Sunday, June 30, 2013

          ጄ/ል ክንፈ ወደ ስራቸው ተመለሱ፤ መከላከያ ውጥረት ነግሷል 


      የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ብ/ጄነራል ክንፈ ዳኘው ላለፉት ሶስት ወራት ገደማ ከስልጣናቸው
ታግደው ከቆዩ በኋላ በዚህ ሳምንት ወደ ሃላፊነት መመለሳቸውን የቅርብ ምንጮች ገለፁ። በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ታግደው ከቆዩት ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል አንዱ ጄ/ል ክንፈ እንደሚገኙበት የጠቆሙት ምንጮቹ ስልካቸውን በመጥለፍ በእንቅስቃሴያቸው ዙሪያ ክትትል ይደረግባቸው እንደነበር አስታውቀዋል። ጄ/ል ክንፈ በሳሞራ ታግደው የቆዩት የነአዜብ/በረከትን ቡድን በመቃወም ከነስብሃት ቡድን ጋር በመሰለፋቸው እንደሆነ ምንጮቹ አመልክተዋል። የጠ/ሚ/ር መለስን ሕልፈት ተከትሎ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት ስር እየሰደደ መሄዱንና የልዩነቱ መንስኤም በሕወሐት የተፈጠረው ቀውስ – ጄነራሎቹ ጎራ እንዲለዩ ጫና ማሳደሩን ያመለከቱት ምንጮች፣ አክለውም ልዩነቱ በአገር ጉዳይ ዙሪያ ሳይሆን አንዱ ሌላኛውን በማስወገድ የራስን ጥቅም አስጠብቆ በስልጣን ለመቆየት የሚደረግ የሙስና መጠላለፍ ነው ብለዋል።
ጄ/ል ክንፈ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት በሟቹ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ እንደሆነ ያስታወሱት ምንጮቹ ከስልጣን ሊያግዳቸውም ሆነ ሊያወርዳቸው የሚችለው በህግ ስልጣን የተሰጠው ጠ/ሚኒስትሩ መሆኑን ያስረዳሉ። በዚሁ መሰረት ስልጣኑ በአዋጅ የተቀመጠው ለጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪይም ቢሆንም – በግልፅ የሚታየው ግን ከህግ ውጭ የጄ/ል ሳሞራ ፈላጭ ቆራጭ ውሳኔ ከመሆኑ በተጨማሪ የታገደውን ጄ/ል ወደ ቦታው የሚመልሰው በተቃራኒው የቆመውና በሕወሐት ውስጥ ያለው የነስብሃት ቡድን መሆኑን ምንጮቹ ያመለክታሉ። አቶ መለስ ይዘውት የቆዩትና “በሕገ-መንግስቱ ተሰጠ” ከተባለው ስልጣን በአብዛኛው ለጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪያም ሊሰጥና ሊተላለፍ አልቻለም ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ ቁልፍ የሆነው የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥነትን ጨምሮ በርካታዎቹ ሕገ-ወጥ በሆነ ሁኔታ በሕወሐት ሰዎች ቁጥጥር ስር መውደቃቸውን አመልክተዋል።
         ይህ በእንዲህ እንዳለ- ጄ/ል ሳሞራ የሚመሩት ስብሰባ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች ተሳታፊነት በዚህ ሳምንት ሲካሄድ መሰንበቱን ምንጮች ጠቆሙ። ውጥረትና ያለመረጋጋት በተስተዋለበት የሳሞራ ንግግር በዋና አጀንዳነት የቀረበው የግንቦት ሰባት ጉዳይ ሲሆን በዚህም ፥ « ግንቦት ሰባት በመንግስትና በሕገ-መንግስቱ ዙሪያ መጠነሰፊ አደጋ ጋርጦብናል፤ በግንቦት ሰባት የሚደገፉ በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ላይ አፋጣኝ እርምጃ ልንወስድ ይገባል፤» ማለታቸውን የገለፁት ምንጮቹ፣ ሳሞራ «ለምሳሌ.» ሲሉ ሰማያዊ ፓርቲን እንዲሁም « አንዳንድ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች» በማለት መፈረጃቸውን አስታውቀዋል። በተጨማሪ የሙስሊሙ ማህበረሰብ እያነሳ ያለውን ፍትሃዊ የመብት ጥያቄ፣ ሳሞራ ከግንቦት ሰባት ጋር ለማያያዝ መሞከራቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
           በሌላም በኩል የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ሃላፊ ብ/ጄነራል ተክለብርሃን ወ/አረጋይ በበኩላቸው፥ ከእንግሊዝ አገር ረቀቅ ያለ መሳሪያ በማስመጣት በስካይፕ ተቃዋሚዎች የሚያደርጉትን ግንኙነቶች በመጥለፍና ተዛማች የስለላ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ከገለፁ በኋላ « ግንቦት ሰባት ከግብፅ ጋር ግንኙነት እንዳለው ለህዝቡ ከነገርነው ከጎናችን ይቆማል፣ ግንቦት ሰባትን በማውገዝ የእንቅስቃሴው ተባባሪ አይሆንም፣ በአገር ውስጥ ያሉትም ተቃዋሚዎች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ ህዝቡ አይቃወምም፤ እንዳውም ለመንግስት ድጋፍ ይሰጣል፤» በማለት በተሰብሳቢ መኮንኖች ጭምር ገረሜታን የፈጠረ ንግግር ማድረጋቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል። በዚህም ለሕዝብ ያላቸውን ግምትና የግንዛቤ ደረጃ ያመላከተ ነው ያሉት ምንጮቹ የጄ/ል ተክለብርሃን የእውቀት ደረጃ ምን ድረስ እንደሆነ ያሳየ ነው ብለዋል። የኤንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በአቶ ደብረፂዮን ጭምር በበላይነት እንደሚመራና አቶ ሃ/ማሪያም የሚያውቁት እንደሌለ ምንጮቹ አያይዘው ጠቁመዋል። በሕገ – መንግስቱ መከላከያ ከየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ እንደሆነ ቢደነግግም፣ ከወረቀት በዘለለ ተግባር ላይ ሲውል እንደማይታይና የነሳሞራና ተከታዮቻቸው ተደጋጋሚ አቋምና ተግባር በቂ ማስረጃና ማሳያ መሆኑን ምንጮቹ በሰጡት አስተያየት አስረድተዋል።
በመጨረሻም፥ የታገዱ ሌሎች ጄኔራሎችን ጉዳይ እንዲሁም ባለፈው ወር በሳሞራ ትእዛዝ የተባረሩ የሕወሐት ጄነራሎች ወደ ከፍተኛ ንግድ መሰማራት በተመለከተ ዝርዝር መረጃውን ይዘን እንመለሳለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር።

Saturday, June 29, 2013

የስምንት ሚኒስትሮች ሹመት ሰሞኑን ይፀድቃል

የስምንት ሚኒስትሮች ሹመት ሰሞኑን ይፀድቃል

        የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ዛሬ ግምገማ ያካሂዳል
የኢህአዴግ 36 ከፍተኛ መሪዎችን ያካተተው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመታዊ ግምገማ ለማካሄድ ዛሬ የሚሰበሰብ ሲሆን የስምንት ሚኒስትሮች ሹም ሽርና ሽግሽግ በሚቀጥለው ሳምንት ለፓርላማ ቀርቦ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል፡፡ ለሹመት የሚቀርቡት ባለስልጣናት፤ የፍትህ ሚኒስትር፣ የከተማና ኮንስትራክሽን ልማት ሚኒስትር፣ የግብርና ሚኒስትር፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር፣ የገቢዎች ሚኒስትር የደህንነትና መረጃ ሚኒስትር፣ የደንና አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር እንዲሁም በፓርላማ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ናቸው ተብሏል፡፡ አንዳንዶቹ ሹምሽር እርምጃዎች ሲሆኑ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ወደ አዲስ አበባ አስተዳደር እንዲዛወሩ በተደረጉ ባለስልጣናት ምትክ የሚካሄድ ሽግሽግ ነው፡፡
ይሁን እንጂ የእጩ ተሿሚዎችን ማንነት ለማወቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡ ዛሬ የሚካሄደው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ከሹምሽሩ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ቢታሰብም፣ የሰብስባው ዋና ርዕሰ ጉዳይ አመታዊ ግምገማና አመታዊ እቅድ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት አስፈፃሚ አካል የመቆጣጠር ስልጣን ያለው የአገሪቱ ፓርላማ ጠንካራ የቁጥጥር ሃላፊነቱን በተግባር ማሳየት እንደጀመረ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጭምር ቢናገሩም፤ በሚኒስትሮች ሹመት ዙሪያ ግን የቀድሞው አሰራር አልተሻሻለም፡፡ በተለያዩ ዲሞክራሲያዊ አገራት ውስጥ የእጩ ሚኒስትሮች ማንነት በይፋ ታውቆ ለበርካታ ሳምንታት በፓርላማና በዜጐች ዘንድ ውይይት የሚካሄድበት ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ግን የተሿሚዎች ማንነት የሚገለፀው ሹመታቸው በሚፀድቅበት እለት ነው፡፡
የስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ ዛሬ ስብሰባ እንደሚያካሂድ የገለፁት የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን፤ የስብሰባው ዓላማ የዓመቱን የስራ አፈፃፀም በመገምገም ድርጅቱ በኪራይ ሰብሳቢነት ላይ የሚያካሂደውን ትግል አጠናክሮ ለመቀጠል በእቅዶች ላይ መወያየት ነው ብለዋል፡፡ የህዝቡን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ በማጐልበት የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትን፤ የህዝብ፣ የመንግስትና የድርጅት አቋሞች እንዲጠናከሩ፣ ችግሮች ያሉባቸውን ደግሞ አንጥሮ ለማውጣት ያለመ ስብሰባ ነው ብለዋል፡፡ በነባር ፖሊሲዎችና አሰራሮች ላይ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው መክሮባቸው አቋም ከወሰደባቸው በኋላ፤ የማስፋት፣ የማጠናከርና የማጐልበት እንዲሁም ተጨማሪና አዳዲስ ዝርዝር የአሰራር አቅጣጫዎችን በመተለም በመጪው አመት እቅድ ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ብለዋል – አቶ ሬድዋን፡፡

ወይዘሮ አዜብ እና ”ለመንግስት ተመላሽ ሊደረግ የነበረ ሰባ ሚሊዮን ብር (70.000.000)


ስብሃት ነጋ …ህዝብን የሚያደነቁሩትን እነበረከትንና የጋሪ ፈረስ የሆኑት ሃ/ማሪያምን እርቃናቸውን አስቀሩ::
ሽማግሌውን በቅርብ የሚያውቋቸው የፓርቲው ሰዎች « ስብሃት ከበረሃ ጀምሮ በቀለኛ ነው። ጥርሱ ውስጥ የገባን ሰው ካላስወገደ እንቅልፍ አይወስደውም፤ ብዙ ሰው አጥፍቶዋል። አሁንም አዜብን እግር በእግር የሚከታተለው ለዚሁ ነው» ይላሉ።
አባተ ኪሾ ከደቡብ ባጀት ተመላሽ የሆነ ሰባ ሚሊዮን ብር (70.000.000) ለመንግስት ተመላሽ ሊያደርጉ ሲሉ …« ወዲህ በል..የምን መንግስት ነው?» በማለት ተቀብለው ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን አባተ ፍ/ቤት ጭምር ያጋለጡት ነው። ስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ደግሞ ታምራት ላይኔ በውሸት እንዲመሰክር አምስት ጊዜ አግባብተውት እንቢ ሲል ከማስደብደባቸው በተጨማሪ ሌላ ክስ እንዲመሰረትበት አድርገዋል። አቃቤ ሕግ የነበረው ዮሃንስ ወ/ገብርኤል የነስብሃትን የውሸት ክስ ተቀብዬ ተግባራዊ አላደርግም፤ ህሊናዬ አይቀበለውም .. በማለቱ ብቻ ለአምስት አመት እንዲታሰር አላደረጋችሁም?…ብዙ ማስረጃና መረጃ መደርደር ይቻላል።..
ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስበውት ይሁን ሳያስቡት “እውነት” አምልጧቸዋል። አጥብቀው ያነሷቸው የሙስና ጉዳዮች ራሱን የቻለ « አላማና ግብ » አላቸው። የመጀመሪያው በፓርቲያቸው ውስጥ ያለው ክፍፍል (የጥቅም) እንደተዳፈነ እሳት ውስጥ ለውስጥ እየተብላላ መሆኑን በግልፅ ያሳያል። ከተናገሩት የሚከተለውን እንመልከት፤ « .በጤናማ ሁኔታ የሚገኙ ሰዎችን እንቆርጣለን፣ እናስራለን ወዘተ እያሉ ሲያስፈራሩ የነበሩ የፖለቲካ፣ የመንግስት ሰዎች ነን የሚሉ የፀጥታና የስነ አእምሮ ሁከት ፈጥረዋል። መቶ ሚሊዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፣ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡት ያታያሉ። » ብለዋል። « እንቆርጣለን » ያሉት መለስ ዜናዊ ናቸው፤ መለስ በአደባባይ ይህን ከመናገር አልፈው ሲያስፈራሩም እንደነበር እናስታውሳለን። መለስ ያንን ያሉት በ10ሺዎች የሚገመት ቡና ከመጋዘን ጠፋ በተባለበት ወቅት ነው። ያንን ቡና የሰረቁትና ባህር ማዶ ሸጠው ገንዙቡን ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ምንጭ ተጠቅሶ ይፋ ተደርጓል። እናም ስብሃት “መቶ ሚሊዮን የሰረቁ..» ያሉት አዜብ መስፍንን ሲሆን፣ « ያስዘረፉ» ያሉት ደግሞ ባለቤታቸው አቶ መለስን ነው። « 10ሺህ የሰረቁ..» የተባሉት በቅርቡ የታሰሩት የጉምሩክ ሰዎችን ሲሆን..እነዚህን በንፅፅር ያስቀመጡት የአዜብ (ተላላኪዎች) ስርቆት መጠነሰፊ መሆኑን ለማመላከት ነው። ስብሃት እስካሁን አድፍጠው ቆይተው በዚህ ሰሞን ይህን መናገራቸው ..«አዜብ የከተማዋ ም/ል ከንቲባ ይሆናሉ» የሚባለውን በመስማታቸው ሆን ብለው ያደረጉት ነው፥ ይላሉ ታዛቢዎች።
« ሙስና ከተነሳ ስብሃትም እስከአንገቱ ተነክሮበታል። በገርጂና ሳር ቤት የሚገኘው በአሜሪካ በሚኖሩ ስጋ ዘመዶቹ ስም እንዲሁም በቀድሞ የአየር ሃይል ጄ/ል ሰሎሞን ስም የሚንቀሳቀስ ግን የስብሃት የግል ንብረት መሆኑን የማይታወቅ መስሎት ነው?….ጎንደር -ሑመራ ያለው የሰሊጥ እርሻ የስብሃት አይደለም?…በ10ሚሊዮን ብር በሚገመት በመቀሌ (አፓርታይድ መንደር) ስብሃት ዘመናዊ ቪላ እንደሚገነባ አይታወቅም ብሎ ይሆን?…» ሲሉ እነዚህ ወገኖች የስብሃትን ሙስና በከፊል ይጠቅሳሉ።
ስብሃት በዚህ አላበቁም፤ « ..እስካሁን ከፍተኛ ሙሰኞች ትንሹን ሙሰኛ ከሰው አሳስረው ያስፈርዱና ያሰቃዩ ነበር ይባላል። ከፍተኛ ሙሰኞች ከመርማሪው ጀምረው አቃቤ ሕጉም ዳኛው፣ ምስክሩም ይቆጣጠራሉ። ትንሽ የሰረቀም ምንም ያልሰረቀም ሲሰቃዩና ሲያደኸዩ የነበሩም፤ አሉም ይባላል። ስልክ እየደወሉም ይፈርዱ ነበር ይባላል።» ብለው አረፉት ስብሃት። ትክክል ናቸው!! ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ « ይህን ካልፈረድሽ በመኪና ገጭተን ነው የምንገድልሽ » ተብላለች። ያውም ከቤተ መንግስት ተደውሎ።
አሁን ስብሃት ተናገሩት እንጂ…ህዝቡ ብሎ-ብሎ የታከተው ነገር ነው!! እነ እስክንድር፣መሃመድ አቡበከር፣ አንዷለም አራጌ፣ ርእዮት አለሙ….ወዘተ በርሶ ጓደኞች በስልክ ትእዛዝ የተፈረደባቸው ናቸው!!… «ፍትሃዊ ስርአትና መንግስት አለ..» እያሉ ህዝብን የሚያደነቁሩት እነበረከትና የጋሪ ፈረስ የሆኑት ሃ/ማሪያም እርቃናቸውን የሚያስቀር ነገር ነው በስብሃት የተቀመጠው።

"ለመንግስት ተመላሽ ሊደረግ የነበረ ሰባ ሚሊዮን ብር (70.000.000)ወይዘሮ አዜብ ወደ ኪሳቸው ከተውታል::"አባተ ኪሾ/ለፍርድ ቤት
ስብሃት ነጋ ...ህዝብን የሚያደነቁሩትን እነበረከትንና የጋሪ ፈረስ የሆኑት /ማሪያምን እርቃናቸውን አስቀሩ::
ሽማግሌውን በቅርብ የሚያውቋቸው የፓርቲው ሰዎች « ስብሃት ከበረሃ ጀምሮ በቀለኛ ነው። ጥርሱ ውስጥ የገባን ሰው ካላስወገደ እንቅልፍ አይወስደውም፤ ብዙ ሰው አጥፍቶዋል። አሁንም አዜብን እግር በእግር የሚከታተለው ለዚሁ ነው» ይላሉ።
አባተ ኪሾ ከደቡብ ባጀት ተመላሽ የሆነ ሰባ ሚሊዮን ብር (70.000.000) ለመንግስት ተመላሽ ሊያደርጉ ሲሉ …« ወዲህ በል..የምን መንግስት ነውበማለት ተቀብለው ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን አባተ /ቤት ጭምር ያጋለጡት ነው። ስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ደግሞ ታምራት ላይኔ በውሸት እንዲመሰክር አምስት ጊዜ አግባብተውት እንቢ ሲል ከማስደብደባቸው በተጨማሪ ሌላ ክስ እንዲመሰረትበት አድርገዋል። አቃቤ ሕግ የነበረው ዮሃንስ /ገብርኤል የነስብሃትን የውሸት ክስ ተቀብዬ ተግባራዊ አላደርግም፤ ህሊናዬ አይቀበለውም .. በማለቱ ብቻ ለአምስት አመት እንዲታሰር አላደረጋችሁም?…ብዙ ማስረጃና መረጃ መደርደር ይቻላል።..
ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስበውት ይሁን ሳያስቡትእውነትአምልጧቸዋል። አጥብቀው ያነሷቸው የሙስና ጉዳዮች ራሱን የቻለ « አላማና ግብ » አላቸው። የመጀመሪያው በፓርቲያቸው ውስጥ ያለው ክፍፍል (የጥቅም) እንደተዳፈነ እሳት ውስጥ ለውስጥ እየተብላላ መሆኑን በግልፅ ያሳያል። ከተናገሩት የሚከተለውን እንመልከት፤ « .በጤናማ ሁኔታ የሚገኙ ሰዎችን እንቆርጣለን፣ እናስራለን ወዘተ እያሉ ሲያስፈራሩ የነበሩ የፖለቲካ፣ የመንግስት ሰዎች ነን የሚሉ የፀጥታና የስነ አእምሮ ሁከት ፈጥረዋል። መቶ ሚሊዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፣ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡት ያታያሉ። » ብለዋል። « እንቆርጣለን » ያሉት መለስ ዜናዊ ናቸው፤ መለስ በአደባባይ ይህን ከመናገር አልፈው ሲያስፈራሩም እንደነበር እናስታውሳለን። መለስ ያንን ያሉት 10ሺዎች የሚገመት ቡና ከመጋዘን ጠፋ በተባለበት ወቅት ነው። ያንን ቡና የሰረቁትና ባህር ማዶ ሸጠው ገንዙቡን ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ምንጭ ተጠቅሶ ይፋ ተደርጓል። እናም ስብሃትመቶ ሚሊዮን የሰረቁ..» ያሉት አዜብ መስፍንን ሲሆን፣ « ያስዘረፉ» ያሉት ደግሞ ባለቤታቸው አቶ መለስን ነው። « 10ሺህ የሰረቁ..» የተባሉት በቅርቡ የታሰሩት የጉምሩክ ሰዎችን ሲሆን..እነዚህን በንፅፅር ያስቀመጡት የአዜብ (ተላላኪዎች) ስርቆት መጠነሰፊ መሆኑን ለማመላከት ነው። ስብሃት እስካሁን አድፍጠው ቆይተው በዚህ ሰሞን ይህን መናገራቸው ..«አዜብ የከተማዋ / ከንቲባ ይሆናሉ» የሚባለውን በመስማታቸው ሆን ብለው ያደረጉት ነው፥ ይላሉ ታዛቢዎች። « ሙስና ከተነሳ ስብሃትም እስከአንገቱ ተነክሮበታል። በገርጂና ሳር ቤት የሚገኘው <ሉሲ አካዳሚ > በአሜሪካ በሚኖሩ ስጋ ዘመዶቹ ስም እንዲሁም በቀድሞ የአየር ሃይል / ሰሎሞን ስም የሚንቀሳቀስ ግን የስብሃት የግል ንብረት መሆኑን የማይታወቅ መስሎት ነው?….ጎንደር -ሑመራ ያለው የሰሊጥ እርሻ የስብሃት አይደለም?…10ሚሊዮን ብር በሚገመት በመቀሌ (አፓርታይድ መንደር) ስብሃት ዘመናዊ ቪላ እንደሚገነባ አይታወቅም ብሎ ይሆን?…» ሲሉ እነዚህ ወገኖች የስብሃትን ሙስና በከፊል ይጠቅሳሉ።

       ስብሃት በዚህ አላበቁም፤ « ..እስካሁን ከፍተኛ ሙሰኞች ትንሹን ሙሰኛ ከሰው አሳስረው ያስፈርዱና ያሰቃዩ ነበር ይባላል። ከፍተኛ ሙሰኞች ከመርማሪው ጀምረው አቃቤ ሕጉም ዳኛው፣ ምስክሩም ይቆጣጠራሉ። ትንሽ የሰረቀም ምንም ያልሰረቀም ሲሰቃዩና ሲያደኸዩ የነበሩም፤ አሉም ይባላል። ስልክ እየደወሉም ይፈርዱ ነበር ይባላል።» ብለው አረፉት ስብሃት። ትክክል ናቸው!! ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ « ይህን ካልፈረድሽ በመኪና ገጭተን ነው የምንገድልሽ » ተብላለች። ያውም ከቤተ መንግስት ተደውሎ።

አሁን ስብሃት ተናገሩት እንጂህዝቡ ብሎ-ብሎ የታከተው ነገር ነው!! እነ እስክንድር፣መሃመድ አቡበከር፣ አንዷለም አራጌ፣ ርእዮት አለሙ….ወዘተ በርሶ ጓደኞች በስልክ ትእዛዝ የተፈረደባቸው ናቸው!!… «ፍትሃዊ ስርአትና መንግስት አለ..» እያሉ ህዝብን የሚያደነቁሩት እነበረከትና የጋሪ ፈረስ የሆኑት /ማሪያም እርቃናቸውን የሚያስቀር ነገር ነው በስብሃት የተቀመጠው።


ኢትዮጵያ ክብር ለዘላለም ትኑር!