔ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ "የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት " በሚል መሪ ቃል በትግራይ ዋና ዋና ከተሞች በተለይም በመቀሌ ሊያደርግ ያሰበዉን የጎዳና ላይ ቅስቀሳ እና ህዝባዊ ስብሰባ ሊያደናቅፍ
ደፋ ቀና እያለ እንደሆነ ተነገረ።
በህዝቡ ዘንድ ጺላ የሚል ቅጽል ስም የተሰጣቸዉ እንቅልፍ የለሽ የገዥዉ ፓርቲ ሆድ አደር ካድሬዎች ሰሞኑን ቤት ለቤት እየዞሩ ህዝቡ ወደ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ወደ ማናቸዉ ህዝባዊ ስብሰባ ተቃዋሚዎችን አምኖ እንዳይወጣ ይህን መመሪያ ተላልፎ በተገኘ ማናቸዉም ሰዉ ላይ ከባድ እርምጃ እንወስዳለን እያሉ እንደሚዝቱ ለማወቅ ተችሏል።
የትግራይ ክልል ወዳ ሳይሆን ተገዳ ልማት አሊያም በወለደቻቸዉ ጡት ነካሽ ልጆቿ ተፈርዶባት ዲሞክራሲ ምናምን ምናምን ከሚል የወያኔ ቱልቱላ ጋዜጣ ዉጭ ሌላ ጋዜጣ እንኳ የማይነበብባት የሲኦል ከተማ ናት።
ሌላዉ አስገራሚ ዜና መብታቸዉን በጠየቁ ብቻ በአሸባሪዉ የጸረ ሽብር ህግ ተከሰዉ ወደ ዘብጥያ የተወረወሩትን ንጹሃን ጀግኖችን የአዉሮፓ ፓርላማ ልኡካን ቡድን ሊጎበኝ ፈልጎ ወያኔ ባለመፍቀድ ቆራጭ ፈላጭነቱን አረጋግጧል። ወያኔ ፍርፋሪዉን የሚያገኘዉ ከምእራባዊያን 
ጌቶቹና ከቻይና ሲሆን የሚሰራዉን ስራም መመሪያዎቹና ቀጭን ትእዛዞችን የሚያገኘዉ ከእነርሱ ነበር።
በባሌም በቦሌም ብለን ወያኔን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቅርቡ ወደማጣበት የደደቢት በረሃ ሳይሆን እስከ አሸባሪ ህጎቹ ወደ መቃብር እናዉርደዉ
ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከሚገኙ ጎዛዎች ማናቸንንም የማይወክል ካህዲና ጭራቅ መንግስት ነው። ድል ለኢትዮ ጵያ ህዝብ ዉድቀት ለወያኔ !!!!!!


No comments:

Post a Comment