Tuesday, March 8, 2016

የተማሪዎች ተቃውሞ በአዲስ አበባ- DW

የአዲስ አበባ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፖሊስ የኃይል ርምጃ እንዲያበቃ በመጠየቅ ዛሬ በከተማይቱ ተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን ዜና ምንጭ ሮይተርስ ዘገበ።


19102632http://www.dw.com/am/%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%88%9B%E1%88%AA%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%89%B0%E1%89%83%E1%8B%8D%E1%88%9E-%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5-%E1%8A%A0%E1%89%A0%E1%89%A3/a-19102632
አደባባይ የወጡት ተማሪዎች የተቀናጀውን የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ የከተማ ማስፋፊያ እቅድን በመቃወም ከጥቂት ወራት ወዲህ የተካሄዱትን ሰልፎች ተከትሎ ፖሊስ አስፋፍቶታል ያሉትን የኃይል ርምጃ ነው የተቃወሙት። መንግሥት እቅዱን ባለፈው ታህሳስ ቢሰርዘውም፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬ፣ «እኛ ሽብርተኞች አይደለንም፣ የኦሮሞ ሕዝብን መግደል አቁሙ» የሚሉ መፈክሮችን በመያዝ በሁለት አቅጣጫዎች ፣ ለኢትዮጵያ ዋና ርዳታ አቅራቢ ወደሆነችው ወደ አሜሪካ ኤምባሲ ማምራታቸውን ዜና ምንጩ አክሎ አስረድቶዋል። ስለተቃውሞ ሰልፉ የመንግሥት ቃል አቀባይ አስተያየት እንዲሰጡ ዜና ምንጩ ላቀረበው ጥያቄ መልስ እንዳላገኘ ገልጾዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በኦሮሚያ ክልል ለተነሳው ቅሬታ መንግሥታቸው መፍትሔ እንደሚፈልግለት ቀደም ሲል ቃል መግባታቸው እና ዓማፅያን ቡድኖች ለሁከቱ ተጠያቂዎች ናቸው ሲሉ መውቀሳቸው የሚታወስ ነው። ዜና ምንጩ የመብት ተሟጋች ቡድኖችን እና በዩኤስ አሜሪካ ያሉ ተቃዋሚዎችን በመጥቀስ እንዳመለከተው፣ የመንግሥቱ እቅድ በቀሰቀሰው ከፍተኛ ተቃውሞ እስከ 200 የሚጠጉ ሰዎች ተገድለዋል። የመንግሥት ባለስልጣናት የሞተው ሰው ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑን ቢያስታውቁም፣ ትክክለኛውን ቁጥር አልገለጹም።
ስለ ሁኔታዉ ነጋሽ መሐመድ የአዲስ አበባዉን ወኪላችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሄርን በስልክ ጠይቆት ነበር።
አርያም ተክሌ
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሄር
ነጋሽ መሐመድ
Source: DW

Ethiopian students demand end to police crackdowns in rare protest

By Aaron Maasho
ADDIS ABABA (Reuters) - Dozens of university students protested in Ethiopia's capital on Tuesday, demanding an end to police crackdowns that followed months of demonstrations over plans to requisition farmland in the country's Oromiya region late last year.
The government wanted to develop farmland around the capital, Addis Ababa, and its plan triggered some of the worst civil unrest for a decade, with rights groups and U.S.-based dissidents saying as many as 200 people may have been killed.
Officials suggest the figure is far lower but have not given a specific number.
Ethiopia has long been one of the world's poorest nations but has industrialized rapidly in the past decade and now boasts double-digit growth. However, reallocating land is a thorny issue for Ethiopians, many of whom are subsistence farmers.
Authorities scrapped the land scheme in January, but sporadic demonstrations persist and, on Tuesday, students from Addis Ababa University marched in two groups toward the embassy of the United States, a major donor, holding signs that read "We are not terrorists. Stop killing Oromo people."
Such protests are rare in a country where police are feared as heavy-handed and the government is seen as repressive.
A government spokesman did not immediately respond to requests for comment.
Ethiopia's Prime Minister Hailemariam Desalegn has promised to address grievances in the Oromiya region and says he blames rebel groups for stoking violence.  
Opponents blame harsh police tactics.
"The aim was to highlight the abuses carried out in the region," one student told Reuters, saying he did not want to be identified for fear of reprisals.
"We waved white cloth to indicate that we were peaceful protesters. But police started beating us up," he said.
New York-based Human Rights Watch said last month that protesters it spoke to and who had been detained after the outbreak of demonstrations in November had been subjected to severe beatings and never appeared before a judge.
The group said women suffered sexual assaults and mistreatment. It said one 18-year-old student was "given electric shocks to his feet".
Officials dismissed the report as not worthy of comment.
(Editing by Edith Honan and Louise Ireland)

Source: Reuters

የስድስት ሰዓት ሴት ተጠያቂዎች

በማሕሌት ፋንታሁን
ጥቂት ስለ ቃሊቲ የሴቶች መቆያ እና ማረሚያ ቤት
የማይቻል ነገር እንደሌለ በተግባር ለማየት ከሚያስችሉ ሁኔታዎች አንዱ የእስር ቤት ሕይወት ነው። እስር ቤት እንገባለን የሚል እሳቤ በአይምሯችን ውስጥ ስለማይኖር በአብዛኛው ከተለመደው የኑሮ ዑደት (መወለድ፣ ማደግ፣ መማር፣ መሥራት፣ ማግባት፣ መውለድ፣ ማደርጀት እና መሞት) እና ተያያዥ ጉዳዮች ተነስተን ነው የግል አቋማችንን የምንቀርፀው። "ከሰው ጋር መተኛት አልወድም/አልችልም፤ እንቅልፍ አይወስደኝም"፣ "ስፕሪስ ሳልጠጣ መዋል አልችልም"፣ "የቀዘቀዘ ምግብ አልወድም"፣ "ሲጃራ ሳላጨስ መኖር አልችልም"፣ "በቀን ቢያንስ ሁለት ፊልሞችን ካላየሁ አልደሰትም"፣ "እከሊትን/እከሌን ሳላይ መዋል አልችልም"፣ "ጨለምለም ካላለ ወደ ቤት መግባት አልወድም"፣ "መብራት ካልጠፋ እንቅልፍ አይወስደኝም" እና የመሳሰሉ የማይለወጡ የሚመስሉን አቋሞቻችን ፈተና ውስጥ የሚወድቁት የእስር ሕይወትን ‹ሀ› ብለን ስንጀምር ነው። ብዙ አልችልም ብዬ የማስባቸውን ነገሮችን ችዬ ስለወጣሁበት ስለ ቃሊቲ የሴት እስረኞች ግቢ ጥቂት ልበላችሁ።
በቃሊቲ እስር ቤት ግቢ ውስጥ ከሚገኙት 8 ዞኖች ሁለቱ የሴት እስረኞች የሚኖሩበት ነው። በአንደኛው ዞን በቀጠሮ ላይ የሚገኙ ሴቶች በሌላኛው ደግሞ የተፈረደባቸው ሴቶች ይኖሩበታል። ልዩ ጥበቃ ወይም የቅጣት ቤት የሚባሉ ቤቶች አሉ። ወይም በተፈለገበት ሰዓት ይሠራሉ። ለምሳሌ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ከማንም እስረኛ ጋር እንዳትገናኝ 5ት ሰው ብቻ የሚኖርበት የቅጣት ቤት ውስጥ ነበር የምትኖረው። ISISን በመቃወም ከተጠራው ሰልፍ ጋር በተያያዘ ሚያዚያ ወር 2007 የታሰሩ ሴቶች ከሌሎች ጋር እንዳይገናኙ ለብቻቸው በተሠራላቸው ቤት ይኖሩ ነበር።
በቀጠሮ ዞን ደግሞ 5 ቤቶች ያሉ ሲሆን በፍርደኛ ግቢ 6 ቤቶች አሉ።አንድ ቤት ውስጥ ከ 40 እስከ 120 እስረኞች ይኖራሉ። ቀጠሮ ግቢ ከአንዲት አነስተኛ ሱቅ በስተቀር ሌላ ምንም ስለሌለ የተለያዩ ነገሮችን ለመገበያየት እና ፀጉር ቤት ለመጠቀም ፍርደኛ ግቢ መሄድ ግድ ይላል። ቤተሰብ መጠየቂያ ቦታው የፍርደኛ ግቢን አቋርጦ የሚገኝ ቦታ በመሆኑ፤ በቤተሰብ መጠየቂያ ሰዓቶች (ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6:00 ከሰዓት ከ7:30 እስከ 10:00 እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ጠዋት ከ2:30 እስከ 6:00)፤ ቀጠሮ ክልል የሚገኙ እስረኞች ከፍርደኛ ክልል ማግኘት የሚፈልጉትን ነገር ማግኘት ይችላሉ። በቀጠሮ እና ፍርደኛ ክልል መሐል 200 ሜትር ገደማ ርቀት ያለው ሲሆን በየግቢዎቹ በር እና ማማዎች ላይ ጠባቂ ፓሊሶች አሉ። ዞኖቹ (ቤቶቹ) ከአስተዳደር ጀምሮ በእስረኞች በተመረጡ የእስረኛ ኮሚቴዎች ይመራል። በየቤቱ ለሊት የሚደረግ ጥበቃ አለ። ሮንድ ይባላል። እያንዳንዷ እስረኛ ተራዋ በደረሰ ቀን ለሁለት ሰዓት ከሌላ አንድ እስረኛው ጋር ይጠብቃል። ከለሊቱ 5:00 ሰዓት እስከ 7:00 እና ከ7:00 ሰዓት እስከ 9:00 ሮንድ ተረኞች የሚጠብቁበት ሰዓት ነው። የእስረኞች ቆጠራ በቀን ሁለቴ ይካሄዳል። የጠዋት ገቢ ፓሊሶች ከጠዋቱ 12:00 ላይ፤ 11:30 ላይ ደግሞ የማታ ገቢ ፓሊሶች ቆጥረው ይረከባሉ።
የስድስት ሰዓት ተጠያቂዎች
ከላይ የጠቀስኳቸው የእስረኛ "መብቶች" እኛ የስድስት ሰዓት ተጠያቂዎች ጋር ሲደርስ ቅንጦት ይሆናሉ። እንኳን በውናችን በሕልማችንም አናስበውም። "ይቺም ቂጥ ሆና ለሁለት ተከፈለች" ዓይነት ነገር ነው። ያም መብት ተብሎ ተሸራርፎ ሲሰጠን እና ስንከለከል "All animals are equal but some are more equal" የሚለው አባባል ትዝ ይለኛል። የስድስት ሰዓት ተጠያቂዎች ማለት በሽብር ወይም በአመፅ ማነሳሳት የሚል ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸውን በቀጠሮ ክልል ሆነው የሚከታተሉ ወይም ተፈርዶባቸው ፍርደኛ ክልል ያሉ ሴቶች ማለት ናቸው። ስያሜው የመጣው ከቤተሰብ ጋር ከምንገናኝበት ሰዓት የተወሰደ ነው። የምንጠየቀው 6 ሰዓት ላይ ብቻ ሲሆን እኔ በቆየሁባቸው ጊዜያት ከ10 ደቂቃ እስከ 30 ደቂቃ ለሚሆን ቅፅበት ነበር። የመጀመሪያዎቹ የስድስት ሰዓት ተጠያቂዎች ለ5 ደቂቃ ብቻ ይገናኙ እነደነበር ሰምቻለሁ። ከዚህ በተጨማሪም የምንጠየቀው በቅርብ ቤተሰቦች ብቻ ነው። ያለንበት ዞንም ሆነ ቤት በኮሚቴነት መመረጥም መምረጥም አንችልም። ሮንድ ጥበቃ እኛን አያካትትም። ፍርደኛ ግቢ ሄዶ መገበያየት ይናፍቀናል። ቢበዛ የ6 ሰዓት ተጠያቂ ያልሆነ (ኖርማል) እስረኛ እንድንልክ ቢፈቀድልን ነው። ሆኖም ግን አስጠጪ እስረኞች ሰበብ ፈልገው የሚላኩትን ኖርማል እስረኞች ለአሸባሪ ይላላካሉ የሚል ክስ ስለሚያቀርቡባቸው፤ የሚላክልን ማግኘት እስቸጋሪ ነው።
ክሊኒክ እና ፀጉር ቤት ለመሄድ ስንፈልግ ለብቻችን አጃቢ ተመድቦልን ነው። የምትመደብልን አጃቢ ፀጉር ቤት ውስጥ ገብታ ተሰርተን እስክንጨርስ ጠብቃ ይዛን ትመለሳለች። ይሄ ሲገርመን የሆነ ጊዜ ላይ ፓሊሶች የሚሰሩበት ፀጉር ቤት እንድንጠቀም መመሪያ ተላለፈ። ይህ መመሪያ ከተላለፈ በኋላ የሆነ ቀን ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ ፀጉር ቤት ለመሄድ ጠይቃ፤ አጃቢዋ እየወሰደቻት የተላለፈውን መመሪያ ስትነግራት "እኔ እስረኛ ነኝ። ለምንድነው የፓሊስ ፀጉር ቤት የምሰራው? ይቀራል እንጂ!" ብላ ፀጉሯን መሠራቱን ትታ ተመለሰች። እስክትወጣ ድረስም በአቋሟ እንደፀናች ነበር። ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬም የሚደርስብንን መገለል በመቃወም ፀጉሯን በመላጨት መልዕክት አስተላልፋአለች።
ስድስት ሰዓት ላይ ቤተሰብ ልንጠይቅ ስንወጣ እና ስንገባ በአጃቢ ነው። ቤተሰብ ስናወራም የምናወራውን የሚሰሙ ከኛም ከቤተሰባችንም በኩል ፓሊሶች ይቆማሉ። ቤተሰብ ለማገናኘት ከሚወስዱን አጃቢ ፓሊሶች በማይሰሙት ቋንቋ ከቤተሰብ ጋር ማውራት አይቻልም። ከግቢያችን ስንወጣም ሆነ ወደ ግቢያችን ስንገባ ከኖርማል እስረኞች በተለየ ብርበራ ይካሄድብናል። ቤተሰብ ልንገናኝ ስንሄድ ፍርደኛ ክልል ያሉ የሚያቁን እስረኞችን ጋር በዓይን እንኳን ሰላም መባባል አይቻልም። እነሱም ሰላም ካሉን የተለያየ ቅጣት ይደርስባቸዋል። እኛ በምናልፍበት ሰዓት ከቤት እንዳይወጡ መከልከል፣ በካቴና መታሰር እና በአጃቢ መንቀሳቀስ የተለመዱት ዓይነት ቅጣቶች ናቸው። ባስ ሲልም እስከ አመክሮ መከልከል ይደርሳል። ማንኛውም ዓይነት ጽሑፍ የተጻፈባቸው ማስታወሻ ደብተሮቻችን በፍተሻ ወቅት ይወሰዳሉ። ፍተሻዎች እኛ ላይ እና ከኛ ጋር ይቀራረባሉ የሚባሉ እስረኞች ላይ ይበረታል። በፍተሻ ወቅት እራሳቸው ሳንሱር አድርገው ያስገቡት መጽሐፍ ሳይቀር ይወሰድብናል። መጽሐፍት ሳንሱር ሰበብ እንዳይገቡ/እንዲመለሱ ይደረጋል። ከሚገቡልን መጽሐፍት የሚመለሱት ይበልጡ ነበር። ሌሎች እስረኞችን በማይመለከት "ሕግ" በመተዳደራችን የተነሳም፤ በእስረኞችም ሆነ በፓሊሶች ዘንድ እንደ ልዩ ፍጡር ነው የምንታየው።
ቤተሰቦቻችንም ሊጠይቁን ሲመጡ የሚደርስባቸው እንግልት ከሁሉ የከፋ ነው። እኛ እስረኞች በመሆናችን የመጠየቂያ ሰዓታችን መቼም ሆነ መቼ ለውጥ የለውም። ጠያቂዎቻችን ግን ከ6 ሰዓት በፊት ግቢ ውስጥ መድረስ አለባቸው። አንድ ደቂቃ እንኳን አሳልፈው በር ላይ ቢደርሱ የሚሰማቸው የለም። በዚህ ምክንያት ቤተሰቦቻችን በር ደርሰው ሳያዩን የሚመለሱባቸው ቀናት ጥቂት አይደሉም። በ6ሰዓት ተጠያቂዎች እና ጠያቂዎች ላይ የሚደርሰው በደል ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም።
በሕገ መንግሥታችን አንቀፅ 21 ላይ በጥበቃ ስር እና ተፈርዶባቸው በእስር ስላሉ ሰዎች መብት ሲያስቀምጥ ምንም አይነት ልዩነት አላስቀመጠም። ወንዶች ጋር ከታዋቂ ጋዜጠኞች፣ የፓርቲ አመራራት እና የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በስተቀር የስድስት ሰዓት ተጠያቂ የሚባል ነገር የለም። ከተመሳሳይ ወንጀል ከተከሰሱ/ከተፈረደባቸው ወንዶች ጋር እንኳን በእኩል አይደለም እንታይ የነበረው። በዚህም በሕገመንግስቱ አንቀፅ 35 የተደነገገውን የሴቶች ከወንዶች ዕኩል የመታየት መብት የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር መጣሱን ማየት ይቻላል። እነዚህ በሕገ መንግሥት የተደነገጉ መብቶች፤ በማረሚያ ቤቱ አስተዳደር እየተጣሰ እንዳለ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ብናሰማም ተገቢውን ምላሽ አናገኝም። ወይ በማረሚያ ቤት አስተዳደር ጉዳይ አያገባኝም ይላሉ፣ ወይም የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ምላሽ እንዲሰጥበት ያዛሉ። የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ኃላፊዎች በአካልም ተገኝተውም፤ በጽሑፍም የስድስት ሰዓት ተጠያቂ የሚባል ነገር እንደሌለ እና ከሌሎች እስረኞች በተለየ አናያቸውም ብለው ዓይን ያወጣ ውሸት ይዋሻሉ። እነዚሁ ኃላፊዎች ወደ ግቢ ሲመለሱ የስድስት ሰዓት ተጠያቂዎች ብለው በማስታወቂያ አስጠርተው ይሰበስቡንና ፍርድ ቤት መናገራችን ለውጥ እንደማያመጣ ይነግሩናል።
ታዲያ እራሱ መንግሥት ለሴቶች አስከበርኩ ያለውን መብት እራሱ እየጣሰ፤ ግን ደግሞ በየዓመቱ የሴቶች ቀን እያለ ስለ ሴቶች መብት መደስኮር በፍፁም የማይጣጣም እና የኢሕአዴግን መንግሥት ግብዝነት የሚያሳይ ነው።
በቃሊቲ የስድስት ሰዓት ተጠያቂ የነበሩ እንዲሁም አሁንም እዛው ያሉ ሴት እስረኞች* ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው።
1. እማዋይሽ ዓለሙ - በ2001 ሚያዚያ ወር ጀምሮ በእስር ትገኛለች። መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ተንቀሳቅሳችኋል በመባል በእነ ብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ ከተከሰሱት ውስጥ አንዷ ስትሆን የዕድሜ ልክ ፍርድ ተፈርዶባት በቃሊቲ የምትገኝ ነች።
2. ሒሩት ክፍሌ - ከ2003 ሰኔ ወር ጀምሮ በእስር ትገኛለች። በነኤልያስ ክፍሌ መዝገብ ከተከሰሱት 5 ሰዎች አንዷ ናት። የሽብር ክስ ተመስርቶባት 14 ዓመት ተፈርዶአባት በቃሊቲ የምትገኝ ነች።
3. ጫልቱ ታከለ - ትውልዷ እና ዕድገቷ ምስራቅ ወለጋ ነው። ከኦነግ ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው በ2000 ከታሰሩ በርካታ ኦሮሞዎች መሃከል አንዷ ናት። የተፈረደባት 12 ዓመት ሲሆን፤ ከ7ዓመት በላይ በእስር አሳልፋለች። አሁን በቃሊቲ ትገኛለች።
4. ባጩ መርጋ - የ18 ዓመት ፍርድ ተፈርዶባት በቃሊቲ የምትገኝ።
5. ቢፍቱ - የ18ዓመት ፍርድ ተፈርዶባት በቃሊቲ የምትገኝ።
6. ድርቤ (ቦንቱ) ኢታና - በ2002 በራሷ ሥም በተከፈተው መዝገብ (እነ ድርቤ ኢታና) ከተከሰሱት 7 ሰዎች አንዷ ስትሆን የሞት ፍርድ ተወስኖባት በቃሊቲ የምትገኝ።
7. ኡርጌ አበበ - በ2002 እነ ድርቤ ኢታና መዝገብ ከተከሰሱት 7 ሰዎች አንዷ ስትሆን የሞት ፍርድ ተወስኖባት በቃሊቲ የምትገኝ።
8. ሃዋ ዋቆ - የቦረና ልጅ ናት። በ2003 በነበቀለ ገርባ መዝገብ ከተከሰሱት 9 ሰዎች አንዷ ናት። በሽብር ተከሳ 5 ዓመት ተፈርዶባት የነበረ እና በ2007 ግንቦት ወር አካባቢ ፍርዷን ጨርሳ የወጣች።
9. ሂንዲያ ኢብራሂም - የሶማሌ ተወላጅ ስትሆን በሽብር ወንጀል ተከሳ 6 ዓመት ተፈርዶባት የነበረ። ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር አካባቢ ፍርዷን ጨርሳ የወጣች።
10. ኡሜማ አሕመድ - የሶማሌ ተወላጅ ስትሆን በሽብር ወንጀል ተከሳ 6 ዓመት ተፈርዶባት የነበረ። ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር አካባቢ ፍርዷን ጨርሳ የወጣች።
11. አበራሽ ኢቲቻ - በ2000 ላይ ለኦነግ የገንዘብ ዕርዳታ በማድረግ እና የኦነግ አባል ናችሁ ተብለው በነኢንጂነር መስፍን አበበ መዝገብ ከተከሰሱት 16 ሰዎች ውስጥ አንዷ ናት። አስር ዓመት ተፈርዶባት በ2007 ሰኔ ወር ላይ ፍርዷን ጨርሳ ከእስር ተለቃለች።
12. ህደያ ከድር - በ2006 ነሐሴ ወር በረመዳን ፆም ወቅት ተቃውሞ በነበረባቸው ጁምአ ቀናት በአንዱ ቀን ከመንገድ ላይ ተይዛ ከእህቷ ራቢያ ከድር ጋር የታሰረች። 5ወር ተፈርዶባት የነበረ ሲሆን ፍርዷን ጨርሳ የወጣች።
13. ራቢያ ከድር - በ2006 ነሐሴ ወር የረመዳን ፆም ወቅት ተቃውሞ በነበረባቸው ጁምአ ቀናት በአንዱ ቀን ከመንገድ ላይ ተይዛ ከእህቷ ህደያ ከድር ጋር የታሰረች። 5ወር ተፈርዶባት የነበረ ሲሆን ፍርዷን ጨርሳ የወጣች።
14. ሃያት አሕመድ - ከሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ጋር በተያያዘ ከአዳማ ከተማ ከተያዙ ሙስሊሞች አንዷ ናት (በእነ አብዱላዚዝ መዝገብ)። በ2005 የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስዳ ውጤቷን በመጠባበቅ ላይ እያለች ነው የድንገቴ እስር የገጠማት። በእስር ሆና ክሷን ለዓመት ከስምንት ወር ስትከታተል ቆይታ በነፃ ተለቃለች። (ማእከላዊ 4 ወር ቆይታለች)
15. ፈቲያ መሐመድ - ከሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጋር በተያያዘ ከአዲስ አበባ እና ከሌሎች ዩንቨርስቲ እና ኮሌጅ ተይዘው ከታሰሩት ውስጥ ናት። ለዓመት ከስድስት ወር ያክል ክሷን በእስር ሆና ስትከታተል ቆይታ 6 ወር የተፈረደባት ሲሆን ከተፈረደባት የፍርድ ልክ በላይ በእስር በመቆየቷ በጥቅምት ወር 2007 ከእስር ወጥታለች። (ማእከላዊ 4 ወር ቆይታለች)
16. መርየም ሐያቱ - ከሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጋር በተያያዘ ከአዲስ አበባ እና ከወልቂጤ ኮሚቴውን ለመተካት ሲንቀሳቀሱ ነበር ተብለው ከተያዙት (እነ ኤልያስ ከድር) ውስጥ አንዷ ናት። መርየም በ2005 መጨረሻ አካባቢ ከወልቂጤ ነው የተያዘችው። ከሁለት ዓመት አራት ወር የፍርድ ቤት መንከራተት በኋላ በታኅሳስ ወር 2008፣ 7ዓመት ተፈርዶባት ቃሊቲ የምትገኝ። (ማእከላዊ 4ት ወር ቆይታለች)
17. ሃያተልኩብራ ነስረዲን - ከ5ት ወር የማዕከላዊ ቆይታ በኋላ ‹የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ› የተባለ ‹የሽብርተኛ ድርጅት› ጋር ግንኙነት በማድረግ በሚል ሐምሌ ወር 2007 ላይ ክስ ከተመሰረተባቸው 20 ሰዎች ውስጥ አንዷ ሆና ቃሊቲ እስር ቤት ገባች። ከወራት በፊት ችሎት እንዲቀየርላቸው ያመለከቱ ሲሆን፤ እስካሁን አቤቱታቸው ባለመመለሱ የዐቃቢ ሕግ ምስክሮችን መሰማት አልተጀመረም።
18. ኤዶም ካሳዬ (ጋዜጠኛ) - በሚያዚያ 17/2006 ተይዛ ማዕከላዊ ለሦስት ወራት ከቆየች በኋላ ክስ ተመስርቶባት ቃሊቲ እስር ቤት ገባች። የኅብረተሰቡን ደኅንነት አደጋ ላይ ለመጣል አሲራችኋል፣ አቅዳችኋል ተብለው በነሶሊያና ሽመልስ መዝገብ ከተከሰሱት 3 ጋዜጠኞች አንዷ ስትሆን ለዓመት ከሦስት ወር በእስር ሆና ክሷን ከተከታተለች በኋላ ክሱ ተቋርጦላት በነፃ ወጥታለች።
19. ማሕሌት ፋንታሁን - በሚያዚያ 17/2006 ተይዛ ማዕከላዊ ለሦስት ወራት ከቆየች በኋላ ክስ ተመስርቶባት ቃሊቲ እስር ቤት ገባች። የኅብረተሰቡን ደኅንነት አደጋ ላይ ለመጣል አሲራችኋል፣ አቅዳችኋል ተብለው በነሶሊያና ሽመልስ መዝገብ ከተከሰሱት 6 ጦማሪ አክቲቪስቶች አንዷ ስትሆን ለዓመት ከሦስት ወር በእስር ሆና ክሷን ከተከታተለች በኋላ ክሱ ተቋርጦላት በነፃ ወጥታለች።
20. ርዕዮት ዓለሙ (ጋዜጠኛ እና መምህርት) - በ2003 ሰኔ ወር ላይ ተይዛ ማዕከላዊ ገባች። በነኤልያስ ክፍሌ መዝገብ በሽብር ወንጀል ከተከሰሱት አምስት ሰዎች አንዷ ናት። ከፍተኛ ፍቤት የ14ዓመት ፍርድ ከበየነባት በኋላ ይግባኝ ብላ ክሶች ተሰርዘውላት ቅጣቱ ወደ 5ዓመት ዝቅ አለላት። በደንቡ መሠረት በአመክሮ ጥቅምት ወር 2007 ላይ መለቀቅ ሲገባት፤ በጥፋቷ መፀፀቷን አምና ካልፈረመች አመክሮ አይሰጥሽም ተባለች። የማላምንበት ነገር ላይ አልፈርምም በማለትም ያለአመክሮ ፍርዷን ለመጨረስ ወሰነች። ባልተጠበቀ እና ባልታሰበ ወቅት ከአራት ዓመት እስር በኋላ ሐምሌ 1፣ 2007 ከእስር ተለቀቀች። የመጨረሻዎቹን ሁለት የእስር ዓመታት አምስት የእሷን ሁኔታ የሚከታተሉ እስረኞች ያሉበት ብቻ በቅጣት ቤት ውስጥ ነበር ያሳለፈችው፤ ከእናት እና አባቷ ውጪም በማንም እንዳትጎበኝ ተከልክላ ነበር። በእስር ሆና ‹የኢሕአዴግ ቀይ እሰክብሪቶ› የሚል የቀድሞ ጽሑፎቿ ስብስብ ታትሞላታል፡፡
21. ረዳት ኢንስፔክተር አዜብ ተክላይ - ለኤርትራ የስለላ ቡድን የሃገሪቱን ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል መረጃ አቀብለሻል ተብላ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ማዕከላዊ ገባች። ከአራት ወር በላይ እዛ ከቆየች በኋላ ምንም ማስረጃ ሳይገኝባት በስለላ ወንጀል ክስ ተመሥርቶባት ቃሊቲ እስር ቤት ገባች። ክሷን በእስር ሆና ስትከታተል ቆይታ በዚህ ዓመት መጀመሪያ አካባቢ ጥፋተኛ ተብላ የ7ት ዓመት ፍርድ ተበይኖባታል። ጥፋተኛ መባል አይገባኝም ስትል ጠቅላይ ፍቤት ይግባኟን አቅርባ ተከራክራለች። ለመጋቢት 16/2008 ለብይን ተቀጥራለች።
22. አበበች ጣሙ - የጎንደር ተወላጅ ናት። በጥር ወር 2006 ላይ ተይዛ ማዕከላዊ ገባች። በእነአበበ ካሴ መዝገብ ከተከሰሱት ውስጥ ስትሆን መሳሪያ ደብቀሻል የሚል ክስ ነው የተመሰረተባት። 1 ዓመት ከአምስት ወር በእስር ቆይታ በ2007 ሰኔ ወር ላይ በዋስ ወጥታ ክሷን ስትከታተል ከቆየች በኋላ ጥር ወር 2008 ላይ በነፃ የተሰናበተች።
23. እየሩሳሌም ተስፋው - የሰማያዊ ፓርቲ አባል የነበረች። በየካቲት ወር 2007 በሰላማዊ ትግል ተስፋ ቆርጣ ሰማያዊ ፓርቲን በመልቀቅ በኤርትራ በኩል ግንቦት 7 ልትቀላቀል ስትል ማይ ካድራ የተባለ ቦታ ላይ ተይዛ ወደ ማዕከላዊ የገባች። ከዛም የሽብርተኛ ድርጅት አባል መሆን የሚል ክስ ተመስርቶባት በቃሊቲ የምትገኝ። እሷ ያለችበት መዝገብ (እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ) መከላከያ ምስክሮችን ለማሰማት ለመጋቢት 22/2008 ተቀጥረዋል።
24. እየሩስ አያሌው - የ2007ን ሃገራዊ ምርጫ ተከትሎ "ትግሬ አይገዛንም" ብለሻል የሚል ክስ ተመስርቶባት ዓመት ከአራት ወር ተፈርዶባት ግንቦት ወር 2007 ላይ ቃሊቲ ገባች። ከፍተኛ የአይምሮ ጭንቀት ሕመም የነበረባት ሲሆን ምግብም አትበላም ነበር። በየካቲት ወር መጀመሪያ 2008 ላይ በእስር ላይ እያለች እራሷን አጥፍታ ሕይወቷ ያለፈ።
25. ቀለብ ስዩም - ከአራት ወር በላይ ይሆናታል ከታሰረች። ከጎንደር ነው የመጣችው። በሽብር ወንጀል ተከሳ ጉዳይዋን በቃሊቲ እስር ቤት ሆና እየተከታተለች የምትገኝ።
26 ሃዊ ጎንፋ - በሽብር ወንጀል ተከሳ ሦስት ያልተገቡ ዓመታትን በእስር አሳልፋለች። ለሦስት ዓመታት ክሷን በእስር ሆና ስትከታተል ከቆየች በኋላ በነፃ ተሰናብታለች። በማዕከላዊ እና ቃሊቲ የታዘበችውን የሚተርክ RIRRIITTAA የተሰኘ መጽሐፍ እና ሌሎች ሁለት ተጨማሪ መጽሐፍቶችን (HIREE GALGALAA እና CANCALA QABSOO) አበርክታለች።
27. አየለች አበበ - ካጋሞ ጎፋ ዞን ተይዘው አራት ወር ማዕከላዊ ከቆዩ በኋላ የሽብርተኛ ቡድን አባል ናችሁ በመባል በሚያዚያ 27 ቀን 2008 ክስ ከተመሠረተባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት (እነ ሉሉ መሰለ) ውስጥ ናት።
የISIS ቡድን በሊቢያ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን ግድያ በመቃወም በሚያዝያ ወር 2006 በተጠራው ሰልፍ ጋር በተያያዘ “ስብሰባ በማወክ”፣ “ሁከት በመፍጠር”፣ እና በመሳሰሉ ክሶች የተመሠረተባቸው በርካቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ ጭራሽ ሰልፉ ላይ ያልነበሩ (እቤታቸው ወይም ሥራ ገበታቸው ላይ የነበሩ) ይገኙበታል፡፡ በነጻ የተሰናበቱት እንዲሁም ስምንት ወር ፍርድ ተወስኖባቸው የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ቅጣታቸውን ጨርሰው ከእስር ወጥተዋል፡፡ ቃሊቲ ገብተው የነበሩት የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. ብሌን መስፍን - (የሰማያዊ ፓርቲ አባል)
2. ቤተልሔም አካለወልድ
3. ወይንሸት ሞላ (የሰማያዊ ፓርቲ አባል)
4. ዝናሽ አንከላ
5. ዝናሽ ምትኩ
6. ማሕሌት ኤርሳዶ
7. እኑኪ ኃይሉ
8. ቤዛዊት ግርማ (ጋዜጠኛ)
9. ራሕሙ ጀማል
10. ፍቅር
11. መስከረም ወንድማገኝ (አርቲስት)
12. ዮዲት ኃይለማርያም
13. ሔለን ነዋይ
14. ሜሮን አስማማው
15. ንግሥት ወንዲፍራው (የሰማያዊ ፓርቲ አባል)
----
*በመረጃ እጦት የተገደፉ ጥቃቅን ስህተቶች እና ያላካተትኳቸው እስረኞች ሊኖሩ ይችላሉ።
Source: Zone9

Monday, March 7, 2016

የኢትዮ-ኤርትራ ዉዝግብ

የኢትዮጵያ መንግሥት ሰሞኑን ኤርትራን ደጋግሞ ማዉገዝ-ማስጠንቀቁም ምናልባት የማይመቸዉን የአስመራና የሐያላኑን መቀራረብ የትኩረት አቅጣጫን ከኦሮሚያዉ ዓይነት ግጭትና ሁከት ለማስቀየስ አልሞ ሊሆን ይችላል።ባይሆን እንኳ ጋዜጠኛ ሮንግ እንዳለችዉ የዉግዘት፤ ዛቻዉ መደጋገም ኢትዮጵያ ምናልባት ወታደራዊ ጡንቻዋን ልትሞክር ትችላለች ማሰኘቱ አልቀረም

አውዲዮውን ያዳምጡ።11:23

የኢትዮ-ኤርትራ ዉዝግብ

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠንካራ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ «ደደብ»-(stupid) ያሉት የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ከቆመ እነሆ ዘንድሮ አስራ-ስድተኛ ዓመቱን አገባደደ።ይሁንና እንደ ጥብቅ ወዳጅ የጋራ ጠላታቸዉን በአንድነት ወግተዉ አስመራ እና አዲስ አበባ ላይ አዳዲስ መንግሥታት ባቆሙ በሰባተኛ ዓመታቸዉ ዉጊያ የገጠሙት ሐይላት ሙሉ ጦርነት አቆሙ እንጂ ሠላም አስፍነዉ አያዉቁም።ጦርነት የለም።ቁርቁስ፤ ሽኩቻ፤ዛቻ፤ ፉከራ-መካከሱ ግን አልተቋረጠም።እና ሠላምም የለም።ሰሞኑን ደግሞ መወጋገዝ፤ መካሰሱ ይደጋገም ይዟል።ሰበብ ምክንያት አስተጋብኦቱ የዝግጅታችን ትኩረት ነዉ።።
የሶማሊያ የርስ በርስ ጦርነት ሲግም የኢትዮጵያ መንግሥት በቀጥታ፤ የኤርትራ በተዘዋዋሪ ጦርነቱን ዘዋሪዎች ናቸዉ።ሠሜንና ደቡብ ሱዳን ሲጋጩ-ሁለቱ ሐገራት በተቃራኒ ጎራ ለመቆም አላመነቱም።ደቡብ ሱዳኖች እርስ በርስ ሲዋጉ፤ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት የሁለቱ መንግሥታት እጅ በቀጥታም፤ በተዘዋዋሪም አለበት።አንዳቸዉ የሌላቸዉን አማፂ ቡድን ማስታጠቅ፤ ማስጠጋት ማደራጀታቸዉም ሚስጥር ሆኖ አያዉቅም።
ሥለ ሁለቱ ሐገራት ግጭትና ግንኙነት ሁለት መፅሐፍት ያሳተመችዉ ጋዜጠኛ ሚካኤላ ሮንግ እንደምትለዉ አንዳቸዉ የሌላዉን ሥርዓት ለማዳከም የማያደርጉት የለም።«ያሁኑን ወቀሳ ዝርዝር ጉዳይ ትተን ሁለቱ ወገኖች ላለፉት አስራ-ስድስት ዓመታት አንዳቸዉ የሌላቸዉን አማፂ ቡድናትን እና ንቅናቄዎችን ለመርዳት አላመነቱም።አማፂያኑ የሚንቀሳቀሱበት አስተማማኝ የጦር ሠፈር፤ ዋና ፅሕፈት ቤት፤ ገንዘብ ይሰጣሉ።ይሕን የሚያደርጉት አንዳቸዉ ከድንበር ማዶ ያለዉን የሌላቸዉን ሥርዓት ለማዳከም ነዉ።»
ኤርትራዉያን ወጣቶች በብዛት ለመሰደዳቸዉ አስመራ ሲአይ ኤን አስቀድማ አዲስ አበባን አስከትላ ትወቅሳለች።ኤርትራ በ2009 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ነዉ) ዓለም አቀፍ ማዕቀብ ሲጣልባት-ባንደኛ ደረጃ ተወቃሽዋ ኢትዮጵያ ነበረች።በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራ አምባሳደር ግርማ አስምሮም በቀደም ደገሙትም።
የኢትዮ-ኤርትራ እስካሁን ያልተፈታዉ «ችግር» ገለልተኛ የተባለዉ ዓለም አቀፍ ኮሚሽን በወሰነዉ መሠረት ኢትዮጵያ ለኤርትራ የሚገባትን መሬት አለማስረከቧ ነዉ።ይሁንና ሁለቱ መንግሥታት ለመጣላት ሌላም ምክንያት አላጡም።
ኢትዮጵያን ከኤርትራ ጋር በሚያዋስነዉ ድንበር ሐገር ጎብኚዎች ወይም ያገሬዉ ነዋሪዎች ከታገቱ ፤ከተገደሉ ወይም ከተጉላሉ አዲስ አበባ-አስመራን ለማዉገዝ፤ ለመዛት ማስፈራራት አትዘገየም።ኢትዮጵያ ዉስጥ የቦምብ አደጋ ከደረሰ ወይም ሊደርስ ነበር ከተባለ የኢትዮጵያ መንግሥት ማንን እንደሚወቅስ ወይም እንደሚያወግዝ ለማወቅ የመንግስት መግለጫ እስከሚወጣ መጠበቅ አያስፈልግም።
በቅርቡ በኦሮሚያ አካባቢ የተነሳዉ ተቃዉሞም የሁለቱን መንግሥታት የአስራ-ስድስት ዓመታት እንኪያ ሠላንቲያ ለማጦዝ ተጨማሪ ምክንያት ነዉ-የሆነዉ።
የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትር አቶ ጌታቸዉ ረዳ።የኤርትራ መንግሥትም ከኢትዮጵያ የተሰነዘረበትን ዉግዘት እንደተለመደዉ አዉግዟል።የሐገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣዉ መግለጫ በኦሮሚያ የተቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የሚከተለዉ የ«ከፋፍለሕ ግዛ» ሥልት ዉጤት ነዉ።
«ዉሸት ቢደጋገም እዉነት አይሆንም» በሚል ርዕሥ የተሠራጨዉ መግለጫ እንደሚለዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ኤርትራን የሚያወግዘዉ በሐገሩ ዉስጥ ያለዉን ሕዝባዊ ተቃዉሞ ዉጪያዊ መልክና ባሕሪ ለመስጠት ነዉ።ማስታወቂያ ሚንስትር የማነ-ግብረዓብም ወቀሳዉን መሠረተ ቢስ ይሉታል።
«ሥለ ጉዳዩ ይፋ መግለጫ ሰጥተናል።ይሕ ወቀሳ በመረጃ ያልተደረገፈና መሠረተ-ቢስ ነዉ።እንደሚመስለኝ ሥርዓቱ የሐገር ዉስጥ ችግሩን ዉጪያዊu ለማድረግ እየሞከረ ነዉ።»የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለሥ ዜናዊ በ2005 ማብቂያ ቦንን በጎበኙበት ወቅት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸዉ ጥያቄ-ሲመልሱ ሁለት ዓመት ያዋጋዉን ጦርነት አላስፈላጊ እና ደደብ በማለት ኮንነዉት ነበር።
ጦርነቱ ራሱ ወይም የጦርነቱ አዋጊዎች «ደደብ» ከነበሩ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች ሕይወታቸዉን የገበሩበት ምክንያት የሁለቱም ሐገራት ሕዝብ በግልፅ ሊያዉቀዉ፤ አላስፈላጊ ጦርነት አቀጣጣዮችም ሊጠየቁ በተገባ ነበር።
ሁለቱ መንግሥታት ለጦርነቱ መጫር አንዳቸዉ ሌላቸዉን ከመወንጀል ባለፍ የየሕዝባቸዉን ይቅርታ ለማግኘትም ሆነ ሐላፊነቱን ለመዉሰድ እስካሁን አልደፈሩም።በጦርነቱ የተገደለና የቆሠለዉ ሰዉ ትክክለኛ ቁጥር፤ የተፈናቀለዉ ሕዝብ ብዛት፤ የጠፋዉ ሐብት ንብረት ትክክለኛ መጠን ጦርነቱ ቆመ በተባለ ባስራ-ስድስተኛ ዓመቱ ዘንድሮም ለሁለቱም ሐገራት ሕዝብ ሚስጥር ነዉ።
ጦርነቱ ከድንበር ዉዝግብ ይልቅ ምጣኔ ሐብታዊ፤ ከምጣኔ ሐብታዊነቱ በላይ አካባቢዉን በበላይነት የመቆጣጠር ፉክክር፤ ከዚም ይበልጥ የሁለቱ ገዢ ፓርቲዎች ወይም መሪዎች ጠብ የወለደዉ እንደሆነ በሠፊዉ ይታመናል።በተለይ ምዕራባዉያን የፖለቲካ ተንታኞች፤ ጦርነቱ በይፋ መቆሙ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ የቀጠለዉ ግጭት፤ ቁርቁስ፤ ዛቻ የሚቆመዉ ከሁለቱ ገዢዎች አንዳቸዉ ወይም ሁለቱ ከሥልጣን ሲለዩ ወይም ሲወገዱ ነዉ የሚል እምነት ነበራቸዉ።2012 አቶ መለስ ሞቱ።የተለወጠ ነገር የለም።
«ጠቅላይ ሚንስትር መለሥ ዜናዊ ከሞቱ በኋላ ትልቅ ተስፋ ነበር።ከሁለቱ ዋና ዋና ተዋኞች አንዱ ከትዕይንቱ ሲለዩ የሁለቱን ሐገራት ግንኙነት እንደገና ይጤናል የሚል ግምት ነበር።ምክንያቱም የጠንካራዉ ፖለቲከኛ ሞት ብዙ ቢያሳዝንም በሁለቱ መሪዎች በመለስና በኢሳያስ መካከል ከነሱም በላይ በሁለቱ (የቀድሞ) አማፂ ቡድናት፤ በTPLF እና በEPLF መካከል ቅራኔ ሥለነበር፤ ቢያንስ አንዱ ተዋኝ ከመድረኩ ሲለቅ አዲስ ሁኔታ ይፈጠራል የሚል ግምት ነበር።ይሕ ግን አልሆነም።እንዲያዉም አዲሱ የኢትዮጵያ መንግሥት አስመራ ላይ ይበልጥ ጠንካራ ነዉ-የሆነዉ።»
ቁርቁስ፤ ግጭት መወጋገዙ ከቀድሞዉ ጠቅላይ ሚንስትር ሞት በኋላም መቀጠሉ የሑለቱን ሐገራት ሕዝቦች በየጊዜዉ እንዳሸማቀቀ ነዉ። ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በኋላ ኤርትራ በተለይ የሶማሊያዉን አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አል-ሸባብን ትረዳለች፤ ጅቡቲን ወርራለች የሚል ወቀሳ ከተሰነዘረባት በኋላ ከአብዛኛዉ ዓለም ተገልላ ነበር።በማዕቀብ ተቀጥታለችም።
የኤርትራ ወጣቶች በብዛት ወደ አዉሮጳ መግባታቸዉ እና ሳዑዲ አረቢያ መራሹ የፋርስ ባሕረ-ሠላጤ አካባቢ የአረብ ሐገራት ጦር በየመኑ የርስ በርስ ጦርነት መነከሩ፤ ኤርትራን አርቋት የነበረዉ ዓለም ዳግም እንዲቀርባት አስገድዶታል።የኤርትራ መንግስት ለሚሰደዱ ወጣቶቹ «የሥራ ዕድል» እንዲፈጥር በሚል ሰበብ የአዉሮጳ ሕብረት «ጨቋኝ» ለሚለዉ የኤርትራ መንግስት የ200 ሚሊዮን ዩሮ ርዳታ ለመስጠት ተፈራርሟል።
የየመንን አማፂ ቡድን የሚወጉት ሳዑዲ አረቢያና ተከታዮችዋ ደግሞ ኤርትራን የስንቅና ትጥቅ ማደራጃና ማቀበያ ለማድረግ አቅደዋል።ኤርትራ ከየመን አርባ ኪሎ ሜትር ብትርቅ ነዉ።ኤርትራም አጋጣሚዉን መጠቀም የፈለገች ይመስላል።ከእስር ቤቶቿ ቢያንስ አንዱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰራተኞች እንዲጎበኙ ፈቅዳለች።የተጣለባት ማዕቀብ እንዲነሳ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታዉ ምክር ቤትን ጠይቃለችም።
የኤርትራ መንግስት በልማዱ ዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ከሚባለዉ ሐያል-ሐብታም ሐይል ጋር መቀራረቡ፤ ምዕራባዉያን ተንታኞች እንደሚገምቱት ለአዲስ አበባ መሪዎች፤ በአዲስ አበቦች ቋንቋ «የሚመች» አይደለም።
የኢትዮጵያ መንግሥት ሰሞኑን ኤርትራን ደጋግሞ ማዉገዝ-ማስጠንቀቁም ምናልባት የማይመቸዉን የአስመራና የሐያላኑን መቀራረብ ለማደናቀፍ ወይም የትኩረት አቅጣጫን ከኦሮሚያዉ ዓይነት ግጭትና ሁከት ለማስቀየስ አልሞ ሊሆን ይችላል።ባይሆን እንኳ ጋዜጠኛ ሮንግ እንዳለችዉ የዉግዘት፤ ዛቻዉ መደጋገም ኢትዮጵያ ምናልባት ወታደራዊ ጡንቻዋን ልትሞክር ትችላለች ማሰኘቱ አልቀረም።ለግማሽ ምዕተ-ዓመት ያክል ከጦርነት-ግጭት እልቂት-ስደት ላልተላቀቀዉ ለሁለቱ ሐገራት ሕዝብ ሌላ ስጋት።እስከመቼ አይታወቅም።
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ
Source: DW

Migrant stowaway survivives flight from Ethiopia


Police evacuate passengers from the Ethiopian Airlines flight en route to Rome, which was hijacked and forced to land in Geneva. (Richard Juilliart, AFP)

The man, 27, said he was an Ethiopian national and has submitted an asylum application in Sweden, police spokesperson Lars Bystrom told dpa. Police and paramedics were alerted, but a check-up showed he did not require medical treatment.Stockholm - A stowaway refugee found on a plane from Ethiopia to the Swedish capital Stockholm survived the 10-hour journey via Vienna in a pressurized container in the cargo hold, police said on Monday.
He was discovered at Stockholm Arlanda Airport by baggage handlers unloading an Ethiopian Airlines flight that arrived early Monday, said Johan Live of Swedaviam, the company that operates the airport.
Police have launched an investigation into possible human trafficking.
Police evacuate passengers from the Ethiopian Airlines flight en route to Rome, which was hijacked and forced to land in Geneva. (Richard Juilliart, AFP)

In August, another stowaway from Ethiopia survived a similar journey in the cargo hold of another flight to Stockholm. He also applied for asylum and said via an interpreter that he had hidden in the cargo hold at Addis Ababa's Bole Airport.
The previous stowaway was in possession of a badge identifying him as an airport employee, which could explain how he managed to get on board the plane, the Swedish border police said at the time.
Source: news24

ETHIOPIA DETAINS JOURNALISTS COVERING OROMO PROTESTS

A woman and her child in Oromia awaits medical attention.

A woman and her child await medical attention in Oromia, Ethiopia, January 31. A severe drought and anti-government protests in Oromia have increased restrictions on press freedom in Ethiopia, according to a journalists' association.EDMUND BLAIR/REUTERS
Press freedom in Ethiopia is dwindling in light of recent anti-government protests and the severe drought in the Horn of Africa state, according to a journalists’ association.
Two journalists and a translator were arbitrarily detained for 24 hours on Thursday when reporting on the protests in Oromia, according to a statement issued by the Foreign Correspondents’ Association of East Africa (FCAEA) on Monday. Bloomberg correspondent William Davison and freelance journalist Jacey Fortin, along with their translator, were not given any reason for their detention. Their phones and identification cards were taken during the arrest.
Protests among the Oromos, who constitute Ethiopia’s largest ethnic group, have been ongoing since November 2015 and were originally directed against plans by the federal government to expand the capital Addis Ababa. At least 140 protesters were killed between November 2015 and January, according to Human Rights Watch (HRW). The Addis expansion plans were dropped in January but the protests—which have morphed into a general expression of dissatisfaction with the government among Oromos—have continued and demonstrators are stillbeing subjected to “lethal force,” HRW said on February 22. The Ethiopian government has said that “destructive forces” —including some from neighboring Eritrea—have hijacked the protests and would be dealt with decisively.
Davison told Newsweek that the risks of reporting on certain topics in Ethiopia is too high because of the threat of detainment. “It was a shock to be held overnight in a prison cell and not be given any explanation of what we were being held for,” says Davison. The “very heavy and militarized response” to the Oromo protests “raises the chance that reporters are going to be obstructed from doing their work,” he says.
The FCAEA said that the detentions marked “a worrying escalation” in Ethiopia, which already has a poor record for allowing journalists to operate freely. Ethiopia was ranked 142nd out of 180 countries in terms of press freedom in 2015 by non-profit organization Reporters Without Borders, which recorded six newspapers closing and more than 30 cases of journalists fleeing abroad in 2014. “Ethiopia is well-known for its tough stance on journalists but this is a worrying spike of arbitrary detention of media workers at a time of increased interest in Ethiopia,” says Ilya Gridneff, chairman of FCAEA. “Journalism is not a crime and those in Ethiopia should not be treated as criminals.”
Newsweek contacted the Ethiopian Embassy in London but was yet to receive a reply at the time of publication.
Coupled with the Oromo protests, Ethiopia is currently experiencing its worst drought in around 50 years, partly due to the El Nino weather pattern. Up to 15 million people in the country require emergency humanitarian food assistance and the United Nations is appealing for $50 million to help the government cope with the crisis.
Source: Europe News Week

Tuesday, March 1, 2016

Ethiopia’s opposition leaders implicated in Oromia violence


JPEG - 24.6 kb

By Tesfa-Alem Tekle
February(ADDIS ABABA) – An Ethiopian minister has accused leaders of a popular opposition party of having allegedly played a role in instigating the recent unrest that rocked the Horn of African nation.
A group of protestors carry placards in support of Oromia region (Opride.com)
Ethiopia’s communication minister, Getachew Reda claimed that leaders of the Oromo Federal Congress (OFC) party had an active role in instigating the deadly violence that erupted in larger parts of the Oromia region.
He said some of the opposition parties in Ethiopia, particularly the OFC, are very opportunistic and often take advantage of situations.
He claimed the OFC was largely linked to people who were long working with groups that had for a while been designated as terrorist entities.
Getachew said there was a tendency by some in the leadership of the opposition party to use both legal and illegal protest means in Oromia region.
“Senior members of the Oromo Federal Congress party were involved throughout the protests in western Showa and South western showa,” he said.
The minister accused the OFC of backing such unrest to get out of control and there by trying to take advantage of it to accomplish a hidden agenda.
According to the minister, some legal opposition parties particularly the OFC is using its legality as a pretext to accomplish missions of other exiled outlawed groups.
“There is a growing tendency within the OFC itself to rather focus on the violence aspect of their moves than to stick to a legal and peaceful means,” he said.
The government has pledged to hunt down and bring to justice all those perpetrators behind the violence.
Dozens of people, including members of security force were killed and hundreds of others injured during the recent violence that began in protest to government plans to expand boundary of the capital, Addis Ababa, to parts of the Oromia region.
University students first began the protest in November, but later on hundreds of farmers who fear could face eviction from their ancestral lands as a result of the master plan joined the protest movement as it continued.
“An organized and armed terrorist force aiming to create havoc and chaos has begun murdering model farmers, public leaders and other ethnic groups residing in the region”, said the minister on 16 December 2015.
Ethiopia’s Prime Minister, Hailemariam Desalegn earlier said his government “will take merciless legitimate action against any force bent on destabilizing the area”.
Last week Human Rights watch accused Ethiopian security forces of violently suppressing the “largely peaceful protests” in the Oromia region.
The Ethiopian Human Rights commission is undergoing investigation over the recent violence and the Ethiopian government couldn’t, at this point, determine death figures.
Human Rights Watch said it has not been able to verify the total numbers of people killed and arrested “given restrictions on access and independent reporting in Ethiopia”. Almost daily accounts of killings and arbitrary arrests have been reported to Human Rights Watch since this year began. Activists claim over 200 people have been killed since 12 November, 2015 based on materials gathered on social media photos and web posts.



Source: Sudan Tribune