ወልዲያ ሰላም መስጂድ ከበባ ላይ ነው፡፡
ጁምአ ሐምሌ 12/2005
በወልዲያ ከተማ ሰላም መስጂድ ለጁምአ ሰላት የተገኙ በርካታ ሙስሊሞች በፖሊስ ከበባ ውስጥ ናቸው፡፡ አሁን ከአካባቢው በደረሰን መረጃ የጁምአ ሰላት እንደተጠናቀቀ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ጥይት በመተኮስ ወደ መስጂዱ ቅፅር ጊቢና ወደ ዋናው መስገጃ ክፍል በመግባት በርካታ ወጣቶችን ያገቱ ሲሆን አርጋውያን የሆኑትን መስጂዱን ለቀው ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ አስገድደዋቸዋል፡፡ በሴቶች በኩልም በተመሳሳይ ወደ 18 የሚጠጉ ሙስሊም እህቶቻችንን አፍነው መውሰዳቸው ተረጋግጧል፡፡ በወንዶች በኩል አሁንም ፌዴራል ፖሊሶች መስጂዱን ከበው ከውስጥ ያገቷቸውን ሙስሊሞች ምን እያደረጓቸው እንደሆነ በውል ማወቅ አልተቻለም፡፡ ከአካባቢው ሰዉ እንዲርቅም ፖሊሶች እያስገደዱ ነው፡፡ ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን፡፡
ሀስቡነላህ ወኒዕመል ወኪል።
አቡ ዑቤዳ
http://ecadforum.com/

No comments:
Post a Comment