Wednesday, March 4, 2015

የነዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ

አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ ዘላለም ወርቃገኘሁ፣ ሀብታሙ አያሌው እና አብርሃም ሰለሞን
አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ ዘላለም ወርቃገኘሁ፣ ሀብታሙ አያሌው እና አብርሃም ሰለሞን

“ሸላሚም እኛ፣ ከሳሽም እኛ!“

አብርሃም ሰለሞን የ25 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ያሳደገው ኢሕአዴግ ራሱ(ወይም ዘመነ መንግስቱ) ነው፡፡ በቤተልሄም የመጀመሪያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ IT መምህር ነበር፡፡ በትምህርት ቤቱ መልካምዝና ነበረው፡፡ በ2006 በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገ ውድድር ላይ ይዞ በቀረበው የመምህራን ዳታ ቤዝ እና የመማሪያ ማኑዋል ዝግጅትንአሸናፊ መሆን ከቻሉ ሦስት ወጣቶች አንዱ ለመሆን በቅቷል፡፡ ጥቅምት 16/2007 - በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሸላሚነት ሲካሄድ በነበረውየሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች የሽልማት ሥነ ስርዓት ላይ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን IT ለማስተማር የሚረዳ የዴስክቶፕሶፍትዌር እና የሞባይል አፕልኬሽን በማዘጋጀት የሜዳልያ ተሸላሚ ተብሎ ተመዝግቧል፡፡ ይሁን እንጂ የዘንድሮውን የስራውን ውጤት በአካልተገኝቶ ሰርተፍኬቱንም፣ ሜዳልያውንም መቀበል አልቻለም፤ በእሱ ፈንታ እናቱ በውክልና ተቀብለውታል፡፡ ምክንያቱም እሱ በሽብር ወንጀልተጠርጥሮ ቂሊንጦ ማቆያ ቤት ይገኛል፡፡
አብርሃምን ስለ አገሪቱ የወደፊት ተስፋ ሰጪ ስራ ሰርተሃል ብሎ በቀኝእጁ የጨበጠው መንግስት፣ በግራ እጁ ደግሞ ለአገሪቱ የወደፊት ተስፋ አደገኛ አሸባሪ ነህ ይለዋል፡፡

“የማይተዋወቁ ግብረ - አበሮች”

በሽብር የሚከሰሱ ሰዎች ከማያውቋቸው ሰዎች ጋር በአንድ መዝገብ (እንደግብረ አበር) የሚታሰሩበት አሰራር የተለመደ ሆኗል፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ የነዘላለም ወርቅአገኘሁ መዝገብ በመባል የሚታወቀው (መዝገብቁጥር 166/07) አንዱ ነው፡፡ በዚህ መዝገብ አራት የተለያዩ ፓርቲ አባላት እና ሌሎች 6 ተጠርጣሪዎች ተከስሰዋል፡፡ የመጀመሪያዎቹ5 ተከሳሾች (ዘላለም ወርቅአገኘሁ፣ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ አብርሃ ደስታ እና የሺዋስ አሰፋ) በፀረ- ሽብርተኝነት አዋጁአንቀፅ  4 ሲከሰሱ፣ ቀሪዎቹ አምስቱ (ዮናታን ወልዴ፣ አብርሃም ሰለሞን፣ሰለሞን ግርማ፣ ባህሩ ዳኑ፣ እና ተስፋዬ ተፈራ) በአንቀፅ 7/1 እና 9ኛ ተከሳሽ (ባህሩ ዳጉ) በሌላ ክስ በወንጀለኛ መቅጫው288/1 መሰረት ከመከላከያ ሰራዊቱ በመኮብለል ተከስሰዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ክሳቸው በአንድ መዝገብ ታጭቀው ቢመጡም ባብዛኛው እርስበርስ አይተዋወቁም፤ በጋራ የሰሩት ስራም የለም፡፡
በፌስቡክ እንቅስቃሴው በስፋት የሚታወቀው እና የአረና ትግራይ ፓርቲአመራር አባል የነበረው አብርሃ ደስታ ለምሳሌ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል ከሆነው ሀብታሙ አያሌው በቀር የሌሎቹን ስም እንኳንአብረው ከመከሰሳቸው በፊት አለመስማቱን ይናገራል፡፡ ተሸላሚው አብረሃም ሰለሞንም ከተከሳሾች የሚያውቀው ዘላለምን ብቻ ነው፡፡‹‹እሱንም›› ይላል አብርሃም ‹‹በ2006 አንድም ቀን አግኝቼው አላውቅም››፡፡ ከተከሳሾች መካከል ብዙ ሰው ያውቃል የተባለለት1ኛው ተከሳሽ ዘላለም እንኳን የሚያውቀው ሦስቱን ብቻ ነው - ዮናታን፣ አብርሃምን እና ባሕሩን ብቻ፡፡

“በስልክ የማውራት አሸባሪነት”

በሽብር የተከሰሱ ሰዎች ላይ በተደጋጋሚ እና በተለይ ከሚቀርቡ የማስረጃዓይነቶች አንዱ የስልክ ግንኙነት ነው፡፡ ከላይ በጠቀስነው መዝገብ ውስጥ ብቻ ክስ ሆነው የቀረቡትን የስልክ ግንኙነቶች እንመልከት፡-
* 1ኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ፣ ‹‹በ 2000 ተድላ ደስታ ከተባለየሽብር ድርጅቱ አባልና አመራር ጋር በስልክ እና በፌስቡክ›› በማውራት፤
* 2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው ‹‹ዘመኑ ካሴ ከተባለ የግንቦት ሰባትታጣቂ›› ጋር በጥር 14/2005 በስልክ በማውራት፤
* 3ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ሺበሺ ‹‹የግንቦት ሰባት አመራር ከሆነው ፋሲልየኔ አለም ›› ጋር በየካቲት 29/2003 በስልክ በማውራት፤
* 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታ ‹‹የደ.ም.ሕ.ት. አመራር ከሆነው ጎይቶምበርሄ ›› ጋር ጥር 3/2006 በስልክ በማውራት፤
* 5ኛ ተከሳሽ የሺዋስ አሰፋ ‹‹የግንቦት ሰባት አመራር ከሆነው ፋሲልየኔአለም›› ጋር ጥቅምት 14/2006 በስልክ በማውራት፤
* 10ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ተፈሪ፣ የግንቦት ሰባት ክንፍ ከሆነው የአ.ዴ.ኃ.ንአባል ጋር ሕዳር 2003 በስልክ በማውራት፤
እነዚህ የስልክ ግንኙነቶች ያለሌላ ተጨማሪ ማስረጃ በብቸኝነት የክስመመስረቻ መሆናቸው ደግሞ ክሱን ተአማኒነት ያሳጡታል፡፡ ዜጎች የስልክ ግኑኝነቶችን በሙሉ እንዲፈሩም ያደርጋቸዋል፡፡ በሽብርተኝነትበተጠረጠሩ ድርጅቶች ውስጥ በዐቃቤ ሕጉ ቃል ብቻ አባል ናቸው የተባሉ ሰዎች ስለደወሉለት ብቻ የተደወለለት ሰው ‹‹አሸባሪ›› ተብሎይከሰሳል፡፡ ፈቅዶ ባልተደወለለት ስልክ ወንጀለኛ ነህ የሚባልበት አሰራር ከኢትዮጵያ ውጪ ያለ አይመስልም፡፡ አንዳንዶቹ የስልክጥሪዎች የተደረጉት ‹‹ሽብርተኛ ናቸው›› በተባሉ ድርጅቶች ውስጥ ባሉ እና በሚታወቁ ግለሰቦች ሳይሆን የአቃቤ ህግ ቃል ብቻ ያልሆነውንነው ብሎ ስላቀረበ ነው፡፡ በዚህ መንገድ የተፈረደባቸው ብዙ ናቸው፡፡ ሳይፈረድባቸው ራሳቸውን ለመከላከል ማረሚያ ቤት እንዲቆዩየተደረጉትም የዚያኑ ያክል ናቸው፡፡ በ2000 የፀረ ሽብርተኝነቱ አዋጅ አልወጣም ነበር፤ ሽብርተኛ የተባሉ ድርጅቶችም አልነበሩም፡፡ክሱ ላይ ግን በዚያ ወቅት የተደረገ የስልክ ግንኙነት ተጠቅሷል፡፡
በሁሉም የሽብር ክሶች ውስጥ copy/paste የተደረገች ውንጀላ አለች፤‹‹ራሱን [እከሌ ]ብሎ ከሚጠራው አሸባሪ ቡድን ግንኙነት በመፍጠርና ተልእኮ በመቀበል ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድበማሰብ . . . ‹‹የምትል ነች፡፡ ይህች ቃል ዐቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎች ላይ ምንም ዓይነት ድርጊት ሳይጠቅስ የሚያስቀጣበት ውንጀላ  ነች፡፡ በዚሁ በነዘላለም መዝገብም ላይ በተደጋጋሚ ተጠቅሳለች፡፡ በስልክአንድ ሰው ጋር ያወራሉ ከዚያ ተልእኮ ይቀበላሉ፡፡ ሽብር ማለት በቃ ይኽው ነው፡፡

“ሥልጠናዎች ሁሉ ሽብር ናቸው”

በነዘላለም መዝገብ ከተከሰሱት ውስጥ 6ኛ እና 9ኛ ተከሳሽ(ዮናታንእና ባሕሩ) ክስ ላይ የተጠቀሰ ነገር አለ፡፡ይኸውም ‹‹ በመንግስት ላይ ያሉ ችግሮችን ለሕዝብ በተለያዩ የኢንተርኔትና የማህበራዊድህረ - ገፆች ላይ በመፃፍ ለግል ሚዲያዎች ግብአት የመስጠት ሥራ የሚሰሩ ቡድኖች አሉ፡፡ ለዚሁ ተግባር ተብሎ የወሰዱትን የኢንተርኔትአጠቃቀም፣ ኮሙኒኬሽን ስኪል እና ሊደርሺፕ በመሰልጠን ተጠቅመዋል እናንተስ እንዲህ አይነት ስልጠና አትፈልጉም ወይ?›› በሚል አንደኛተከሳሽ ለሁለቱ ተከሳሾች ቀርበዋል የተባሉት ጥያቄዎች ወንጀል ተብለው ተፅፈዋል፡፡ ‹‹ሠልጥነዋል›› ተብለው በምሳሌው የተጠቀሱት‹‹ቡድኖች›› ዞን ዘጠኞች መሆናቸው በሌላ ማስረጃ ተጠቅሷል፡፡ሥልጠናውን ዐቃቤ ሕግ 9ኛ ተከሳሽ ላይ ሲጠቅሰው መጀመሪያ ‹‹ተመሳሳይሥልጠና ለተመሳሳይ አላማ ›› ይልና ዝቅ ብሎ ‹‹የሽብር ድርጅቱን ተልዕኮ ለመፈፀም እንዲረዳቸው ባዘጋጁት ስልጠና ›› ይላል፡፡የመንግስታችን ችግሮች መፃፍ ፣ ወይም ለመፃፍ መሰልጠን በምን መሥፈርት አሸባሪነት ተባለ?

“አብርሃም ሰለሞንን ማን መለመለው?”

የክስ መዝገቡ መጀመሪያ ላይ ‹‹[አብርሃም ሰለሞን] በ1ኛ ተከሳሽ [ዘላለም] አማካኝነት ለሽብር ድርጅቱ በአባልነት ተመልምሎ . .. ›› ይላል፡፡ አንድ አንቀፅ ዝቅ ብሎ ደግሞ ‹‹[አብርሃምን] በአባልነት የመለመለው አንደኛ የአቃቤ ሕግ ምስክር [እዮብ] አማካኝነት. . . ›› ይላል፡፡ አብርሃምን የመለመለው ዘላለም ወይስ እዮብ? (ብቸኛው የዐቃቤ ሕግ ምስክር) መልምሏል የተባለው አብርሃምንብቻ አይደለም፡፡ 8ተኛ ተከሳሽ ሰለሞን ግርማንም ጭምር እንጂ፡፡ እዮብ ሰለሞንን ሲመለምል ተናግሯል የተባለው ይህንን ነው፤
‹‹ኤርትራ ሀገር ግንቦት ሰባት የተባለ ጥሩ ድርጅት አለ፡፡ ወታደራዊእና ፖለቲካዊ ሥልጠና ሠልጥነህ ከድርጅቱ ጋር ከተቀላቀልክ በኋላ ግንቦት ሰባት የሚሰጥህን ተልዕኮ ተቀብለህ ከኢትዮጵያ መንግስትጋር እንዋጋለን፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ሕዝቡን በኃይል እየገዛ ነው ስለዚህ ታግለን መጣል አለብን፡፡ ››
የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ከተጠርጣሪዎች ጋር ታስረው ቆይተው ኋላ ላይምስክር ለመሆን ሲስማሙ መለቀቃቸው የተለመደ ነው፡፡ የፀረ ሽብር ሕጉ ሽብርን ለማጋለጥ ለተባበረ ርሕራሔው ይኼን ይመስላል፡፡ ነገርግን ክፍተት አለው፡፡ ተጠርጣሪዎች በአባሪዎቻቸው ወይም ሌሎች ላይ መስክረው መፈታት እንደሚችሉ ቃል ሲገባላቸው በሐሰትም ቢሆንለማድረግ የሚስማሙበት ዕድል አለ፡፡ በዚህ መንገድ መልማዩ ምስክር ሆኖ የሚቀርብበት ተመልማዩ ላይ ይሆናል፡፡
በዚህ ዓይነት መንግስት ያልወደደውን ፖለቲከኛ (ዜጋ) ስልክ ሲደወልደዋዩ አሸባሪ ነው በማለት፣ ወይም የራሱን ሰው ልኮ በማባበል ለ‹‹ሽብር›› መልምሎ ሲያበቃ መልማዩንምስክር ተመልማዩን ተከሳሽ ለማድረግ ወይም ደግሞ በስጋት ሰብስቦ ካሰራቸው ሰዎች መሃከል ለነፍሳቸው ግድ የሌላቸው የሃሰት መስካሪዎችንእያሰለጠነ እየፈረደ ሊኖር ይሆን?!   

Tuesday, March 3, 2015

ለኢትዮጵያ መብትን፣ ክብርን እና ነጻነትን የሚያጎናጽፍ ሰነድ?

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የእንግሊዝ ህዝብ መሰረታዊ ህገ መንግስት 800ኛ ዓመት በዓል በማክበር ላይ እገኛለሁ!
እንዴት!?
አንዴ በጅ በሉኝ! ጥያቄአችሁን  ተገንዝቤዋለሁ!
በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ ሀገር የሚኖር አንድ በአፍሪካ ያውም በኢትዮጵያ የተወለደ ሰው በመካከለኛው ዘመን ከ800 ዓመታት በፊት በእንግሊዝ ሀገር ያመፁ ባለጉልት ባላባቶችና  በነጉሳቸው መካከል በተደረገው የስልጣንና የግል ጥቅም ትግልና  ስምምነት ለምንድነው የሚያከብረው? ስለነሱ መብትና ነፃነት ምን ግድ አገባው? ብላቸሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ።
የፊውዳል ወይም ደግሞ የንጉሳውያንን ስርዓት በፍጹም አልወድም፡፡ ተወልጀ ያደግሁት በፊውዳሏ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ የፊውዳሉን ስርዓት አስከፊነት፣ ስብዕና የለሽነት እና የበሰበሰ መሆኑን በሚገባ አይቸዋለሁ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት የመንግስት ዓይነት ንጉሳዊ የመንግስት ስርዓት ነበር፡፡
የደርግ ወታደራዊ የሆነው የህብረተሰባዊ/socialist ስርዓት ማጭድ ፈላጭ ቆራጭ የነበረውን የንጉሳዊ ስርዓት ከስሩ ቆርጦ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ገነደሰው፡፡ ለእኔ የመሬት ከበርቴው/ፊውዳሊዝም እና የንጉሳውያን/ሞናርኪ ስርዓቶች ለታሪክ ጥናት ካልሆነ ምንም ፋይዳ የላቸዉም፡፡ የመሬት ከበርቴው ስርዓት ለካፒታሊዝም ስርዓት መደላድል ነው የሚለውን የካርል ማርክስን ትንተና ማንበቤን አስታውሳለሁ፡፡ እ.ኤ.አ በ1974 በስሜት የሚነዱ እና ምንም ዓይነት እርባና ያለው ስራ የማይሰሩ ባለዝቅተኛ ማዕረግ የነበራቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች በወታደራዊ ኃይል ክንፍ ስር ሆኖ ሀገሪቱ ካለችበት የመሬት ከበርቴ ስርዓት በቀጥታ ወደ ህብረተሰባዊነት ስርዓት መሸጋገር ትችላለች ብለው አስበው ነበር፡፡ በእርግጠኝነት ለመናገር የእንግሊዞች የመብት፣ ክብር እና ነጻነትን/Magna Carta ህገ መንግስት በዓል የማከብረው ንጉስ ጆን የፈላስፋ ንጉሥ ስለነበሩ አይደለም፡፡ ንጉስ ጆን መጥፎ አርዓያነት ያለው ስራ የሚሰሩ፣ ክብር የማይሰጣቸው እና ለመርህ የማይገዙ ሰው ነበሩ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ሰው እምነት የማይጥልባቸው ከሀዲ፣ እምነተቢስ፣ ገብጋባ እና ጨካኝ ሰው ነበሩ፡፡ ጆን ሰውን ሲገድሉ እንደ እኛዎቹ ዓይን አውጣ ፈጣጣዎች ለይስሙላም እንኳ ቢሆን ማዘናቸው ቀርቶ መሳቅ የሚቀናቸው ሰይጣናዊ ባህሪ የተጠናወታቸው ንጉስ ነበሩ፡፡ ሰዎች እንዲህ ብለው ነበር፣ “በእርኩሱ ንጉስ ጆን መኖር ገሀነም እራሷ ትጸየፋለች፡፡“ ጆን በቀልተኛ እና አምባገነናዊ ንጉስ ነበሩ፡፡ የእራሳቸውን ሰዎች በእራሳቸው ፈቃድ በቁጥጥር ስር ያውላሉ፣ ወደ እስር ቤት ያግዛሉ፣ ያስራሉ፡፡ የማይሞላ የገንዘብ ካዝናቸውን ለመሙላት በህዝቦች ላይ አስከፊ የሆነ ግብር በመጣል ገንዘብ ይዘርፋሉ፡፡ የስግብግብነት እና የገንዘብ ጥማታቸውን በማርካት እራሳቸውን የበለጠ በሀብት እንዲበለጽጉ ጦርነት ሁሉያደርጉ ነበር። የውትድርና አገልግሎት ላለመስጠት የመሬት ከበርቴዎች የሚሰጧቸው ገንዘብ እና ሰዎችን በገንዘብ በመቅጣት የሚዘርፉት ገንዘብ ዋና ዋና የገንዘብ ማጋበሻ ምንጮቻቸው ነበሩ፡፡
ጆን የእራሳቸውን ሰዎች መሬቶች፣ ፈረሶች፣ ጋሪዎች፣ የበቆሎ ሰብል እና እንጨቶቻቸውን ሳይቀር ከህግ አግባብ ውጭ በመቀማት የሚዘርፉ ገብጋባ ንጉስ ነበሩ፡፡ ከዚህ አንጻር የንጉሳውያንን ደን ዋና የገቢ ምንጫቸው አደረጉ፣ እናም በእርሳቸው የአገዛዝ ዘመን ዋና የሙስና ምሽጋቸው አደረጉት፡፡ በትክክል ለመናገር ጆን ፍትህን ሸጠዋታል፡፡ የንጉሳውያን/ት የፍትህ ስርዓት በጠቅላላ በሚገዙት የወሰን ክልል ውስጥ ሁሉ ሙሉ ቁጥጥር ያለው ስለሆነ ለህግ ጥብቅና የሚቆሙ ሰዎች እና ቡድኖችም ለንጉሳውያን ቤተሰቦች ገንዘብ እንዲከፍሉ ያስገድዷቸው ነበር፡፡ በአንድ በተወሰነ ጊዜ በሚደረግ የገንዘብ ፍሰት ሁኔታ ላይ በመመስረት ጆን የህግ መብት እና ክብርን ሁልጊዜ ከፍተኛ ጨረታ ላቀረበ ሰው ወይም ቡድን በሽያጭ ያቀርቡ ነበር፡፡ ጆን ጦርነቶችን ለማሸነፍ በቅጥር ወሮበላ ነፍሰ ገዳዮች ተከብበው ይኖሩ ነበር፡፡ በኃይማኖት ጉዳዮች ላይ ጣልቃ ይገቡ ነበር፡፡ የስልጣን ሀራራ የተጠናወታቸው የስልጣን ቁንጮ ሰው ነበሩ፡፡
ንጉስ ጆንን የምገልጽበት ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ በ21ኛው ክፍለ ዘመን አንድ አማካይ የአፍሪካ አምባገነን ወሮበላ ዘራፊ “መሪዎች“ ከሚያደርገት ጋር ተመሳሳይ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከአንዱ የአፍሪካ ጫፍ ወደ ሌላው የአፍሪካ ጫፍ ሲታይ የአፍሪካ አምባገነኖች ተቃዋሚዎቻቸውን በእራሳቸው ስልጣን ከህግ አግባብ ውጭ በቁጥጥር ስር ያውላሉ፣ በየእስር ቤቱ ያግዛሉ፣ ያሸማቅቃሉ እንዲሁም ያስፈራራሉ፡፡ የአፍሪካ አምባገነኖች የይስሙላ ፍርድ ቤቶቻቸውን በመጠቀም ተቃዋሚዎቻቸውን ለማሰቃያነት ይጠቀሙባቸዋል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ በግልጽ በአደባባይ ከፍተኛ ገንዘብ ለሚሰጥ ፍትህን ይሸጧታል፡፡ ቀደምቶቻቸው ይዘውት የኖሩትን እና ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የመሬት የባለቤትነት መብት በመንጠቅ ለውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች በጣም ርካሽ በሆነ ዋጋ ይሸጡታል፡፡ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ሳያነሱ በሰላማዊ መንገድ በሚቃወሟቸው ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጦር በማዝመት እልቂት እንዲፈጸምባቸው ያደርጋሉ፡፡ እነዚህ አምባገነኖች የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን ያስራሉ፣ ያሰቃያሉ እናም ግዞት እንዲወርዱ ያደርጋሉ፡፡ በየዓመቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ከእራሳቸው ህዝቦች በመስረቅ በውጭ ሀገር የሚገኙ የባንክ ሂሳቦቻቸውን በማደለብ ላይ ይገኛሉ፡፡ በኃይማኖት ላይ ጣልቃ ይገባሉ እናም በስልጣን ወንበሮቻቸው ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመኖር የጥላቻ መንፈስን ያራምዳሉ፡፡ በእራሳቸው ህዝቦች ላይ ግድያን የመፈጸም እና እልቂትን የማምጣት ጦርነት ናፋቂዎች ናቸው፡፡ በሰው ልጆች ላይ የሰብአዊ መብት ወንጀሎችን የሚፈጽሙ እና የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን የሚተገብሩ ፈጣጣዎች ናቸው፡፡ በሰው ልጆች ላይ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ወንጀል በመፈጸማቸው ምክንያት በአሁኑ ጊዜ ቢያንስ ሁለት የሚሆኑ የአፍሪካ ሀገር መሪዎች በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶባቸው የክስ ሂደታቸው በመታየት ላይ ይገኛሉ፡፡ እንደ ንጉስ ጆን ሁሉ የአፍሪካ አምባገነን ገዥዎች ሰላማዊ ዜጎችን ሲገድሉ ይስቃሉ፣ ሆኖም ግን እየሳቁም ቢሆን ይገድላሉ፡፡ ገሀነም እራሷ የበሰበሱትን የአፍሪካ አምባገነኖች እና ወሮበላ ዘራፊዎች ትጸየፋቸዋለች፡፡
የእንግሊዝ መብት፣ ክብር እና ነጻነት የጸደቀበትን/Magna Carta (ማግና ካርታ) ጊዜ የማከብረው ለምንድን ነው?
የእራሴን ጥያቄ ለመመለስ በኢትዮጵያ ገና ልጅ የነበርኩበትን ጊዜ ወደ ኋላ 50 ዓመታት ተጉዠ ማስታወስ ይኖርብኛል፡፡ ማንበብን በጣም የምወድ ልጅ ነበርኩ፡፡ የዓለምን የስነጽሁፍ እና ፍልስፍና ስራዎች በማግኘቱ ረገድ በጣም እድለኛ ነበርኩ፡፡ እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ ለነበሩት የአሜሪካ የስነጽሁፍ ስራዎች ፍጹም እንግዳ አልነበርኩም፡፡ እንደዚሁም ደግሞ የአማርኛ ታዋቂ ስነጽሁፍ የሚባሉትን ሁሉ አነባለሁ፡፡
በህጉ የበለጠ እደነቃለሁ፡፡ ገና ከወጣትነት እድሜዬ ጀምሮ ስለዓለም የህግ ሂደት ተጋላጭነቱ ነበረኝ፡፡ በአዲስ አበባ በከፍተኛ ፍርድ ቤቶች እና በሌሎች ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ ፍርድ ቤቶች ላይ የሚካሄዱትን የፍርድ ሂደቶች በአንክሮ እከታተል ነበር፡፡
ከፍርድ ቤቶች ግቢ ውጭ ባሉ መንገዶች ዳርቻ በሚገኙ ትናንሽ ቤቶች/ኪዮስኮች ውስጥ ተቀምጠው በግራ እና በቀኝ ለሚደረግ ክርክር የሚሆን ማመልከቻ  በአማርኛ በእጅ ጽሁፍ በቢክ እስክብሪቶ ይጽፉት የነበረውን ውብ የሆነ የእጅ ጽሁፍ በግልጽ አስታውሳለሁ፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ ሰዎችን ሊያሳምን የሚችል አንደበት ያላቸውን የህግ ባለሙያዎችን እና ጥሩ ዳኝነት የሚሰጡ የህግ ሰዎችን በተለይም ደግሞ ስለህግ ጭብጦች በተለይም በፍርድ ችሎቱ ላይ ስለሚሰጠው ፍርድ ሳይሆን ስለህግ ስነስርዓት የሚናገሩትን እና የሚከራከሩትን ዳኞች ማዳመጥ ከምንም በላይ ደስታ ይሰጠኝ ነበር፡፡ አንደበተ ርትኡ የሆነው ንግግራቸው እና ያነጋገር ግልጽነታቸው፣ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ሊያሳምን በሚችል መልኩ የሚቀርበው ንግግራቸው እና በጥቂት የህግ ባለሙያዎች የሚደረገው አዕምሮን የሚገዛው ንግግራቸው እንደዚሁም በህግ ሂደቱ ላይ በሚነሱት የሰሉ ጥያቄዎች እና ነገሮችን ፈጥኖ የመረዳት እና ተገቢ የሆነ ፈጣን መልስ የመስጠት ችሎታቸውን በመመልከት በአዕምሮዬ ላይ የዕድሜ ልክ ትዝታን ጥሎ አልፏል፡፡ እነዚህ ሰዎች ለእኔ ትልቅ ተምሳሌቶች ነበሩ፡፡
በአማርኛ የተዘጋጁትን የኢትዮጵያን የወንጀለኛ መቅጫ እና የፍትሐብሄር ህጎችን በተለይም ደግሞ የህግ ባለሙያዎች እና ዳኞች በእነዚህ ህጎች ላይ ክርክር ካካሄዱ በኋላ  ነጥብ በነጥብ እየለየሁ አንብቢያቸዋለሁ፡፡ በተለይም የወንጀለኛ እና የፍትሐብሄር ስነስርዓቶችን ከምንም በላይ እወዳቸዋለሁ፡፡ የፍትሐብሄር ስነስርዓት ህግ ከ245 ገጾች ባነሰ ጥራዝ የተቀነበበ ነው፡፡ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ወደ 69 ገጾችን አካትቶ በመያዝ ከፍትሐብሄር ስነስርዓት ህጉ ጋር በአባሪነት እንዲያያዝ ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡ ማንኛቸውም ቢሆኑ ለማንበብ እና ግንዛቤ ለመውሰድ የሚያስቸግሩ አይደሉም፡፡
የስነስርዓት ህጎችን በመጣስ ረገድ የሚቀርቡ የህግ የክርክር ጭብጦችን መከታተል ከምንም በላይ ያስደስቱኛል፡፡ ፖሊስ የቀረበለትን የወንጀል ድርጊት ተገቢ በሆነ መልኩ መርምሮ ለፍትህ ያቀርባልን? ወንጀለኛ ነው ተብሎ የተጠረጠረን/የተጠረጠረችን ሰው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለው ግምታዊ በሆነ ስሌት በመገፋፋት ነውን? ፖሊስ ተሰራ ለተባለው ወንጀል ተገቢ የሆነውን ማስረጃ ይዟልን? ለፍትሐብሄር ስነስርዓት ሕግ ክርክር ጉዳይ የቀረቡት ሰነዶች በትክክለኛነት የተረጋገጡ ናቸውን? በአንድ በሕግ በተያዘ ጉዳይ ላይ ማገጃ ለማውጣት የሕግ መሰረት አለውን? ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት (ከላይ ያሉትን ስዕሎች ይመልከቱ) ተዘጋጅተው እስከ አሁን ድረስ በስራ ላይ እየዋሉ ያሉት የኢትዮጵያ የሕግ ስርዓቶች ዋናዎቹ ሰነዶች በእጀ ላይ ይገኛሉ፡፡ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ እና የፍትሐብሄር ስነስርዓት ሕግ ሰነዶች በአሁኑ ጊዜ ካለው ዓለም አቀፍ የሕግ መስፈርት አንጻር ሲገመገሙ እንኳ ከፍተኛ የሆነ እመርታ የነበራቸው መሆናቸውን አውቃለሁ፡፡ በእርግጥ የግማሽ ምዕተ ዓመት እድሜን ከመግፋት አንጻር በሰነዶቹ ጥራዞች ላይ የእርጅና ምልክት ከመታየት ባለፈ ምንም ዓይነት ችግር የለባቸውም፡፡ ወረቀቱ ከጊዜ ብዛት የተነሳ ቀለሙ ወደ ብጫነት ተቀይሯል፡፡ እንደዚሁም በእነዚህ ጥራዞች ዋና መገጣጠሚያ ላይ የነበረው ሙጫ ደርቋል እናም ከብዙ ጊዜ በፊት ተለያይቷል፡፡ ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን በጥንቃቄ በማንበብ እና በመመርመር እነዚህ የሕግ ስርዓቶች ምን ያህል ዘመናዊ እና የተሻሻሉ እንደነበሩ በአድናቆት እመለከታለሁ፡፡
ከ30 ዓመታት በኋላ የእራስ ጥፋትን በፍርድ ቤት ማመንን በማስመልከት በተደረገው በ5ኛው የዩ.ኤስ አሜሪካ የሕገ መንግስት ማሻሻያ ያጎናጸፈውን መብት ከግንዛቤ በማስገባት የስነስርዓት ሂደቱን ለመጠበቅ በዓለም ላይ አንዱ እና ታዋቂ ከሆነው ከካሊፎርኒያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፊት የመቆም ዕድልን አግኝቸ ነበር፡፡ በዚያ ፍርድ ቤት በሳክራሜንቶ ካሊፎርኒያ ለቃል ክርክር ከፍርድ ቤቱ በር ደረጃ ላይ ስራመድ  በዚያ የልጅነት ዕድሜዬ እንደዚያ ያሉትን አስደማሚ የሆኑትን ታላላቆቹን የህግ ባለሙያዎች እና ዳኞችን ለአጭር ጊዜም ቢሆን አስታወስክዋቸው። ደስ ብሎኝም በጣም ፈገግ አልኩኝ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ እ.ኤ.አ በ1955 ተሻሽሎ የወጣው የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ሕገ መንግስት ነበር፡፡ በማንኛውም ጊዜ ቢሆን ግን በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት ውጭ ስለሕገ መንግስት የተደረገ ክርክር ተመልክቸ አላውቅም፡፡ አንዳንድ ጊዜ የተማሩ፣ የበቁ ዳኞች እና የሕግ ባለሙያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ “ሕገመንግስቱ” ሲሉ እሰማለሁ፣ ሆኖም ግን በሕገ መንግስቶቹ ረቂቆችም ሆነ ከዚያ በኋላ ባሉት ጊዚያት ውስጥ ሁሉ የእነርሱ የተመዘገበ ውይይት ወይም ደግሞ የተናገሩት ንግግር ለመኖሩ በህሊናዬ ላይ የሚያቃጭል አንድም ነገር የለም፡፡
ያንን የኢትዮጵያን ሕገ መንግስት ለበርካታ ዓመታት እንዳጠናሁት የሕገ መንግስቱ ምዕራፍ 3 ከአሜሪካው የሰብአዊ መብት ሕግ ጋር ባልተጠበቀ መልኩ አንድ ሆኖ የመገኘቱ ጉዳይ በጣም አስገርሞኛል፡፡ ምዕርፍ 3 “የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ሕግ” ተብሎ ሊገለጽ ይቻላል፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ እንደዚህ ያለውን ሰፊ መሰረት ያለውን እና ለህዝባቸው ነጻነትን ሊያጎናጽፍ የሚችል ሕገ መንግስት እንደ ንጉሳዊ ወግ አጥባቂ አስተዳደር ልዩ የሆነ የፖለቲካ ቁጥጥር ባለበት ስርዓት ውስጥ ቢያንስ በመርህ ደረጃ እንኳ ምን ያህል ዘመናዊነትን ለማስፈን ጥረት ያደርጉ እንደነበር ጉልህ ማስረጃ ነው፡፡ እንዲያም ሆኖ ጥቂቶቹ ሕገ መንግስቱ ባጎጸፋቸው ነጻነቶች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ በታሪክ እንደምንረዳው እንደማንኛውም ንጉሳዊ አገዛዝ ሁሉ የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ሕገ መንግስትም ጊዜ አልፎበት አልፏል፡፡
እ.ኤ.አ በ1955 ተሻሽሎ የወጣው የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ከጥቂት ነጥቦች በስተቀር እንዳለ የአሜሪካ የሰብአዊ መብት የሕግ ድንጋጌ ጋር እና ከዩ.ኤስ አሜሪካ ሌሎች የሕገ መንግስት ማሻሻያዎች ጋር አንድ እና ተመሳሳይ የሆነ የካርቦን ቅጅ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል የሚከተሉትን መመልከቱ ዋቢነቱን የበለጠ ግልጽ ያደርገዋል፣
ማንም ቢሆን የሕግ እኩልነትን አይነፈግም…ማንም በሀገሪቱ ግዛት ውስጥ ያለ ሰው ከሕግ አግባብ ውጭ ሕይወቱን፣ ነጻነቱን ወይም ንብረቱን አያጣም…ማናቸውም ሰው በሀገሪቱ ሕግ መሰረት በሕግ አግባብ ካልሆነ በስተቀር ንብረቱን አያጣም…የኢትዮጵያ ሕዝቦች በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብ መብት አላቸው…ማናቸውም ሰው በፍርድ ቤት ማዘዣ ካልሆነ በስተቀር በቀጥጥር ስር አይውልም…ማናቸውም በቁጥጥር ስር የዋለ ሰው በ24 ሰዓቶች ውስጥ ለፍትህ አካል መቅረብ አለበት…በማናቸውም በወንጀል ጉዳዮች ክስ የተመሰረተበት ሰው የምስክሮችን ማስረጃነት በማቅረብ ጉዳዩ በፍጥነት እንዲያልቅለት ይደረጋል… በጥርጣሬ የተያዘ ወንጀለኛ የሚፈልገውን የሕግ አማካሪ ጠበቃ በመንግስት ወጭ እንዲቀጠርለት እና የሕግ አገልግሎት የማግኘት መብት አለው…የሕግ ጠበቃ ቀጥረው መከራከር የማይችሉ ድሆች በመንግስት ጠበቃ ተቀጥሮላቸው መከላክል እንዲችሉ በግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ሕገ መንግስት ከጸደቀ እናመተግበር ከጀመረ ከ8 ዓመታት በኋላ እንኳ እ.ኤአ. እስከ 1963 ድረስ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ጠበቃ ቀጥረውመከራከር የማይችሉ ደኃ ዜጎች ነጻ የሕግ አግልግሎት ጥቅም የማግኘት መብት አልነበራቸውም፡፡ ማናቸውም በቁጥጥር ስር የዋለ ሰው ጥፋተኝነቱ በፍትህ አካል እስካልተረጋገጠ ድረስ ወንጀለኛ አይደለም…ማናቸውም ሰው  በአንድ ዓይነት ጥፋት ሁለት ጊዜ ሊቀጣ አይችልም…ማናቸውም ሰው ጭካኔ የተሞላበት እና ሰብአዊነት የጎደለው ቅጣት ሊፈጸምበት አይችልም…ሁሉም ሰዎች እና የግል መኖሪያ ቤቶች ከህገ ወጥ ምርመራ እና ፍተሻ ነጻ ናቸው…ማናቸውም ሰው በንጉሱ ላይክስ የመመስረት መብት ሊኖረው አይችልም…በአሁኑ ጊዜ ተሻሽሎ የተዘጋጀው ሕገ መንግስት በሀገሪቱ ላሉ ግዛቶች ሁሉ የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ይሆናል…
እ.ኤ.አ በ1994 በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ሕወሀት) ተረቅቆ በስራ ላይ የዋለው ሕገ መንግስትም ፍትህን እና ነጻነትን በማጎናጸፉ ረገድ በተግባር ሳይሆን በቃላት አጻጻፉ በጣም የተዋበ እና የተሽሞነሞነ የተዋጣለት ሰነድ ነው፡፡ በምዕራፍ 3 “ሰብአዊ መብቶች” ከሚለው ስር የተገለጹት በእርግጠኝነት የአሜሪካንን የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች እዳለ በመኮረጅ እንዲህ በማለት እንዲካተቱ ተደርገዋል፣
በህግ አግባብ ከተደነገገው ውጭ ማንም ሰው ቢሆን ነጻነቱን አያጣም…ማንም ሰው ክስ ሳይመሰረትበት እና ጥፋተኛነቱ በህግ አግባብ ሂደት ሳይረጋገጥ በቁጥጥር ስር ሊውል ወይም ደግሞ ሊታሰር አይችልም…ማንም ሰው ቢሆን ጭካኔ የተሞላበት እና ኢሰብአዊነት የሆነ ድርጊት ወይም እራስን ሊያዋርድ የሚችል ቅጣት ሊፈጸምበት አይችልም፡፡ ማንም በወንጀል ክስ የተመሰረተበት ተጠርጣሪ ስለተከሰሰበት ክስ ምንነት እና ለክሱ ምክንያት ስለሆነው ጉዳይ ወዲያውኑ እና በዝርዝር የመነገር መብት አለው፡፡ ማንም ቢሆን ስለተከሰሰበት ጉዳይ ምስክርነት ያለመስጠት፣ ወይም ደግሞ ዝም የማለት እና ያለመናገር መብት አለው…ማንም ቢሆን ተጥርጥሮ በቁጥጥር ስር በዋለ ሰው በ24 ሰዓቶች ጊዜ ውስጥ ለፍትህ አካል የመቅረብ መብት አለው፡፡ ማንኛውም በወንጀል የተጠረጠረ ሰው ሕጋዊ ከሆነው የፍትህ አካል የመጥሪያ ደብዳቤ ሊደርሰው እንደሚገባ የመጠየቅ እና የማግኘት መብት አለው…ማንኛውም በጥርጣሬ በቁጥጥር ስር የዋለ ሰው በዋስ የመለቀቅ መብት አለው…ማናቸውም በጥርጣሬ በቁጥጥር ስር የዋለ ሰው ምንም ዓይነት የመዘግየት ሁኔታ ሳይፈጠር በፍርድ ቤት ድምጹ የመሰማት መብት አለው…ማንም በጥርጣሬ በቁጥጥር ስር የዋለ ሰው ስለተከሰሰበት ጉዳይ በዝርዝር በጽሁፍ ሊገለጽለት ይገባል፡፡ ማንም በጥርጣሬ በቁጥጥር ስር የዋለ ሰው በእራሱ የሕግ ጠበቃ አቁሞ መከራከር ወይም ደግሞ የገንዘብ አቅም የሌለው ከሆነ መንግስት ጠበቃ ቀጥሮለት ሊከራከር የሚያስችል መብት አለው… ሕገ መንግስቱ የሀገሪቱ የሕጎች ሁሉ የበላይ ሕግ ነው…
ህወሀት የአሜሪካንን የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች እንዳለ ኮርጆ በሰነዱ ላይ አሰፈረ፣ ከዚያም ብዙም ሳይቆይ ወዲያውኑ በመበጣጠስ ወደ ቅርጫት መጣል ጀመረ፡፡
ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ እ.ኤ.አ በ1955 ተሻሽሎ ስለወጣው የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ስለሲቪል ርትዕ እና ስለግለሰብ ነጻነቶች የሚያትተውን ሀሳብ ያገኙት ከየት ነው?
ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ስለሲቪል ርትዕ እና ስለግለሰብ ነጻነቶች የሚደነግገውን እና እ.ኤ.አ በ1994 ያረቀቀውን ሕገ መንግስት የመነሻ ሀሳቡን ያገኘው ከየት ነው?
ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ከላይ የቀረበውን የህገ መንግስት ድንጋጌ እንዳለ ያገኙት እና ገልብጠው የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አካል ያደረጉት ከአሜሪካ የሰብአዊ መብት ድንጋጌ ወስደው መሆኑን ምንም ዓይነት ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ አይደለም፡፡
ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ስለሲቪል ርትዕ እና ስለግለሰብ ነጻነቶች የሚያትተውን ሕገ መንግስት ሀሳቡን ያገኘው እና የኮረጀው እ.ኤ.አ በ1955 ተሻሽሎ ከወጣው የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ነው፡፡
ስለሆነም የ64 ሺ ዶላር ጥያቄ ሆኖ ሊቀርብ የሚችለው፡ አሜሪካውያን ስለእያንዳንዱ ሰው ነጸነት እና ርትዕ የሚያትቱትንጠቃሚ ሀሳቦች ያገኟቸው ከየት ነው? የሚለው ነው፡፡
አሜሪካኖች እነዚህን ጠቃሚ የግለሰብ መብቶች እና ርትዕ ሀሳቦች ያገኟቸው የእንግሊዝ ህዝብ መብቱን፣ ክብሩን እና ነጻነቱን/Magna Carta ካስከበረባቸው የሰብአዊ መብት ድንጋጌ መሰረታዊ ሀሳቦች በመነሳት ነው፡፡ በአሜሪካ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች ላይ በዝርዝር የተቀመጡት ነጻነቶች (የመጀመሪያዎቹ የዩ.ኤስ አሜሪካ አስሩ የሕገ መንግስት ማሻሻዎች) ቅሬታን የማቅረብ ነጻነት (1ኛው ማሻሻያ)፣ የሕግ የበላይነትን እና አብዛኞቹን ነጻነቶችን ያካተተውን  (5ኛው እና 14ኛው ማሻሻያዎች)፣ ስለትክክለኛ ካሳ (5ኛ ማሻሻያ)፣ ከመጠን ያለፈ ዋስትና እና ገንዘብ የማስያዝን (8ኛ ማሻሻያ)፣ ፈጣን የሆነ የዳኝነት ሂደት፣ ከሳሾችን፣ የዳኞችን የችሎት ሂደት እና ከአድልኦ ስለጸዳ የዳኝነት ሂደትን ከመጋፈጥ አንጻር (6ኛ ማሻሻያ)፣ ስለሀገሪቷ የበላይ ሕግ (አንቀጽ 4)፣ የመጥሪያ ወረቀት ስለማግኘት መብት (አንቀጽ 1 ንኡስ አንቀጽ 9) እንደዚሁም የመንቀሳቀስ፣ የግል ነጻነት እና ሌሎች መብቶች ሁሉ መሰረታቸው የእንግሊዝ ህዝብ መብቱን፣ ክብሩን እና ነጻነቱን ያወጀበት ድንጋጌ ነው፡፡
ቀደም ሲል አቅርቤው ለነበረው ጥያቄ መልሱን አግኝቻለሁ፡፡ የእንግሊዝ ህዝብ መብቱን፣ ክብሩን እና ነጻነቱን/Magna Carta ያስከበረበትን ጊዜ አከብራለሁ ምክንያቱም ለኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ርትዕ እና ነጻነቶች መሰረቱ የሚገኘው የእንግሊዝ ህዝብ መብቱን፣ ክብሩን እና ነጻነቱን/Magna Carta ካወጀበት የቀደምት የዘረመልድ/ዲኤንኤ ውህድ ውስጥ ስለሆነ ነው፡፡ ይኸ እውነታ ለጥቂቶች እንደ አስደናቂ ነገር ሊሆን ይችላል፣ ሆኖም ግን የኢትዮጵያ የሕገ መንግስት የነጻነት ድንጋጌዎች የዘረመልድ አፈጣጠር የተወረሱት ከእንግሊዝ ህዝብ መብቱን፣ ክብሩን እና ነጻነቱን/Magna Carta ለማስከበር ከደነገገበት ትዕዛዞች እና መርሆዎች የመነጨ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ያ ውርስ ወይም ደግሞ የዝርያ ቅብብሎሽ ለኢትዮጵያ ብቻ ልዩ ሆኖ የተተወ አይደለም፡፡ በግልጽ የሚታየው እና የዜጎችን ነጻነት እና ፍትህ በማጎናጸፍ የግለሰቦችን ነጻነት እና ክብር የሚያስጠብቀው ማንኛውም ዘመናዊ የሆነ ሕገ መንግስት ቅርጹ የተለያየ ሊመስል ይችላል ሆኖም ግን ሁሉም በቀጥታ የዘር ግንዳቸው የእንግሊዝን ህዝብ መብቱን፣ ክብሩን እና ነጻነቱን ካስጠበቀበት/Magna Carta ሕገ መንግስት የሚመዘዝ ነው፡፡
የእንግሊዝ ህዝብ መብቱን፣ ክብሩን እና ነጻነቱን ያስጠበቀበት/Magna Carta (ማግና ካርታ) ምንድን ነው?
ማግና ካርታ በተገዥ ህዝቦች የተረቀቀ እና በገዥዎች ላይ እንዲተገበር የተጣለ የመጀመሪያው የሕግ ሰነድ ነበር፡፡ ተገዥ መደቦች ገዥዎቻቸውን አስገድደው የሕግ የበላይነትን እንዲቀበሉ ለማድረግ የተደረገ የመጀመሪያ ጊዜ ድፍረትን የተላበሰ ጥረት ነበር፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገዥዎችን ደህንነት እና የቀጣዩን ትውልድ ሰላም እና ንብረት ሊያስጠብቅ በሚችል መልኩ በእራሳቸው በተገዥዎቹ እጆች ሕጎቹ ተጽፈው በተገዥዎች እና በገዥዎች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ የግዳጅ የፖለቲካ ስምምነት ሰነድ ነው፡፡ በእርግጥ ያ ሰነድ የእንግሊዝ ተራ ህዝቦች በእንግሊዝ ንጉሳውያን እና የመሬት ከበርቴዎች ይደርሱባቸው የነበሩትን የዘፈቀደ ያልተገደቡ ጭቆናዎችን እና በደሎችን ከስርዓቱ በማስወገድ ነጻነታቸውን ለማስከበር ሲሉ ያዘጋጁት ሰነድ ነው፡፡
የማግና ካርታ ሕጎች አስርቱን ትዕዛዞች መተግበር ከመጀመራቸው በፊት ሌሎች ታላላቅ የሆኑ የሕግ ድንጋጌዎች ነበሩ፡፡ ትክክለኛነታቸው ታምኖበት ቀደም ሲል ተሰብስበው የነበሩ ሕጎች እና የሮማን የሕግ ባለሙያዎች የተረጎሟቸው የሕግ ትርጉሞች በዚህ ርዕስ ስር ከሚካተቱት ውስጥ ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ሮማውያንም ህጉን ከታች ያሉት ተራ የሆኑት የሮማ ህዝቦች መብቶቻቸውን እንዲያውቁ እና በንጉሳውያን ቤተሰቦች እና በመሬት ከበርቴዎች ሰብአዊ መብቶቻቸው እንዳይደፈጠጡ ለመከላከል በማሰብ ቀደም ሲል ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ451 – 450 የወጡ የፍትሐብሄር፣ የወንጀለኛ እና የኃይማኖታዊ ጉዳይ ሕጎችን ከሮማ ሕጎች ጋር በማጣመር ለሁሉም ዜጎች እንዲዳረስ ያደርጉ ነበር፡፡ በጥንታዊ አቴን የሶሎን ሕጎች የመሬት ባለቤት በሆኑ ንጉሳውያን ቤተሰቦች እና በገበሬዎች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ዒላማ በማድረግ ግጭቶችን በሰላማዊ መልኩ ለመፍታት ጥረት ያደርጉ ነበር፡፡ የሶሎን ሕጎች  የተሳሳተ እና ትክክለኛ ያልሆነ ቡድን ካልሆነ በስተቀር ለማንኛውም አቴናዊ የህግ ችሎት ስርዓት ለማካሄድ የሚያስችሉ ነበሩ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ሆነው ብይን የሚሰጡ ዳኞችን ውሳኔ የሚገመግም ስርዓትን አቋቁመው ለብዙሀኑ ህዝብ ጥሩ የሆነ የህግ አገልግሎት ይሰጡ ነበር፡፡ የጥንታዊ ባቢሎናውያን የሐሙራቢ ህግ በርካታ የሆኑ ጉዳዮችን ያካተቱ ማለትም የቤተሰብ አባወራዎችን እና የቤተሰብ ጉዳዮቸን ጨምሮ እንዲሁም የሲቪል እና ወታደራዊ አገልግሎቶችን በመያዝ 282 ሕጎችን በማውጣት በስራ ላይ አውለው ነበር፡፡ ያ ሕግ በአሁኑ ጊዜ ዓይን ላጠፋ ዓይን፣ ጥርስ ለሰበረ ጥርስ የሚለውን አስከፊ ሕግ ያስታውሰናል፡፡
የማግና ካርታን የሕግ ሰነድ የሚቀድሙ ማናቸውም ዓይነት ሕጎች በሕግ የበላይነት መርህ ላይ የተመሰረተ ሕግ እስከ አሁን ድረስ አልተገኘም፡፡ ማናቸውም ሕጎች ቢሆኑ ተራ በሆነው ህዝብ ሉዓላዊነት ላይ በመመስረት የተረቀቁ እና የጸደቁ አይደሉም፣ ወይም ደግሞ በእራሳቸው በተራ ሕዝቦች የወጡ ሕጎች አይደሉም፡፡ ተራ የሆኑ ሕዝቦች በሌሎች ተረቅቀው እና ጸድቀው በእራሳቸው ላይ ስለሚጫኑባቸውን ሕጎች የሚሉት ነገር በጣም አናሳ ነው፡፡ ለሕጎቹ እንዲገዙ እና እየታዘዙ አስከፊ የሆነ ህይወትን ብቻ ያለምንም ተስፋ እንዲኖሩ ነው የሚፈለገው፡፡ ተራው ሕዝብ በገዥዎቻቸው ስልጣን ላይ ገደብን ለመጣል ድፍረቱ የላቸውም፡፡
ከማግና ካርታ ሕግ መውጣት በፊት ንጉስ ጆን እና የእርሳቸው ቀደምት ንጉሶች በኃይል እና በማስገደድ መርህ ላይ የተመሰረተ የአገዛዝ ስርዓትን ያራምዱ ነበር፡፡ ጆን የፈለጉትን ነገር ያደርጉ ነበር ምክንያቱም እንደ ንጉስነታቸው እርሳቸው ከሕጉ በላይ እንደሆኑ አድርገው ያምኑ ነበር፣ እናም ምንም ዓይነት ምድራዊ ለሆነ ኃይል ተጠያቂ አልነበሩም (ምናልባትም ለቅዱስ ጳጳሱ)፡፡ ለመካከለኛው እንግሊዝ ዘመን ፖለቲካ የእንግሊዝ ንጉሳውያን በጊዜው ባለው የማህበረሰብ ልማድ እና ልማዳዊ ህግ (በፍርድ ቤቶች ዳኝነት እና አዋጆች) እየታገዙ እና በአገዛዙ ዋና አማካሪ እየተረዱ ይሰሩ እንደነበር በአጠቃላይ ሁኔታ ቅቡል ነበር፡፡ በእርግጥ የጆን ቀደምት የነበሩት ሄንሪ 2ኛ ተግባራዊ የሆነ የሕግ ስርዓትን በመተግበር ከሕግ አግባብ ውጭ የንብረት መወሰድን የሚከለክል ህግ አውጥተው ነበር፡፡
ጥያቄ ሆኖ የሚቀርበው ንጉሱ እራሱ ያወጣውን ሕግ እና ከእርሱ በፊት የነበሩ ነገስታት ያወጧቸውን ሕጎች ሳይተግብራቸው የቀረ እና ልማዳዊ ስርዓቶችን በሙሉ የተወ እና ቀደም ሲል የታወጁ አዋጆችን ወይም ደግሞ ሌሎች ነገሮችን ሁሉ አልቀበልም ያለ እንደሆነ ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ1215 ተራ የሆነው የእንግሊዝ ህዝብ ከንጉስ ጆን ጋር በተያያዘ መልኩ እንደዚህ ባለ ችግር ውስጥ ነው ወድቀው ሲማቅቁ የነበሩት፡፡ ንጉስ ጆን ደንታ ቢስ እና ተራ ህዝቦችን የሚጨቁኑ ገዥ ነበሩ፡፡ በተራው ህዝብ ላይ ጦርነትን አወጁ፡፡ ምንም ዓይነት ማስረጃ ሳይቀርብ ወይም ደግሞ ጥፋት ለመስራታቸው በማስረጃ ሳይረጋገጥ ሰዎችን እንዲያቀርብ የፍርድ ቤት ዳኛን አዝዘው በመላክ ሰዎችን አምጥቶ እንዲታሰሩ ያደርጉ ነበር፡፡ ንጉስ ጆን ከህዝቦች ላይ የመሬት ከበርቴነት ክፍያዎችን እና ግብሮችን ይጠይቁ ነበር፡፡ ጆን እራሳቸው ላወጧቸው ህጎች ተገዥ መሆን እንዳለባቸው አይቀበሉም ነበር፡፡ እንዲሁም ያሉት የሕግ ሂደቶች በተግባር ላይ እንዳይውሉ ቀስ አድርገው በድብቅ እንዲወጡ ያደርጉ ነበር፡፡
የእንግሊዝ ተራ ሰዎች በጆን የዘፈቀደ ስልጣኖች ላይ ገደብ ለማስቀመጥ ፈለጉ፡፡ ጆን እራሳቸው ላወጧቸው ህጎች እና ለሀገሪቱ ሕጎች እራሳቸውን እንዲያስገዙ ለማድረግ ፈለጉ፡፡ እ.ኤ.አ ሰኔ 1215 በቁጣ የተሞሉ የታጠቁ ተራ ህዝቦች በታምስ ወንዝ ዳርቻ ባለው የውኃ መስክ ቦታ ከለንደን ከተማ በቅርብ ርቀት በሩኒሜድ አካባቢ በንጉስ ጆን ላይ ባሏቸው ቅሬታዎቻቸው ላይ ለመወያየት እና መፍትሄ ለመስጠት ተሰባስበው ታዩ፡፡ በእርግጥ በዚያ ቦታ ላይ የተሰባሰቡት ለንጉስ ጆን እንዲህ የሚል ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ነበር፡ አምባገነናዊ የሆነ አሰራርዎን ያቁሙ ወይም ደግሞ ከአማጺያን ጋር የእርስ በእርስ ጦርነት ለማካሄድ እራስዎን ዝግጁ ያድርጉ የሚል ነበር፡፡
ጆን ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ አልነበሩም፡፡ ይልቁንም በቅርቡ ፈረንሳይን መውረራቸውን ተከትሎ በደረሰባቸው አሳፋሪ ሽንፈት በመበሳጨት ላይ ነበሩ፡፡ ተራው ህዝብ ለጆን ቅጥር ነፍሰ ገዳይ ወታደሮች የገንዘብ ክፍያ ዕዳ እንዲከፍሉ እንዲሁም የውትድርና አገልግሎት ላለመስጠት የመሬት ከበርቴዎች ገንዘብ ይከፍሉ ነበር፣ ወይም ለወታደራዊ አገልግሎት ወታደር ያቀርቡ ነበር፡፡ ከፈረንሳይ ንጉስ ጋር የንጉስ ጆንን ጥላቻ በመከተል አብረው ጥላቻ ውስጥ ለመግባት እና ለውጊያው ድጋፍ መስጠት አልፈለጉም፡፡  የእንግሊዝ ተራ ሕዝቦች ለጆን ወታደራዊ ጀብድ ድጋፍ ላለመስጠት መፈለጋቸውን ተከትሎ ንጉስ ጆን የጭቃ ጅርፋቸውን ማጮህ እና መበሳጨት ጀመሩ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ እ.ኤ.አ በ1208 ከሮማ ጳጳስ 3ኛ ጋር በነበራቸው ችግር ምክንያት የንጉስ ጆን የድርድር አቋምም እየተዳከመ እና እየተሸረሸረ መጣ፡፡ በጳጳሳት ሹመት ላይ ጣልቃ የመግባት እና እና በቤተክርስቲያን ገንዘብ ላይ ጣልቃ የመግባት ሁኔታ እ.ኤ.አ በ1209 ከጳጳሳት ጋር የግንኙነት ችግርን ፈጠረ፡፡
እ.ኤ.አ ሰኔ 1215 በሩኒምድ ላይ የታዬው ተራው አማጺ ህዝብ ደስተኛ የካምፕ ሰዎች አልነበሩም፡፡ ከአንድ ወር በኋላ ለንደንን በቁጥጥራቸው ስር አደረጉ፣ እናም ታላቅ የሆነ መደራደሪያ በእጃቸው እንዳለ አረጋገጡ፡፡ በተራው ህዝብ የተረቀቁ አንቀጾች እንዳሉ እና በአሁኑ ጊዜ የሚፈለገው የንጉስ ጆን ፊረማ እንዲያርፋባቸው ነበር፡፡ ጆን ነገሮችን ሊያወሳስቡ እና ሊያታልሉ የሚችሉበት መንገድ አልነበራቸውም፡፡  ንጉስ ጆን ምንም ዓይነት ትኩረት በሌለው መልኩ የንጉሳዊ ማህተማቸውን በማኛ ካርታ ላይ በማሳረፍ እ.ኤ.አ ሰኔ 15/12115 ስምምነቱ ተፈጸመ፡፡ በዚህምመሰረት ጆን ሊያደርጉት የነበረውን የእርስ በእርስ ጦርነት በመተው ካመጹት ተራ ህዝቦች ጋር ሰላምን በማውረድ ታማኝነታውን እንደገና ለመመለስ በቁ፡፡
ንጉስ ጆን የማግና ካርታን ስምምነት ቢፈርሙም እንኳ የህጉን ዋና ባህሪያት በውል ተገንዝበው እና አጢነው ያለምንም ሰይጣኒያዊ ባህሪ እና ዕኩይ አስተሳሰብ ለመተግበር የሚያስችል ተነሳሽነት አልነበራቸውም (አንቀጽ 63ን ልብ ይሏል)፡፡
በሳምንታት ጊዜ ውስጥ የማግና ካርታ ዉጤታማነት  ግልጽ እየሆነ መጣ፡፡ ጆን በተለዬ መልኩ የማግና ካርታን ስምምነት ወደ ተግባር ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት እራሳቸውን ያስጨንቁ ጀመር፡፡ ስለ ህገ መንግስት ማስፈጠም የሚናገረው አንቀጽ 61ን በተለየ መልኩ አስቸጋሪ ሆኖ አገኙት፡፡ በዚያ አንቀጽ ላይ የንጉሳውያንን የተጠራቀመ ስልጣን አሳልፈው የሰጡትን ያህል ተሰማቸው፡፡ ተራዎቹ ሰዎች እራሳቸው ኃላፊነቱን ወስደው ከመካከላቸው 25 የሚሆኑትን በመምረጥ የሰጠናቸውን ሰላም እና ነጻነቶች በሙሉ አቅማቸው እና ኃይላቸው እዲያረጋግጡ እና ለተፈጻሚነታቸውም ክትትል እንዲያደርጉ በማለት ጆን በጥርጣሬም ቢሆን እየኮመዘዛቸው ተቀበሉ፡፡ ጆን በተራ ህዝቦች ቁጥጥር እና ክትትል ስር እንዲሆኑ እራሳቸውን ዝግጁ አደረጉ፡፡ በተራ ህዝቦች የተዘጋጀው አንቀጽ 61 ታላቅ የሆነ ብልሀት የታከለበት ነበር፡፡ ምክንያቱም ጆን በሳር ውስጥ ያለ እባብ መሆናቸውን ያውቁ ነበርና ነው፡፡
ጆን አላዘኑም፡፡ ይልቁንም እ.ኤ.አ በ1215 የበጋ ወቅት የማግና ካርታ ሕግ ተፈጻሚነት እንዳይኖረው ለጳጳሱ መልዕክት ላኩባቸው፡፡ በማመጽ ለንደንን ከበው ይዘዋት የቆዩት ተራዎቹ ሰዎች ጆን የማግና ካርታን ሕግ ተግባራዊ ካላደረጉ በስተቀር ለንደንን አንለቅም በማለት ተቃውሟቸውን አሰሙ፡፡ እ.ኤ.አ ነሀሴ 1215 ጳጳስ ኢኖሰንት 3ኛ “የጳጳሱ መግለጫ“ በሚል ርዕስ ማህተም ያረፈበት ደብዳቤ በመጻፍ የማግና ካርታን ህገወጥነት የሚያሳይ እና ትክክለኛ ያለመሆን እንዲሁም ይህ ድርጊት የንጉሳውያን ቤተሰቦችን መብት ለታላቅ ጉዳት የሚያጋልጥ መሆኑን እና ይህ ድርጊትም ለእንግሊዝ ህዝብ ታላቅ አሳፋሪ ነገር እንደሆነ በመግለጽ ይህም መቸውንም ጊዜ ቢሆን ተፈጻሚነት እንደማይኖረው እና መሰረዝ እንዳለበት የሚያስጠነቅቅ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ መስከረም 1215 በንጉስ ጆን እና በተራው ህዝብ መካከል የእርስ በእርስ ጦርነት ተጀመረ፡፡ እንደተለመደው ሁሉ ጆን ተራዎቹን ህዝቦች ለመውጋት በማሰብ ቅጥረኛ ተዋጊዎችን ቀጠሩ፡፡ ተራዎቹ ህዝቦች በበኩላቸው የፈረንሳይ አልጋወራሽ የነበሩትን በመጋበዝ ወደ እንገሊዝ መጥተው በዙፋኑ ላይ እንዲቀመጡ እና ንጉስ እንዲሆኑ ጥሪ አቀረቡ፡፡ እ.ኤ.አ በ1216 ፈረንሳዮች እንግሊዝን ወረሩ፡፡ በዚያ ጦርነት ወቅት ጆን በተቅማት በሽታ ምክንያት ህይወታቸው አለፈ፡፡
ሄንሪ 3ኛ በ9 ዓመታቸው ጆንን በመተካት በዙፋኑ ላይ ተቀመጡ፡፡ እ.ኤ.አ ጥቅምት 1216 የተሻሻለው የማኛ ካርታ ሰነድ እንዲወጣ እና የንጉሱን ፈቃደኝነት በመሳብ የተራ ህዝቦችን ሀሳብ ደጋፊ እንዲሆኑ ጥረት ማድረግ ጀመሩ፡፡ እ.ኤ.አ በ1217 ፈረንሳዮችን ከእንግሊዝ ካባረሩ በኋላ ሌላ የተሻሻለ የማግና ካርታ ሰነድ ተዘጋጅቶ ቀርቦ ነበር፡፡ ሄንሪ 18 ዓመት ከሞላቸው በኋላ እ.ኤ.አ በ1297 ንጉስ ኤድዋርድ 1ኛ ያዘጋጁትን እና በሰነዱ ላይ የነበረውን ጠቃሚ ነገር በማካተት እንዲታተም አደረጉ፡፡
የ1215 የማኛ ካርታ ሰነድ ውስጥ ያለው ነገር ምንድን ነው?
የማግና ካርታ ዝግጅት ለእንግሊዝ ህዝቦች ነጻነት እና ርትዕ ርቆ የሚያስብ ታላቅ ዕይታ የተንጸባረቀበት ልዩ የሆነ ሰነድ ነው፡፡
ይህ ሰነድ ከመሬት የባለቤትነት ጥያቄ ጀምሮ አስከፍትህ ስርዓቱ፣ ስለግብር አከፋፈሉ (መሬትን ለመጠቀም በየጊዜው የሚደረግ ክፍያ) እንዲሁም ከበርካታ ወንዞች ዓሳን እስከማስወገድ እና በርካታ ሚዛኖችን ደረጃ እስከመስጠት፣ ወዘተ ድረስ በርካታ ጉዳዮችን በማንሳት እንዲካተቱ ተደርጎ የተዘጋጀ ሰነድ ነበር፡፡
በጣም ታዋቂ ከነበሩት አንቀጾች መካከል የማግና ካርታ ሰነድ (አንቀጽ 1) የእንግሊዞችን ነጻነት ዘርዝሮ የሚያቀርብ እና እስከ ዛሬም ድረስ በተለያዩ ዘመናዊ ሕገ መንግስቶች እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ውሎች እና ስምምነቶች ላይ ጉልህ ድርሻን በመያዝ የቀጠለ መሆኑን ያመላክታል፡፡
እ.ኤ.አ በ1215 የማኛ ካርታ ላይ ንጉስ ጆን ለሁሉም ዓይነት ነጻነቶች ዕውቅና እንደሚሰጡ እና ለመቀበልም ዝግጁ እንደሆኑ ሰነዱ እጅግ በጣም ጠቃሚ እና ልዩ እንደሆነ እና በማንኛውም የዕድሜ ክልል ላይ ላለ ዜጋ ሁሉ ጠቃሚ እንደሆነ ግልጽ አድርገው ነበር፡፡ በተለይም በሚከተሉት አንቀጾች ላይ ስምምነትን አድርገው ነበር፣
በእራሳቸው በጆን ፈቃድ እና እምነት ወራሾቻቸውን ለዘላለም የመምረጥ የሚለውን የሰነድ እና ስለነጻነት የተጠቀሰውን እንደገና ማየት እና መመርመር (አንቀጽ 1)፣
በእራሳችን የመንግስት ምክር ቤት እስካልተወሰነ ድረስ ማንኛውንም ግብር የመጣል ድርጊት እንዲቆም (አንቀጽ 12)፣
የተለመዱ የህግ ችሎት ስርዓቶች እንዲካሄዱ የተለዬ ነገር ማድረግ፣ ስለሆነም የእኛን የፍርድ ቤት አሰራር ሳይከተሉ በአንድ በተወሰነ ቦታ ላይ ብቻ እንዲታዩ ሊደረግ ይችላል (አንቀጽ 17)፣
ለትንሽ ጥፋት ሁሉ ነጻ በሆነ ሰው ሁሉ ላይ የገንዘብ ቅጣት መጣል እንዲቆም… (አንቀጽ 20)፣
በዘውዱ እየታዘዙ በህዝቦች ላይ ችግርን እና መከራን የሚያዘንቡት ሕግ አስፈጻሚዎች፣ መለስተኛ ሕግ አስፈጻሚዎች፣ በጥርጣሬ የሞተን ሰው የአሟሟት ሁኔታ የሚመረምሩ ሰዎች እና የፍርድ ቤት ኃላፊዎች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ (አንቀጽ 24)፣
መለስተኛ ሕግ አስፈጻሚዎች እና የፍርድ ቤት ኃላፊዎች ከተራው ህዝብ ዘንድ የሚወስዱትን የበቆሎ እና ሌሎችንም ምርቶች ወዲያውኑ ገንዘብ ሳይከፍሉ ከመውሰድ እንዲታቀቡ (አንቀጽ 28)፣ ወይም ደግሞ የማንኛውንም ነጻ የሆነ ሰው ፈረስ ወይም ጋሪ ከተጠቀሰው ነጻ ሰው ፈቃድ ውጭ መውሰድ እንዳይችሉ (አንቀጽ 29)፣ ወይም ደግሞ ለቤተመንግስቶቻችን ለሌላ አገልግሎት ሲባል የሌላ ሰውን እንጨት ከመውሰድ መታቀብ (አንቀጽ31)፣
አንድ ነጻ የሆነ ሰው ምንም ዓይነት ከፍትህ አካል የመጥሪያ ወረቀት ሳይደርሰው በፖሊስ ወይም በማናቸውም አስገዳጅ ኃይል ተይዞ ወደ ህግ አካል እንዲቀርብ ሲደረግ የቆየው አሰራር እንዲቋረጥ (አንቀጽ 34)፣
አንድ የሕግ ኃላፊ በእራሱ ፈቃድ እና ስልጣን ታማኝነት ያለው የምስክርነት ቃልን የሚሰጥ እንዳይቀርብ በማድረግ አንድን ሰው በመመደብ በፍርድ ቤት ቀርቦ እንዲያስረዳ ሲደረግ የቆየው አሰራር ክልክል ነው (አንቀጽ 38)፣
ከሕግ አግባብ ውጭ ዜጎችን በቁጥጥር ስር ማዋል፣ በቀጥጥር ስር አውሎ ወደ እስር ቤት ማስገባት፣ ከሕግ አግባብ ውጭ ንብረትን መውረስ፣ ህገወጥነት ድርጊትን መፈጸም፣ ማንኛውንም ነጻ የሆነ ሰው ማውገዝ ወይም ደግሞ ከሕግ አግባብ ውጭ በሆነ መልኩ ምንም ዓይነት ወንጀል የሌለበትን ዜጋ ወደ እስር ቤት ማጋዝ ወይም ለሀገሪቱ ሕግ ተገዥ ያለመሆን ዓይነት የአሰራር ድርጊቶች እንዲቆሙ (አንቀጽ 39)፣
ፍትሕን፣ መሸጥ፣ መካድ ወይም ደግሞ መብትን ወይም ፍትሕን ሆን ብሎ ማዘግየት እንዲቆም (አንቀጽ 40)፣
ማንኛውም የሀገሪቱ ዜጋ የሆነ ሁሉ ከሀገሪቱ ግዛት የመውጣት እና በደህና ወደ ሀገሩ የመመለስ መብቱ አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንዲጠበቅለት (አንቀጽ 42)፣
የሀገሪቱን ሕግ እና የአሰራር ሂደቱን የማያውቁ እስካልሆኑ ድረስ የፍትህ ዳኞችን፣ መለስተኛ የሕግ አስፈጻሚዎችን፣ የሕግ ኃላፊዎችን ወይም ደግሞ የፍርድ ቤት ዳኞችን መሾም (አንቀጽ 45)፣
ሕገወጥ በሆነ መልኩ ወይም ደግሞ ከሕግ አግባብ ውጭ መሬት፣ ቤተመንግስት፣ ነጻነትን ወይም መብትን እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችን ነጥቀው ወስደው ከሆነ በአስቸኳይ እንዲመልሱ እና ተገቢ የሆነ ካሳም እንዲከፍሉ ማድረግ (አንቀጽ 52)፣
ፍትሀዊ ባልሆነ መልኩ ወይም ደግሞ የሀገሪቱን ሕግ በተጻረረ ሁኔታ ሁሉም የቅጣት ከፍያዎች የሕግ አግባብን ባልተከተለ መልኩ ተጭነው ያሉትን ወይም ከሀገሪቱ ህግ በሚጣረስ መልኩ ሲፈጸም የቆየው ክፍያ እንዲቆም ከዚህ ቀደም የተፈጸሙት ሀግወጥ  ክፍያዎችም ለባለመብቱ ተመላሽ እንዲደረጉ (አንቀጽ 55)፣
የማግና ካርታን ሕግ በተሳካ ሁኔታ ለማስፈጸም እንዲቻል ነጻ በሆነ ምርጫ አማካይነት 25 ሰዎች ተመርጠው ሁሉንም ዓይነት ስልጣን ተሰጥቷቸው የሕጉን አፈጻጸም እንዲመለከቱ፣ እንዲጠብቁ እና የተጎናጸፍናቸውን ሰላም እና ነጻነቶች ተግባራዊ ለመሆናቸው ክትትል እንዲያደርጉ ስምምነት መፈጸም (አንቀጽ61)፣
ከዚህም በተጨማሪ የማግና ካርታ የሕግ ሰነድ ነጻነትን የማያጎናጽፉ ሀረጎችንም እንዲካተቱ አድርጓል፡፡ ለምሳሌም ያህል በባሏ መሞት ምክንያት ካልሆነ በስተቀር በሌሎች ሰዎች መሞት ምክንያት አንዲት ሴት አቤቱታ ብታቀርብ አቤቱታ የቀረበበት ሰው በቁጥጥር ስር አይውልም ወይም ደግሞ አይታሰርም (አንቀጽ 54)፡፡ አንዲት ባሏ የሞተባት ሴት ምንም ዓይነት ባል ሳይኖራት ለመኖር የፈለገች ከሆነ ባል እንድታገባ የሚያስገድዳት ምንም ዓይነት ኃይል የለም (አንቀጽ 8) ካገባች ግን ለነጉሡ ክፍያ ማረግ አለባት ፡፡ ከ600 ዓመታት በኋላ የእንግሊዝ ፈላስፋ የነበሩት ጆን ስታውርት ሚልስ እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “በተፈጥሮ ሕገ መንግስት ማንም ቢሆን ሴቶች ምንድን እንደሆኑ ወይም እንዳልሆኑ፣ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ወይም እንደማይችሉ ለመወሰን የሚሞክር ማንም ሰው ቢሆን በእኔ እምነት በማስረጃ ያልተደገፈ ግምት ነው እየተናገረ ያለው የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡  ሁልጊዜ እስከ አሁንም ድረስ ተፈጥሯዊ ባልሆነ ሁኔታ ግብታዊ እድገት እስከታሰበ ድረስ ተፈጥሯቸው በከፍተኛ ደረጃ በተሳሳተ መንገድ ከመሄድ እና ከመመራት ውጭ  በተፈጥሯቸው ላይ ምንም ዓይነት አዲስ ዓይነት ነገር አይመጣም…“ የአሜሪካ ሴቶች ድምጽ የመስጠት መብታቸውን የተጎናጸፉት እ.ኤ.አ በ1920 ነው፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን በሁለተኛው አስርት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ባለንበት በአሁኑ ጊዜ ሴቶች በምርጫ ድምጽ የመስጠት መብት የሌለባቸው ሀገሮች እስከ አሁን ድረስ አሉ፡፡
የማግና ካርታ የሕግ ሰነድ ስለአይሁዶች የሚሊኒየሙን ታጋሽነት ባሳጣ መልኩ ደረጃ የሚያስይዝ ፍረጃም አቅርቧል፡፡ እንዲህ የሚል ድንጋጌን አስቀምጧል፣ “ማንም ከአይሁድ ሰው ምንም ዓይነት ነገር በብድር ቢወስድ እና ይህ ብድሩን የወሰደው ሰው ብድሩን ከመክፈሉ በፊት ቢሞት እና ብድሩን የወሰደው ሰው ወራሽ ቢሆን ለብድሩ ወለድ ሳይታሰብ የሚከፈል ይሆናል…አንድ ሰው ከአይሁድ የተበደረውን ብድር ሳይከፍል ቢሞት የሟቹ ሚስት የባሏን ውርስ የምትወስድ ሲሆን ምንም ዓይነት ብድር ሊከፈላት አይችልም…(አንቀጽ 10፣ 11)”
እ.ኤ.አ በ1215 የተዘጋጀው እና የጻደቀው የማግና ካርታ የሕግ ሰነድ በመጀመሪያ ደረጃ ለህዝብ ሲሰጥ 63 አንቀጾችን አካትቶ የያዘ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ በጣም ጥቂቶቹ  ሕጎች ብቻ የእንግሊዝ ሕግ አካል ሆነው ቀጥለዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1969 1,225 የሚሆኑ የማኛ ካርታን ህጎችን ከአንቀጽ 1፣ 9፣ 29 በስተቀር ሁሉንም በሚባል መልኩ ተፈጻሚነት እንዳይኖራቸው ሽሯቸዋል፡፡ እንደዚሁም እ.ኤ.አ በ1998 በተዘጋጀው የሰብአዊ መብት ድንጋጌ ተተክተዋል፡፡
የማግና ካርታ ትሩፋት በእኔ ዕይታ፣
የበቁ ልሂቃን፣ የሕግ ባለሙያዎች፣ ዳኞች እና ሌሎችም እንደዚሁ ለ800 ዓመታት ያህል ስለማግና ካርታ የሕግ ሰነድ ጠቃሚነት እና አስፈላጊነት ላይ ክርክር ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ፡፡ የማግና ካርታ የሕግ ሰነድ ለእንግሊዝ ህዝብ ወይም ደግሞ ለነጻው ተራ ህዝብ ፍትህን እና ፍትሀዊ ዳኝነትን አጎናጽፏን? ለመሬት ከበርቴ ጌቶቻቸው አቤቱታ ሲያቀርቡ ለነበሩት ነጻ ላልሆኑት ገበሬዎች የሕግ ሰነዱ ጠቃሚነት ነበረውን? የማግና ካርታ ሕግ በሕግ አግባብ በዳኝነት የመታየት መብታቸውን አጎናጽፏቸው ነበርን? የማግና ካርታ ሕግ የሕግ የበላይነትን መርሆዎች በማጠናከር የሕግ የበላይነትን አስገኝቶ ነበርን? ሰነዱ የሕግ የበላይነትን ተቋማዊ ይዘት እንዲኖረው አድርጎ ነበርን? በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመንግስት እና በዜጎች መካክል የሕገ መንግስት ማዕቀፍ (የማህበረሰብ ስምምነት) ስምምነት እንዲኖር አስችሎ ነበርን? ያ የሕግ ሰነድ የግለሰብ ነጻነቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ አስችሏልን? በሀገሪቱ ግዛት ውስጥ ያሉት ማለትም ንጉሶች እና ንጉሳዊ ቤተሰቦች፣ ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ ፕሬዚዳንቶች፣ የምክር ቤት/ኮንግረስ አባላት፣ የሕዝብ ተወካዮችን፣ ወዘተ… ጨምሮ በሀገሪቱ ባለው የሕጎች ሁሉ የበላይ በሆነው ሕገ መንግስት እንዲገዙ የሚያስችሉት የሕግ መርሆዎች ተቋማዊ እንዲሆኑ አስችሏልን?
በዚህ ጉዳይ ላይ ምሁራን የማይስማሙበት ቢሆንም የማግና ካርታ የሕግ ሰነድ ለአሜሪካ ሕገ መንግስት አርቃቂዎች (1787) እንደ ዋና እርሾ ሆኖ ያገለገለ ከመሆኑም በላይ እንደዚሁም የሰብአዊ መብት ደንጋጌ [አስርቱ ትዕዛዛት] በ(1791) ሲረቀቁ በግብዓትነት በማገልገል የመንግስትን ስልጣን በዘፈቀደ ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀም እንዳይቻል በማድረጉ ሁኔታ ጉልህ ድርሻን አበርክቷል፡፡ ከአፍጋኒስታን እስከ ዙምባብዌ ሁሉም ሀገሮች በሚባል መልኩ እ.ኤ.አ በ1948 በተፈረመው የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ድንጋጌ/Universal Declaration of Human Rights (UDHR) ሰነድ ላይ የማኛ ካርታ አሻራ እና መንፈስ ተንጸባርቆበታል፡፡ ኤሎኖር ሩዝቬልት የUDHRን ሰነድ አርቃቂ ኮሚቴ በሚመሩበት ጊዜ ለሁሉም ህዝቦች እና ሀገሮች አንድ ዓይነት መስፈርትን በማዘጋጀት እኩልነትን፣ ክብርን እና መብትን በመተግበር ስኬትን መጎናጸፍ እንደሚቻል ወይዘሮ ሩዝቬልት ህልም ታይቷቸው ነበር፡፡ ከእርሳቸው ጋር እኔም እስማማለሁ፡፡ የኢትዮጵያ መብቶች፣ የአሜሪካ መብቶች፣ የእንግሊዝ መብቶች፣ የቻይና መብቶች፣ የግብጽ መብቶች… በሚለው ነገር ላይ ፍጹም አልስማማም…የሰብአዊ መብቶች አሉ በሚለው ላይ ብቻ እምነት አለኝ፡፡
ለእኔ በሙሉ ልብ እና በጽናት ከቆመ የኢትዮ-አሜሪካዊ የሕገ መንግስት የሕግ ባለሙያ እና ልሂቅ ማግና ካርታ ከፍተኛ የሆነ አንጸባራቂ አሻራ አለው የሚል አምነት አለኝ፡፡ ማግና ካርታ የመንግስት ተጠያቂነት እና ግልጸኝነት ለሚሉት ለሁለቱ መንታ መርሆዎች ተግራዊነት በጣም አስፈላጊ የሆነ የሕግ ስርዓት ያለው ሰነድ እንደሆነ ግንዛቤ አለኝ፡፡ ስልጣንን የያዙ ኃይሎች ለሚፈጽሟቸው ጉድለቶች እና ህጸጾች በሀገሪቱ ባለው የሕጎች ሁሉ የበላይ በሆነው ሕገ መንግስት ተጠያቂ መሆን አለባቸው፡፡ በገዥዎች እና በተገዥዎች መካከል ባለው ግንኙነት በተወሰኑ የሕግ ማዕቀፎች የሚቀነበብ ነው፡፡ ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ መልኩ ማንም በስልጣን ላይ ያለ ባለስልጣን የዜጎችን ህይወት ሊያጠፋ ወይም ደግሞ ንብረት ሊወርስ አይችልም፡፡ ስልጣናቸውን በዘፈቀደ በመጠቀም የዜጎችን ሰብአዊ መብት ለመደፍጠጥ እና የግለሰብ ነጻነቶችን ከአደጋ ለመጠበቅ እና ስልጣናቸውን በመጠቀም በሙስና የበከቱትን ባለስልጣኖች ከመቅጽበት ከስልጣናቸው ለማስወገድ እና በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረጉ ረገድ የማኛ ካርታ ሕግ በታሪክ የመጀመሪያው ሕግ እንደሆነ አምናለሁ፡፡
በ19ኛው ክፍለ ዘመን በተለያዩ 4 አጋጣሚዎች የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ዊሊያም ግላንድስተን የማግና ካርታን ህግ በማስመልከት እንዲህ የሚል ምልከታን አድርገው ነበር፣ “የእንግሊዝ ሕገ መንግስት ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ከተመሰረተ ተራማጅ ታሪክ ማህጸን ውስጥ አድጎ እና ዳብሮ እንደተገኘ ሁሉ የአሜሪካ ህገ መንግስትም እጅግ በጣም የሚደንቅ እና በአንድ ወቅት ጭንቅላት ባለቸው ሰዎች ለህዝቡ ጠቀሜታ ሲባል ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እገነዘባለሁ፡፡“
እንደዚሁም ሁሉ እንከን ያለበትን ሕገ መንግስት አይነ ስውር የሆነውን ወደ ባርነት የቀየረውን ሕገ መንግስት ያረቀቀው እና ወደ ተግባር እንዲገባ ያደረገውም ልዩ የሆነው የሰው ልጅ ጭንቅላት እንደሆነ የሚያጠራጥር ጉዳይ አይደለም፡፡
ነጻነት የሚለው የእኔ አመለካከት በጣም ቀላል የሆነ ነገር ነው፡፡ ነጻነት መንግስት ከመፈጠሩ በፊት የነበረ መሆኑን አምናለሁ፡፡ መንግስት መብቶችን እና ነጻነቶችን ለዜጎች ይሰጣል የሚል እምነት የለኝም፡፡ መንግስት እራሱ የሰዎች ስብስብ እንደመሆኑ መጠን ዋና ስራውም የህዝቦችን፣ ህይወት፣ ነጻነት እና ንብረቶችን ለመጠበቅ ብቻ ሲባል የሚኖር ነው፡፡
በመንግስት እና በዜጎች መካከል ያለውን ግንኙነት ለመግለጽ የሆነ የአገላለጽ ዘዴን በመጠቀም ሀሳቤን ለመግለጽ ሞክሪያለሁ፡፡ መንግስት ጌቶቹ ለሆኑት ለህዝቦች እንደጠባቂ ውሻ እንደሆነ አድርጌ እገነዘባለሁ፡፡ (የወንዶችን እና የሴቶችን ምርጥ ጓደኛ የሆነውን አካል በዚህ ምሳሌዬ ላይ ከተገለጸው እንስሳ ጋር በማመሳሰሌ ቅር አሰኝቸ ከሆነ ይቅርታ እንድታደርጉልኝ እጠይቃለሁ፡፡) የዚህ የጠባቂ ውሻ ብቸኛው ስራው የአለቆቹን ህይወት፣ ነጻነት እና ንብረቶች መጠበቅ ነው፡፡ ይህ ጠባቂ ውሻ በተፈጥሮው ከዳተኛ ወይም ደግሞ ለመክዳት የሚያስችል ባህሪ የተጠናወተው ስለሆነ በአለቆቹ የጭልፊት ዓይን እና አይነ ቁራኛ በአንክሮ ተመልካች ጌቶቹ ሁልጊዜ መታየት እና መጠበቅ አለበት፡፡ ይህ ጠባቂ ውሻ በአጭር ገመድ ተይዞ በተወሰነ ቦታ ላይ ብቻ እንዲቀሳቀስ ካልተገደደ በስተቀር በተፈጥሮ የተወረሰ፣ ሊቀየር እና ሊወገድ የማይችል የተፈጥሮ ባህሪን የተላበሰ ሁሉንም አካባቢ ካልዞርኩ እና ካልተቆጣጠርኩ የሚል ከንቱ ባህሪ አለው፡፡ በመንግስት የውሻ ጠባቂነት ሕገ መንግስቱ ማሰሪያ ገመድ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ማሰሪያው ሰንሰለት ካጠረ ለውሻ ጌቶች ደህንነት እና አስተማማኝነት መልካም ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ ይህንን ጉዳይ በማስመልከት ቶማስ ጃፈርሰን እንዲህ የሚል ምልከታን አድርገው ነበር፣ “መንግስት ህዝቡን መፍራት ሲጀምር ነጻነት አለ ማለት ነው፡፡ ህዝቡ መንግስትን መፍራት ሲጀምር አምባገነንነት ተንሰራፍቷል ማለት ነው፡፡“ መንግስት የሚኖረው ህዝቡን ለማገልገል እንጅ ሌላውን ተቃራኒውን ሁኔታ ለመፈጸም አይደለም፡፡ የውሻው ጌቶች በምንም ዓይነት ሁኔታ ውሻውን መፍራት የለባቸውም፡፡
ለዚህም ነው ሁሉም የመንግስት ባለስልጣኖች፣ መሪዎች፣ ተቋማት እና ማንም ስልጣኑን የሚተገብር ሰው ሁሉ የሀገሪቱ የሕጎች ሁሉ የበላይ በሆነው ሕገ መንግስት ገመድ መታሰር እና ለሚሰራቸው ስራዎች እና ለሚፈጽማቸው ግድፈቶች እና ጉድፎች ሁሉ ተጠያቂ መሆን  አለበት የሚባለው፡፡ ያ የሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነው ሕገ መንግስት ሌላ ምንም ሳይሆን ዜጎች በዘፈቀደ ከህግ እግባብ ውጭ ህይወታቸውን እንዳያጡ፣ ስልጣንን በተቆናጠጡ ሰዎች እንዝህላልነት ነጻነታቸውን እንዳይገፈፉ እና ንብረታቸውን ከህግ አግባብ ውጭ እንዳያጡ የሚከላከለው ሕገ መንግስት ነው፡፡ የአሜሪካንን ሕገ መንግስት ካረቀቁት ታላላቅ ሰዎቸ መካከል አንዱ የሆኑት እና የታወቁት ጀምስ ማዲሰን በአንድ ወቅት እንዲህ የሚል ጽሁፍ አስፍረው ነበር፣ “ሰዎች መላዕክት ቢሆኑ ኖሮ ምንም ዓይነት መንግስት የሚባል ነገር አስፈላጊ አይሆንም ነበር፡፡“ እኔ ደግሞ እዲህ እላለሁ፣ መንግስት ወደ ከፋ እና ሰይጣናዊ ባህሪ ወዳለው አካልነት ባይቀየር ኖሮ የሰው ልጆች የተቻላቸውን ያህል የደግነት ባህሪያት ጥረትን በማድረግ ወደ መላዕክትነት ለመቀየር ከፍተኛ የሆነ ፍላጎትን ያሳዩ ነበር፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ሁለተኛው ፕሬዚዳንት ከነበሩት ከጆን አዳምስ ጋር እንዲህ ከሚለው ምልከታቸው ጋር በሙሉ ልብ እስማማለሁ፣ “ከሁሉም ወንዶች እና ሴቶች ጋ ታላቅ አደጋ አለ፡፡ ብቸኛው የነጻ መንግስት ህግ በስልጣን ላያ ያለ ማንም ወንድ ወይም ሴት የህዝብን ነጻነት አደጋ ላይ የሚጥል ስለሆነ እምነት ሊጣልበት አይችልም፡፡“
ፕሬዚዳንት ዊት. ዲ.ኢሰንሀወር እንዲህ የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር፣ “የሕግ የበላይነት ዕለት በዕለት ህይወታችን ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ በጣም ቀላሉ እና ግልጽ የሆነው መንገድ የህግ የበላይነት ባይኖር ኖር ሊሆን የሚችለውን ነገር ማስታወስ መቻል ነው፡፡“ እኒህ ታላቅ ሰው ይህንን ሲሉ በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ አህጉር እየተደረገ ያለውን ዕጣ ፈንታ አስቀድመው እየነገሩን ነበር ማለት ነውን?
እ.ኤ.አ ሀምሌ 28/2014 ፕሬዚዳንት ኦባማ ለወጣት የአፍሪካ መሪዎች በአንድ ከተማ ላይ በተደረገ ስብሰባ እንዲህ ብለዋቸው ነበር፣ “አንድ ሀገር የፈለገውን ያህል የተፈጥሮ ሀብት ይኑራትም አይኑራትም፣ እንዲሁም የፈለገውን ያህል የተማረ ሰው ይኑራትም አይኑራትም የሕግ የባላይነት መሰረታዊ ስርዓት ከሌለ የሲቪል እና የሰብአዊ መብቶች የማይከበሩ ከሆነ፣ ለህዝቡ ግልጽነትን በተላበሰ መልኩ በፖለቲካ እንቅስቃሴ ህይወት ውስጥ ያለምንም ተጽዕኖ ተንቀሳቀስው የፈለጉትን ነገር ለማድረግ ታማዕኒነት እና ህጋዊ የሆነ የአሰራር ሂደት ከሌለ፣ መሰረታዊ የሆኑት የመናገር እና የመደራጀት መብቶች የማይከበሩ ከሆነ… አንድ ሀገር በስኬት ጎዳ ላይ ትራመዳለች ማለት እጅግ በጣም የመነመነ አስተሳሰብ ነው፡፡“
ኢትዮጵያ እንደሀገር እና እንደ ህዝብ ስኬታማ መሆን አለባት፡፡ አፍሪካ እንደ አህጉር ስኬታማ መሆን አለባት፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ የጨነገፈ መንግስት ለመሆን በመጨረሻው ጠርዝ ላይ ትገኛለች፡፡ ያለ ምዕራቡ ዓለም እርዳታ እና ብድር አንድም የአፍሪካ ሀገር አይደለም ለሳምንታት ለቀናት እንኳ መቆየት ሳይችል ፍርክስክሱ ሊወጣ እንደሚችል ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያሉት የአፍሪካ ገዥዎች ህልውናቸው አለ ምክንያቱም ኪሳቸው በምዕራብ ሀገሮች ግብር ከፋዮች ዶላሮች ስለሚታጨቅላቸው ብቻ ነው፡፡ ይኸ ነው እንግዲህ ለመዋጥ በጣም የመረረ ክኒን እየሆነ ያለው!
ባለፉት አምስት ዓመታት የታማኝነት አለመኖር እና ጨለምተኛ በመሆን በአፍሪካ የህግ የበላይነት እና ወደ የብዘሁን ፓርቲ ፖለቲካ ሰላማዊ ሽግግር በማድረግ ዴሞክራሲ ይገነባል የሚለው ተስፋዬ እና ህልሜ እየተሟጠጠ ሄዷል፡፡ በየዕለቱ እራሴን እንዲህ እያልኩ በመጠየቅ ላይ እገኛለሁ፣ “የአፍሪካ ተስፋ ሊኖራት ይችላልን?“ ኢትዮጵያስ? የአፍሪካ ዕጣ ፈንታ በተስፋ መለምለም እና በተስፋ መመናመን መካከል ተንጠልጥሎ በመዋዠቅ ላይ ይገኛልን? ወደፊት ሊደረጉ በሚችሉት የእርስ በእርስ ጦርነቶች፣ የዘር ማጥፋት እኩይ ምግባሮች፣ የስርዓተ አልበኝነት ሁኔታ፣ ህገወጥ እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች አፍሪካ ልትወገዝ ትችላለችን? የአፍሪካ ብሩህ ተስፋ ተንጠልጥሎ ያለው በብዙሀን ሀገሮች ብድር እርዳታ ላይ ነውን? አፍሪካ እየተቆለለባት ባለው የዕዳ ተራራ ምክንያት የውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች በታደሙበት ከዓለም አቀፉ የዕዳ ቁልል ተራራ ስር ልትቀበር ትችል ይሆን? አፍሪካ ለቀሪው ዓለም የተመጽዋችነት፣ የሀዘን እና የትካዜ ማዕከል የመጥፎ ተምሳሌት ሆና ልትቀጥል ትችላለችን? አፍሪካ ችግር እና ምስቅልቅል ያለ ተስፋ በተንሰራፋበት ባህር ውስጥ ተንሳፍፋ ወይስ ደግሞ በተስፋየለሽነት ከውቅያኑ ውስጥ ሰምጣ ትጠፋለች? በአፍሪካ ባህሪ፣ በአፍሪካ አመክኖያዊ አዕምሮ፣ መንፈስ እና በአፍሪካ እርባናየለሽ ትረካ ይህም አፍሪካን ወደ መጥፎ 3 ነገሮች የሚያመራውን ማለትም ጨካኝነት፣ አምባገነንነት እና በሙስና ላይ የተደበቀ ነገር ይኖራልን? አፍሪካ ከዳንቴ ሰይጣናዊ የመድረክ ላይ የአስቂኝ ትወና ደረጃ ላይ ደርሳለችን? በአፍሪካ የምትኖሩ ሁሉ ተስፋችሁ ተሟጧል እና ተውት ማለት ነው ፡፡
የማግና ካርታን በዓል በደስታ በማክበሬ ምክንያት ጥያቄ የሚያነሱ እና ከዚያም ባለፈ ትችትን የሚያቀርቡ ከአንባቢዎቸ መካከል ጥቂት ሊኖሩ እንደሚችሉ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ከሁሉም በላይ የነጮች ሰነድ ነው (እውነቱን መናገር አለብኝ!) የጭራቆቹ ቅኝ ገዥዎቹ እና የሌሎቸም የመሰረት ሰነድ ነው፡፡ የማግና ካርታ ሰነድ ለጥቁሮች፣ ለቡናማዎቹ፣ ለብጫዎቹ እና አዎ ለአረንጓዴዎቹ ህዝቦች ጠቃሚነት ሊኖረው አይችልም፡፡ ከአረንጓዴ ህዝቦች በስተቀር ሌሎቹ የየእራሳቸውን ሕገ መንግስቶች እንዲመለከቱ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ በአቧራ በተጀቦነው ሕገ መንግስታቸው ውስጥ የሰው ልጆች ነጻነቶች መሰረታቸው ከየት እንደሆነ ልጠይቃቸው እፈልጋለሁ፡፡ ከነጻነት መብቶቻቸው ውስጥ  የትኞቹ ለመንግስቶቻቸው ሰለባ እንደሆኑ ለማወቅ በጣም ደስ ይለኛል፡፡
ኤሊ ዊሰል እንዲህ ብለው ነበር፣ “በእርግጠኝነት ማንም ሰው ቢሆን ያለ ሕልም ሊኖር አይችልም፣ እንዲሁም ካለ ተስፋ ሊኖር አይችልም፡፡ ሕልሞች ያለፈውን የሚያንጸባርቁ ከሆነ ተስፋ ደግሞ የወደፊቱን ያመላክታል፡፡” ስለሆነም ስለ ተስፋ መንገድ ለማለም ምርጫ አድርጊያለሁ – ነጻነትን፣ ፍትህ እና እኩልነትን ለማራመድ እንዲቻል ብቃት ባለው እና ነጻ የሆነ የዳኝነት ስርዓት እና የህግ የበላይነት መኖር– ከኢትዮጵያ እና ከአፍሪካ አህጉር የተስፋ መቁረጥ ስሜትን ማስወገድ ተገቢ ጉዳይ ነው፡፡
በመላ አህጉሪቱ ውስጥ የአምባገነንነት እና የግፈኞች የጨቋኝነት ደመና በየቦታው አጥልቶ ባለበት በአሁኑ ጊዜ ያሉትን ተስፋ እና ህልሞች ማሳካት ቀላል የሚሆን አይደለም፡፡ የዚህ ዓይነት የሀዘን ድባብ  በተንሰራፋበት ስሜት ነው እንግዲህ እንዲህ የሚሉትን የሄንሪ ፍራንስን የግጥም ስንኞች ማስታወስ ተገቢ የሚሆነው፡፡
ለውስን ዓመታት ለምንቆየው መሬት፣
እርስ በርስ ተባልተን ተቧጭቀን በሀሜት፣
ገሀነምን ሰርዞ ለመግባት ከገነት፣
በማጭበርበር መኖር በሸፍጥ በሀሰት፣
ይህችን ከሀዲ ዓለም እንዴት እናድናት?
የምጻት ቀን ደርሷል፣
ማዕበሉ ይነጉዳል፣
ወዠቦው ይጥላል፣
እሳቱ ያጋያል፣
ግፈኞችን ሁሉ ጥርግርግ ያደርጋል፡፡
ያልዘሩትን ሰብል በሸፍጥ ለማጨድ፣
አቀበቱን ወርዶ ከማሳው በመሄድ፣
ሀ ብሎ ለማጨድ እጆችን በመስደድ፣
የእርሱ ያልሆነውን የሌላ ለመውሰድ፣
በሰማይም ግፍ ነው አምላክም አይፈቅድ፣
በምድራዊም ዓለም በሰው አይወደድ፡፡
የመሬት ደስታ ቀስ ብሎ ይጠፋል፣
ዝናዋ ኮስምኖ አቅሟ ይዳሽቃል፡፡
ለውጥ እና መበሰበስ ሁለቱም ባንድ ላይ፣
ሰምና ወርቅ ሆነው ፍጹም ባደባባይ፣
እኔ እጥል እኔ እጥል ሁለቱም ሲላፉ፤
አንደኛው ለበጎ ሌላኛው ለክፉ፣
ምንም ባልጠበቁት ወድቀውት አረፉ፡፡
የለውጡ ሐዋርያ የዕድገቱ መሀንዲስ፣
ብስባሽን ቀብሮ መንፈስን የሚያድስ፣
ሀገርን ከካንሰር ከደዌ እሚፈውስ፣
የለውጥ ተሟጋች በህዝብ እሚወደስ፣
እኮ እሱ ማን ይሆን የልብን የሚያደርስ?
ትዕዛዝን ተከተል አርማህንም አንሳ፣
መስዋት ሁን ላገርህ ወድቃ እስክትነሳ፣
ታገል ላህጉርህ ለህይወት ሳትሳሳ፣
ዓለምን ለውጣት ቃልህን ሳትረሳ፡፡
በማግና ካርታ አስደሳች ትችት ላይ የሀዘን ስሜትን በሚያንጸባርቅ መልኩ እደዚህ ባለ ሁኔታ ላይ በመደምደሜ የተከበሩ አንባቢዎቼን ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡
ከ800 ዓመታት በፊት የተጻፈውን የእንግሊዝ የነጻነት ሕገ መንግስት በአሁኑ ጊዜ እንኳ ህግ ያልሆነውን በነጻ ማክበር በመቻሌ እና ከ20 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ነጻነት፣ ፍትህ እና እኩልነትን ለማጎናጸፍ በሚል ተረቅቆ የጸደቀውን ሕገ መንግስት ለማክበር አለመቻሌ እንቆቅልሽ የሆነብኝ እና በጣም ያዘንኩበት የቆዘምኩበት ሁኔታ ነው፡፡ ምክንያቱም በኢትዮጵያ ተረቅቆ ጸደቀ የተባለው ሕገ መንግስት ወረቀቱ የተጻፈበትን ዋጋ እንኳ ሊያወጣ አይችልም፡!
የኢትዮጵያን የማግና ካርታ የሕግ ሰነድ የማዘጋጃ ጊዜው አሁን ነው!!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
የካቲት 24 ቀን 2007 ዓ.ም
Source: addisvoice

ኢትዮጵያዊያንና ትግላችን፤ ( ትግሉ ወደፊት እንዲሄድ ምን ማድረግ አለብን? )

ኢትዮጵያዊያንና ትግላችን፤ 
( ትግሉ ወደፊት እንዲሄድ ምን ማድረግ አለብን? )
እስከመቼ ቅፅ ፲፯ ቁጥር ፲፯
አንዱ ዓለም ተፈራ
መስከረም ፲፭ ቀን ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህረት ( 9/25/2014 )
በስታቲስቲክስ የተደገፈ የጥናትና ምርምር ዘገባ ማቅረብ ባልችልም፤ ባካባቢዬ ያለውን ሀቅ ተከታትዬ የሚኖረኝ ግንዛቤ፤ መንገዱኝ ይከፍትልኛል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ፍላጎት ሰብስቤ፤ ይሄ ነው ብዬ የማቀርበው የጥናት ዘገባ የለኝም። ውጪሰው ኢትዮጵያዊያን ስለሚፈልጉት ወይንም ስለሚያደርጉት ተጨባጭ ማስረጃ ያጠራቀምኩት ዝርዝር የለኝም። ነገር ግን፤ በመጀመሪያ እኔ ራሴ የውጪሰው ኢትዮጵያዊያን አካል በመሆኔ፤ በዙሪያዬ ከምገናኛቸው እንደኔው የውጪሰው ኢትዮጵያዊያን ጋር ስለሀገራችን ሁኔታ እወያያለሁ። ለጥቆም በየድረ ገጹ የሚጻፈውን አነባለሁ። ባጠቃላይ በማንኛውም የዜና መለዋወጫ መንገዶች ሁሉ የሚካሄደውን የሀገሬ ጉዳይ ሳላሰልስ በቀን ሳይሆን በየሰዓቱ ማለት በሚቻልበት ሁኔታ እከታተላለሁ። ከሞላ ጎደል ሁላችን በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሀቅ መለወጥ እንዳለበት እናምናለን። ከዚያ አልፎ እያንዳንዳችን ለዚህ ለውጥ ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት እንዳለብን እናምናለን። እናም ዝግጁ ነን። ታዲያ እንዴት አድርገን ነው ይኼን ኃላፊነት፣ ፍላጎትና ዝግጁነት፤ በትክክለኛና በተሰባሰበ የአንድነት መንገድ ለትግሉ እንዲሠለፍ የምናደርገው?
በተከታታይ፤ ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ በሀገራችን ያለው ምን ዓይነት መንግሥት እንደሆነና ምን ዓይነት ትግል እንደሚያስፈልገን በዚሁ ብሎግ አስፍሬያለሁ። በዚህ ጽሑፍ ደግሞ የሚከተሉትን በቅደም ተከተል የማቀርባቸው ነጥቦች፤ ሀ) ይህ የወራሪ መንግሥት ሀገራችንንና ሥልጣኑን ወዶ እንደማይለቅ፤ ለ) ከዚህ መንግሥት ጋር የሚደረገውን ትግል፤ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያዊነት ብቻ ለስኬት እንደሚያበቃው፤ ሐ) ትግሉ በአንድ ማዕከል መመራት እንዳለበት፤ መ) ትግሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ የነፃነት ንቅናቄ እንደሆነ፤ ሠ) ትግሉ የግድ የሰላም ትግል እንደሆነ እና ረ) አሁን የተያዘው አወቃቀሩ የተሣሣተ የድርጅቶች መንገድ መሰረዝ እንዳለበት በመዘርዘር፤ ምን ማድረግ እንዳለብን አመላክታለሁ።
ሀ) ይህ የወራሪ መንግሥት ሀገራችን እና ሥልጣኑን ወዶ አይለቅም።
አንዳንዶች፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወራሪውን መንግሥት ስለማይወደው፤ “በምርጫ አቸንፈነው ሥልጣኑን ይለቃል”፤ ብለው ያምናሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ወራሪውን መንግሥት ስለማይወደው የሚለው፤ ትክክል ነው። ቀጥሎ ያሉት ሁለት ነጥቦች ግን አጠያያቂ ናቸው። በመጀመሪያ በምርጫ አቸንፈነው! የሚለውን እንመልከት። ምርጫን ማቸነፍ የሚቻለው፤ ትክክለኛ የሕዝብ ወኪልነትን ለማግኘት ትክክለኛ መፍትሔ መያዝ ቅድሚያ ያለው ሆኖ፤ ትክክለኛ የምርጫ ቅንብርና አስተማማኝ የአመራረጥ ሂደት ሲኖር ነው። የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በምንም መንገድ ትክክለኛ የምርጫ ቅንብር እንዲኖር አይፈልግም። እንዳልነው ሕዝቡ አይወደውምና! ምርጫ የሰላም የፖለቲካ ትግልን መሠረት ያደረገ ነው። ለዚህ ደግሞ፤ መንግሥቱ የኢትዮጵያ ሆኖ፤ የሚያስተማምን ሕጋዊ መንገድ ሲኖር ነው። ይኼ የለም።
ሰላማዊ ትግልን በተመለከተ፣ ያልተስተካከሉ ሁለት አፅናፋዊ አመለካከቶች አሉ። የመጀመሪያው “ሰላማዊ ትግል አይሠራም!” ብሎ አጠቃሎ የሚኮንነው ክፍል ነው። ሌላው ደግሞ “ሰላማዊ ትግሉን እንደ እንቁላል ተሽቆጥቁጦ አቅፎ መጓዙ!”ን ያመነበት ክፍል ነው። ሰላማዊ ትግል፤ በነዚህ መካከል ነው በተግባር የሚካሄደው። ሰላማዊ ትግሉን የሚያምኑ ታጋዮች፤ ባለው ሕገ መንግሥት ተገዝተው ማጌጫ፤ ያንገት ጌጥ የሚሆኑ አይደሉም። ማኀተማ ጋንዲ ወራሪ እንግሊዞችን፤ ፓርላማ እንዲያስገቡት ከምርጫቸው ውድድር አልገባም። በጥቅማቸው ላይ ተነስቶ አመጽ ነው ያካሄደው። እሰሩን እንጂ አናደርግም ብሎ ነው ያመጸው። “የናንተን ጨው ከምንቀበል፤ በእግራችን ረጂም መንገድ ተጉዘን የራሳችን እናገኛለን!” ነው ያሉት። ማርቲን ሉተን ኪንግና አፍሪቃዊ አሜሪካዊያን ሰላማዊ ታጋዮች ለሚያደርጉት ሰላማዊ ሰልፍ፤ ፕሬዘዳንቱና አቃቤው “እባካችሁ ታገሱን፤ እስካሁን ያገኘነውን ድል ያስተጓጉልብናል!” ሲሉ፤ “ያ የናንተ ጉዳይ ነው። ለኛ ከነፃነታችን የበለጠ የናንተን አቋም አክብደን ቦታ አንሠጠውም!” በማለት ሰልፋቸውን ቀጠሉ።
ሰላማዊ ታጋዮች እንግዲህ ዋና ዓላማቸውን ለማግኘት፤ የሚከፈለውን መስዋዕትነት እያወቁ፤ እምቢታን ማስቀደማቸው ነው ትግሉ። ይህ ወራሪ መንግሥት ነው። በሱ ፓርላማ መግባትና አለመግባት፣ በዚህ ምርጫ ቁጥር ማግኘትና አለማግኘት፤ ዋጋ እንደሌለው ታሪኩ አስተምሮናል። ይህ ወራሪ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ ምንም ዓይነት የመግባባትና አብሮ ነገሮችን የመመልከት አእምሮ የለውም። ስለዚህ የምርጫ ጉዳይ ለሱ ጌጥ ከመሆን ሌላ ምንም ትርጉም የለውም።
ወራሪው መንግሥት የፈለገውን ገደብ ቢያደርግም፤ የሕዝቡ ታጋይ ክፍል ባንድነት የሚነሳበትን መንገድ ማበጀት አለብን። ለሕዝቡ የሚቀርቡት ምርጫዎች፤ ወራሪው በሚያዘጋጃቸው የሱ መደነቂያ መድረኮች ሳይሆኑ፤ ታጋዩ ክፍል በሚያዘጋጃቸው የራሱ መድረኮች መሆን አለባቸው። የራሱ መድረኮች በሙሉ ለራሱ የተዘጋጁ ናቸው። እኒህን ማስወገድና ከኒህ መራቅ አለብን። በታጋዩ ክፍል ለሕዝቡ የሚቀርቡት፤ ኢትዮጵያዊነት ወይንም የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ብቻ መሆን አለባቸው። በዚህ ታጋዩ ራሱ በሚያዘጋጀው ምርጫ፤ ወገን ይለያል። አንድም ከሕዝቡ ጋር መቆምን፤ አለያም ከወራሪው ጋር መቆምን። ትግሉ በኢትዮጵያዊነት ላይ ብቻ ያተኮረ መሆን አለበት። ይህ እንዳይሆን ወራሪው መንግሥት ሰማይ ይቧጥጣል፣ ይለምናል፣ ያስፈራራል፣ ጦር ይቀስራል፣ የማያደርገው ነገር የለም። እኛም ተመችተንለታል። ስለዚህ ራሳችንን ካላስተካከልን፤ ወደፊት መሄድ አይቻለንም። እናም በምርጫው ለሱ ጃኖ አልባሽ ከመሆን ይልቅ፤ የመውደቂያው አለት ድንጋይ እንዲሆን ማድረግ አለብን። በሱ ድግስ እናቸንፋለን የሚለው ተቀይሮ፤ የምርጫውን ምንነት በማሳወቅ በራሱ ድግስ መውደቂያዉን ለማዘጋጀት እንጣር።
በሌላ በኩል ደግሞ ወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ሥልጣኑን ስለመልቀቁ ነው። ይህ እኮ ወራሪ ነው። ወራሪ በየትኛው ታሪክና ቦታ ነው ወዶ ሥልጣኑን የለቀቀው? ወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግምባር እኮ ሥልጣኑን የሚለቀው፤ መቃብሩ ላይ ሲደርስ ብቻ ነው። እናም በአንድነት እንግፋው። ወዶ ይለቃል ማለታችንን ትተን፤ አስገድደን ለማስለቀቅ ወስነን በተግባሩ እንሰማራ። የምናስገድደው ጦር መዘን ሳይሆን በሕዝብ የአንድነት እምቢታ ነው። ጠመንጃችን እምቢታችን ነው። ይህ ወራሪ ሕግ ያወጣል መልሶ ያፈርሰዋል። የሚያውቀው ቢኖር እሱ ዘለዓለም ገዥ ሆኖ መቀመጥ እንዳለበት ብቻ ነው። ስለዚህ ምንም መያዣ መጨበጫ ስነ ሥርዓት የለውም። እናም በዚህ ወይንም በዚያ የሚለው መንገድ አይሠራም። ራሱ የገነባቸውን ሕጎች የሚያፈርስ መንግሥት፤ ለማናቸውም የሕዝቡ አቤቱታ ፈቱን ሠጥቶ ያስተናግደዋል የሚል፤ ራሱን መመርመር አለበት። የራሱን ሕጎች በማፍረሱ፤ ሕጎችን ማፍረስ ትክክል ነው! እያለ እኮ ነው። ሕዝቡ ለምን የሱን ሕጎች መከተልና ማከበር ይገደዳል? ይህ መንግሥት በምንም መንገድ ሥልጣኑን ወዶ አይለቅም።
አንዶንዶች በውጭ መንግሥታት ተገፍቶ ትክክለኛ ምርጫ ያደርጋል ብለው ያምናሉ። የውጭ መንግሥታት እኮ የቆሙት ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ነው። ለኢትዮጵያዊያን የተመሠረተና የቆመ የውጭ መንግሥት የለም። ወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ሎሌያቸው ሆኖ፤ የነሱን ጥቅም እስካስጠበቀላቸው ድረስ፤ በምንም መንገድ እንዲወግድባቸው አይፈልጉም። እኛኮ ዳር ደንበራችንን እናስከብራለን፣ ለሙን የሀገራችን መሬት ለራሳችን አራሾችና የመሬቱ ባለቤቶች እናስመልሳለን፣ ይህ ወራሪ መንግሥት ያለእውቅናው ያደረጋቸውን ሀገር የማስገንጠል፤ ወደብ የማሳጣት፣ የአባይን ዕድል በሌሎች እጅ የማስገባትና የመሳሰሉትን ዓለም አቀፍ ውሎች ልናፈርስ የተነሳን ነን! ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያዊያን ብለን የተነሳን ነን! እንዴት ብለው እኛን ይደግፉ? ወይንስ የዋህነት ውጦናል? ስለዚህ፤ ለውጭ መንግሥታት አቤቱታ ማቅረባችንን ትተን፤ በአንድነት በመሰባሰብ፤ ጠንካራ ሆነን በመገኘት፤ ወደኛ እንዲመጡና እንዲለምኑን እናደርግ።
አንዳንዶች ዴሞክራሲያዊ አሠራር ሊከተል ይችል ይሆናል ብለው ያምናሉ። ከእባብ እንቁላል እርግብ እንዲፈለፈል እንጠብቃለን ወይ? ምንነቱና የሕልውናው ምሰሶ የሆነውን ፀረ-ኢትዮጵያዊነት እንዴት አድርጎ ይገፈዋል? ምኞት ጥሩ ነው። ምኞት ገሃድ ሆኖ በራሱ ይቆማል ብሎ መጠበቅ ግን የዋኅነት ነው። ወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በምንም ተዓምር ዴሞክራሲያዊ አሠራርን ይጎራበታል ማለት ቅዠት ነው። በታሪኩም ሆነ ዛሬ፤ በዛሬው ዕለት በሚያደርገው ተግባር፤ ዴሞክራሲያዊነትን ከአጥሩ ወዲያ በጎሪጥ በጠላትነት የሚያይ ነው። የአዲስ አበባን መሬት እንዳሻው ከሕዝቡ እየነጠቀ ለራሱ ጄኔራሎችና ደጋፊዎች የሠጠ ድርጅት፤ ምን ይከተላል ብሎ ነው ዴሞክራሲያዊ አሠራርን የሚቀበል? ዴሞክራሲን ሊማረውም የማይችለው ጉዳይ ስለሆነ፤ በፀረ-ዴሞክራሲያነቱ እንደዳቆነ በዚያው ቀስሶ ይቀበርበት።
ለ) ይህን ትግል፤ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው ለስኬት የሚያበቃው።
የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመከፋፈልና ይሄንን ክፍፍል ዘለዓለማዊ ለማድረግ፤ የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ያልፈነቀለው ደንጋይ፤ ያልገባበት ጉድጓድ የለም። የዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ ቡድን እምነቱ፤ “ደጋግሜ ካሰቃየኋቸውና ጊዜ ከወሰደ፤ የኔ ፍላጎትና ተግባር ዘለዓለማዊ ሆኖ ይቀመጣል።” ነው። “ኢትዮጵያዊነትን አጥብቀው የሚሟገቱለትን ግለሰቦች በማሰቃየትና ኢትዮጵያዊነትን የሚያጠብቁ ድርጅቶችን መፈናፈኛ በማሣጣት፤ ደፍረው ወደ ኢትዮጵያዊነት የሚመጡትን ቁጥራቸውን እቀንስና፤ ያለትክ የሚያልፉት ሲያልቁ፤ ለኢትዮጵያዊነት ቋሚ አይኖርም።” ብሎ ነው። ይህ መንግሥት ምንም ዓይነት ጠንካራ እምነት በዚህ ላይ ቢኖረውም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነቱን በነጠላው ጫፍ ቋጥሮ የያዛት ዕቃ ሳትሆን፤ በልቡ ውስጥ ያለ የደሙ ቀለም፣ የእምነቱ ማሠሪያ ስለሆነ፤ ሕዝቡ ኢትዮጵያዊነቱን ይዞ፤ ኢትዮጵያዊነት ደግሞ ሕዝቡን ይዞ ይኖራሉ። የሚጠፋው፤ ጊዜ ያበቀለው የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ከነመንግሥቱ ነው።
አሁን በሀገራችን በኢትዮጵያ ያለው የወራሪና የተወራሪ ግዛት ነው። ይህ የዴሞክራሲ ጥያቄ አይደለም። ይህ እኔ በዚህ ተበድያለሁ ብሎ የራስን በደል የሚቆጥሩበት አይደለም። ይህ ርስ በርስ የምንወዳደርበት የቁንጅና ምርጫ ዝግጅት አይደለም። ይህ የወገን ደራሽ የሀገር አዳኝ ትግል ነው። ይህ ትግል እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊና እያንዳንዷን ኢትዮጵያዊት በአንድነት የሚያሰልፍ ትግል ነው። እናም ኢትዮጵያዊነት ነው። ስለዚህ ትግሉ ለድል የሚበቃው መላ ኢትዮጵያዊያን የኔ ብለን አብረን ስንነሳ ነው። ለዚህ ደግሞ የሁላችን ፍላጎትና እምነት የያዘ የትግል ራዕይ መቀመር አለበት። ባሁኑ ሰዓት ይህ ራዕይ አራት የትግሉ ዕሴቶችን ያካተተ ይሆናል።
አንደኛ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ መሆኑንና ሉዓላዊነቱን መቀበል ነው።
ሁለተኛ፤ የኢትዮጵያን አንድ ሀገር እና አንድ ብሔር መሆን መቀበል ነው።
ሶስተኛ፤ የየአንዳንዱ/ዷ/ን ኢትዮጵያዊ/ት/ የግለሰብ ዴሞክራሲያዊ መብት መከበር መቀበል ነው።
አራተኛ፤ በሀገራችን በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነትን መስፈን መቀበል ነው።
እኒህ ናቸው ሁላችን የምንጋራቸው አሁን የኢትዮጵያ መታገያ ዕሴቶቻችን።
ሐ) ይህ ትግል በአንድ ማዕከል መመራት አለበት።
አሁን በፊታችን የተዘረጋው አንድ ትግል ነው። አሁን ሀገራችን ኢትዮጵያን ወጥሮ የያዛት፤ ወራሪው መንግሥት በሕዝቡ ላይ የሚያደርገው በደል ነው። በዚህ በደል የሚማቅቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ በትግል ላይ ነው። ይህ ትግል በኢትዮጵያ ሕዝብና በወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መካከል ያለ ትንቅንቅ ነው። ትግሉ፤ ሕዝቡ ነፃ ለመውጣት፤ ወራሪው የፈለገውን በሕዝቡና በሀገሩ፣ በሕዝቡ ነፃነትና በሕዝቡ እምነት ላይ የሚያላግጥበትን ሁኔታ ለመቀጠል፤ እያደርጉ ያሉት ግብግብ ነው። ስለዚህ ያለው የትግል ሠፈር፤ ሁለት ብቻ ነው። አንዱ የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ሠፈር ሲሆን፤ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሠፈር ነው። እናም ትግሉ አንድና አንድ አጥር ብቻ ነው ያለው። የሚቻለው አንድም ከአጥሩ ወዲህ ሆኖ ከሕዝቡ ጋር መቆም ነው፤ አለያም ከአጥሩ ወዲያ ሆኖ ከወራሪው ጋር መቆም ነው።
ይህ በግልፅ የሚያሳየው የዚህ የወራሪ መንግሥት ጠላትና ድራሹን አጥፊ፤ ኢትዮጵያዊነት ብቻ መሆኑን ነው። ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ መሣሪያ ነው። ለዚህ የሚያስፈልገው ደግሞ አንድ ማዕከል ነው። ኢትዮጵያዊ ማዕከል። የትግሉ ማጠንጠኛ በሆነው ኢትዮጵያዊነት ዙሪያ አንድ ማዕከል ማበጀት ነው። ይህ ሕዝባዊ ንቅናቄ ብቻ ነው፤ ሕዝቡን ለድል የሚያበቃው። ይህ ማዕከል ነው ትግሉን መምራት ያለበት።
መ) ይህ ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ ንቅናቄ ነው።
የትግሬዎችን ነፃ አውጪ ግንባር ለማጥፋት፤ ድርጅት መመሥረትና መታገሉ አንድ ነገር ነው። መዋቅርና በዚህና በዚያ ማስፋፋቱ አንድ ነገር ነው። ቆም ብሎ፤ እያንዳንዱ የድርጅት አባል፤ ድርጅታችን ከተመሠረተ አንስቶ ምን ሠራን? ከጀመርንበት ነጥብ እስካሁን ምን ያህል ፎቀቅ አልን? ተሳክቶልናል? ወይንስ አልተሳካልንም? አደግን? ወይንስ ደከምን? የዚህ ሂደት ዕድገታችን መመዘኛው ምንድን ነው? ባገኘነው ስኬትስ ጠግበናል ወይ? እያልን መለካት አለብን። በዚህ ምርምራችን ደስተኞች ከሆን መቀጠሉ ተገቢ ነው። ካልተደሰትን ደግሞ፤ አንድም ድርጅቶቻችንን መቀየር አለያም ግባችንን መቀየር ይኖርብናል። አለያ ትግሉን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ተዘጋጅተናል ድርጅታችንም ጌጣችን ነው፤ ማለት ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ጊዜም በሚደርስበት በደል አንገቱን ደፍቶ አልተቀመጠም። በየወቅቱ በደሉን በመቃወም የተለያዩ ትግሎችን አድርጓል። ከነመንግሥቱ፣ ግርማሜ ንዋይና ወርቅነህ ገበየሁ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጀምሮ፤ በተማሪዎች እንቅስቃሴ፤ በየክፍለ ሀገሮች የገበሬዎች መነሳሳትና በየካቲት ፷ ፮ቱ የታየው ሕዝባዊ እምቢታ የዚህ ምስከር ነው። በየጊዜው የተደረጉት መነሳሳቶች በተለያዩ ምክንያቶች ለስኬት አልበቁም። ይኼንን መርምረን ትምህርት መውሰድ አለብን። ሀገራዊ ውይይቶች የተደረጉባቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ያማረ ውጤት ያስከትላሉ። ይሄን ለማድረግ ግን ጥረቶች አልታዩም። ለምን?
አሁንም ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች አሉ። ችግራቸው ምንድን ነው? ብለን አልጠየቅንም። ለምን? ለምሳሌ፤ የእስልምና ተከታይ ወገኖቻችን ለረጅም ጊዜ እየታጋሉ ነው። ይህ እንቅስቃሴያቸው በአብዛኛው የሃይማኖቱ ተከታዮች ዘንድ ተቀባይነት አለው። ታዲያ ለምን ግቡን አልመታም? በተጨማሪ፤ በኤርትራ የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ እናደርጋለን ብለው የተነሱ ብዙ አሉ። እኒህም ለረጅም ጊዜ መግለጫዎችን ሲያወጡ ስምተናል። ለምን ከፍተኛ ደረጃ ላይ አልደረሱም? እንቀጥል። በውጭ ሀገር ያለን ኢትዮጵያዊያን ነፃነት፣ ጊዜ፣ ንብረት፣ ሀገር ወዳድነት፣ ለወገን ተቆርቋሪነት ሞልቶናል። ታዲያ ለምን በአንድነት ተሰልፈን አልተነሳንም? ልጨምርበት። በሀገር ቤት የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች አሉ። ለምን እንቅስቃሴያቸው ወደፊት አልተራመደም? በማዕከላዊነት ደግሞ፤ የየድርጅቶቹ መሪዎችና የትግሉ ልሂቃን፤ ለምን ይሄን ማድረግ እንዳልቻልን ጥናት አድርገን መፍትሔ ለምን አላቀረብም? ይሄ በተደጋጋሚ መታየት ያለበት ጉዳይ ነው።
ለዚህ ሁሉ ጥያቄ መልስ የግድ መኖር አለበት። እንግዲህ ሁሉም በያሉበት ያነሱት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄዎችን ነው። አንዱ ከሌላው የሚለየው፤ በራሳቸው ዙሪያ ብቻ ያለው ላይ ማተኮራቸው ነው። ቁም ነገሩ ግን የያዳንዳቸው ጥያቄዎች የሁሉም ጥያቄዎች ናቸው። የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የጠየቁት የመብት ጥያቄ ነው። መምህራንና ተማሪዎች የጠየቁት ይኼኑ ነው። ነጋዴዎች የጠየቁት መብትና እኩልነትን ነው። ይህ የሁሉም ጥያቄ ነው። ቤት ተከራዮችና ቤት ለመሥራት የተዘጋጁት የጠየቁት መብታቸውን ነው። ይሄ የሁሉ ጥያቄ ነው። በደቡብ የተፈናቀሉት ኢትዮጵያዊያንና በኦጋዴን የሚሰቃዩት ኢትዮጵያዊያን የጠየቁት ኢትዮጵያዊ መብታቸውን ነው። ይህ የሁሉ ጥያቄ ነው። ስለዚህ የጎደለው እኒህን ጥያቄዎች በማያያዝ የሁሉም ማድረግና ሁሉም በአንድ ላይ የሚነሱበትን ማዘጋጀቱ ነው። ሁሉም የመብት፣ የነፃነት፣ የሕግ፣ የእኩልነት ጥያቄዎችን ነው ያነሷቸው። ሁሉም የሁሉም ጥያቄዎች ናቸው። ስለዚህ ሁሉም በአንድ ላይ ሁሉንም ማንገብ ያለባቸው ጥያቄዎች ናቸው። የድርጅት ሚና ይሄን ማድረግ ነው። ድርጅት የራሱን መርኀ-ግብር ብቻ አንግቦ ለራሱ ሥልጣን ማግኛ መንገድ ማስላት ሲይዝ፤ ፉክክር ይነግሳል። በርግጥ ነግሷል። እናም ቁጥር ለማብዣ ያለው እሽቅድድም፤ ዋናው ቁም ነገር ሆኗል። ከዚህ መውጣት አለብን። ይህ ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ መነሳሳት ነው። የሕዝቡ ንቅናቄ ነው።
ሠ) ይህ ትግል የሰላም ትግል ነው።
አሁን ያለንበትን የደበዘዘ የትግል እንቅስቃሴ ሕይወት ሠጥተን ወደፊት ለመጓዝ፤ ማመንና መከተል ያለበን የትግል ቅደም ተከተል ዝርዝር፤ በግልፅ መስፈር አለበት። ነፃነት የመጀመሪያው ነው። ወራሪውን፤ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ማስወገድ አለብን። የተለያዩ ክፍሎች በተለያየ መንገድ በትግሉ ተጠምደዋል። የተለያዩ ድርጅቶች በመድረኩ ተጋግረዋል። በትጥቅ ትግል ላይ “ተሰማርተናል” የሚሉም አሉ። እንግዲህ ማን ከማን ጋር እንደሚታገልና ድሉ በምን እንደሚተረጎም ግራ የተጋባበት ሀቅ በመካከላችን ሰፍኗል። ይህ ትግል ወራሪውን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ማስወገድ ብቻ ሳይሆን፤ ከዚያ ቀጥሎ ለሚመጣው ሥርዓትም ጭምር ነው። ወራሪውን ማስወገድ ብቻ የትግሉ ዋና ማውጠንጠኛ ማድረግ አጓጉል ነው። ከዚያ ቀጥሎ የሚመጣው ሥርዓትም በእኩል ደረጃ መቀመጥ አለበት። አንድን ትግል በሌላ ትግል የመተካት አባዜ በሺታ ነው። ይህ ለኔ ብቻ ብለው በራሳቸው ድርጅት ተጎናንፈው የተቀመጡ ክፍሎች አጀንዳ ነው። ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ አጀንዳ አይደለም። ስለዚህ የዚህ ትግል ባለጉዳዮች መላ ኢትዮጵያዊያን ነን። እናም ትግሉ አሁን ባለበት ደረጃ፤ ሰላማዊ ነው። የትግሉን ተሳታፊዎች መሰባሰብ እና አንድነትን መፍጠር፤ ዋና የቅድሚያ ተግባሩ ነው። ሕዝቡ የትግሉ ባለቤት ነው፣ ሕዝቡ ሉዓላዊነቱ መጠበቅ አለበት፣ ሕዝቡ ትግሉን ይምራ ስንል፤ በአንድነት ሆነን ትግሉን ሁላችን እንቀላቀልበትና የሕዝቡን መብት እናስከብር ማለት ነው። “የኔ ድርጅት ሲያቸንፍ መብቱን ለሕዝቡ እሠጣለሁ።” የሚለው የቁጮ አባባል፤ ትናንት አልፎበታል። የዛሬ ሰዎች ነን። የዚህ ትርጉም፤ በቀጥታ ሲቀመጥ፤ “እኔ ገዥ መሆን እፈልጋለሁን በኔ ሥር ሆናችሁ እኔን ለማንገሥ ታገሉ።” ማለት ነው።
ረ) አወቃቀሩ የተሣሣተው የድርጅቶች መንገድ መሰረዝ አለበት፤
አዎ! ሳይደራጁ ትግል የለም። ጣሊያን ፋሽስቱን የተጋተሩት ጀግኖች አርበኞቻችን፤ በየጎጡና በየመሪያቸው ከመንደር እስከወረዳ፣ ከወረዳ እስከ አውራጃ፣ ከአውራጃ እስከ ንጉሣቸውና ከንጉሣቸው እስከ ንጉሠ ነገሥታቸው ባንድ ሀገር፤ ባንድ መንግሥት ስም ተደራጅተው ነው። በየግሉ የሚደረግ እንቅስቃሴ ለድል አያበቃም። ከራሳችን ከዚህ ታሪክ የምንወስደው ትምህርት፤ ድርጅት ለወቅታዊ ጥያቄው መልስ የሚሆን መሣሪያ ነው። አሁን ደግሞ የሚያስፈልገን መሣሪያ፤ መላ ኢትዮጵያዊያንን በኢትዮጵያዊነት አሰብስቦ፤ በወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ላይ የሚያስነሣና፤ ለድል አብቅቶ የሽግግር መንግሥት የሚያቋቁም ነው። ይህ የሀገር ነፃነትን ለማስገኘት የሚደረግ መደራጀት ነው። ይህ መደራጀት የሚያስከትለው የሽግግር መንግሥት፤ ሕገ መንግሥት ተረቆ የሚጸድቅበት፤ ሕገወጥ በሆነ መንገድ የተደረጉት የወራሪው መንግሥት ዓለም አቀፍም ሆነ የሀገር ውስጥ ውሎችና ሕጎች የሚሰረዙበት፤ የፖለቲካ ድርጅቶች ምዝገባ ተደርጎ፤ እኒህ ድርጅቶች የሚወዳደሩበትና ተቀባይነት የሚያገኘው ወገን ሥልጣኑን የሚያስረክብበት ወቅት ነው።
ለዚህ ሂደት የሚያስፈልገን ኢትዮጵያዊ የሆነ አንድ ሕዝባዊ የነፃነት ንቅናቄ ነው። ይህ ንቅናቄ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ክፍት ነው። “ጉዳዬ ነው” ያለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በግሉ ገብቶ የሚሳተፍበት ንቅናቄ ነው። መደራጀት ለሆነ ተግባር የሚደረግ የሰዎች መሰባሰብ ነው። አሁን በኢትዮጵያ የትግል ምኅዳር፤ ለዚህ ንቅናቄ ተወዳዳሪ ሌላ ድርጅት አይኖርም። ያሁኑ ሰዓት መደራጀት ሀገርን ነፃ አውጥቶ የሕዝቡን የበላይነት ለማስከበር ብቻ ካልሆነ፤ ኢትዮጵያዊም ሕዝባዊም አይደለም። ከዚህ ይልቅ የራሴን ድርጅት ነው የማጠናክረው ብሎ የሚሯሯጥ ድርጅት፤ ከወራሪው የትግሬዎች ነፃ ወጪ ግንባር የተለዬ አጀንዳ የለውም። አሁን ቅድሚያ ቦታ ያዥነት ኖሮኝ፤ ሌሎችን ዘግይተው ሲመጡ አቸንፋለሁ የሚል ድርጅት፤ ከመርኀ ግብሩና ከቆመለት ዓላማ ይልቅ ብልጣ ብልጥነትን የተካነ፤ ድርጅቱን ከሀገሩ ያስቀደመ፤ ግለኛ ድርጅት ነው። ይህ የሕዝብ ወገን አይደለም። ይህ ኢትዮጵያዊ አይደለም። እናም ይኼን የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነት ንቅናቄ በአንድነት እንመሥርተው። ሃሳብ ላለው በeske.meche@yahoo.com እገኛለሁ።

Tedros Adhanom caught in $20 million teen prize scandal .Abebe Gelaw

Government of Australia and Rotary Foundation deny funding teenager
By Abebe Gellaw
(Addis Voice) The Foreign Minister of Ethiopia has been caught in an explosive web of lies with a schoolgirl as the Government of Australia and the Rotary Foundation have denied giving 20 million Australian dollars to a 14-year old teenager, whom the nation’s “top diplomat” publicly praised and endorsed as an “exemplary philanthropist” and claimed her to be the winner of an unnamed “international prize”.
beritu and family 1.jpg
The Ethiopian-Australian girl, Beritu Jaleta Ahmed, claimed last week in a joint press conference with Dr. Tedros Adhanom in his own office that she was ready to build a school in Ethiopia with the 20 million Australian dollars that she won in a student competition held at her school in Melbourne. According to her, the prize money was jointly funded by the Australian Government and the Rotary Club of Australia [sic].
But Baden Powell College’s leadership, who knew nothing about the the competition or the prize, have already referred the matter to Victoria Police for investigation, Addis Voice has learnt. The public school that takes students from prep to 9th grade is dominated by students from immigrant families. It has around 1800 students, 180 staff and 50 volunteers. It gets an annual budget of around 12 million Australian dollars from the coffers of the Victoria Department of Education.
Tedros Adhanom publicly praised the teenager as a unique “role model” among the Ethiopian Diaspora for allocating such a large amount of money for development at such a young age. He commended her philanthropy and pledged that the government of Ethiopia would provide all the necessary support for the completion of the “modern school” project from nursery to secondary school levels that she planned build in Gara Muleta, Eastern Harargie, the birthplace of her father.
The Government of Australia and the Rotary Foundation have distanced themselves from the scheme and told Addis Voice that they have never heard of such a grand prize or the teenage winner of a multi-million dollars school competition. Some members of the Ethiopian community in Melbourne have blamed the girl’s father and the government in getting involved in such a shameful scam that can adversely affect the image of the country.
Jenna Hand, a spokesperson for Australia’s Department of Foreign Affairs and Trade, refuted the teenager’s claim that the Government of Australia gave her half of the prize money. In a written statement emailed to this reporter, the spokesperson said: “The Department of Foreign Affairs and Trade has not given 10 million Australian dollars to fund a school in Gara Muleta, Ethiopia. The Department of Foreign Affairs and Trade supports education in Ethiopia by providing core funding to the Global Partnership for Education. Ethiopia is a recipient of Global Partnership for Education funding,” the official Australian Government statement said.
The Foreign Minister had also maximized the PR “opportunity” by spreading and spinning the news, along with pictures of himself, the girl and her father, Jaleta Ahmed, on Facebook and Twitter. “Beritu Jaleta has done an extraordinary deed that we should all learn from,” he wrote on his Facebook page. Under Australian law any person under the age of eighteen is considered a child.
“I came here to Ethiopia to build a school in Gara Muleta, Harargie. I won a competition of 20 million Australian dollars. So I came here with the Embassy of the government of Ethiopia in Australia to begin my project and the construction and also see the area and the land,” she told journalists, who were not allowed to raise any serious questions during the press the stage managed conference held in the office of the Minister.
Tewolde Mulugeta, a spokesperson of the Ministry of Foreign Affairs, added a spin to the propaganda claiming that she received the award last year for her extraordinary academic performance and proposal to build a school. “She used to participate in various school clubs. One of the clubs was the one she headed in areas of human affairs. While she was working in that club, they were exchanging views regarding the support of people for others,” Tewolde said unconvincingly. “The main thing was that she proposed an idea to create opportunities for others to get education. We have learned that people who have heard the idea arranged the prize for her. This happened nearly one year ago, around 2014,” he claimed nervously without providing any proofs and verification.  official.jpg
Bruce Allen, Manager of Rotary International in Australia, pointed out that 1300 Rotary Clubs raised only $A 5.6 million dollars for its own humanitarian projects and activities last year let alone giving “an outrageous amount of money” to a 14-year old school girl. “It is totally out of question. There was no application or grant to this person,” he said.
“She is saying that half the money came from the Rotary Club and half of it from the Government Australia. There is no way that any Rotary Club in Australia could afford to pay that amount of money. We just don’t have the money. She got 20 million Australian dollars and I find it highly unlikely. That is an outrageous amount of money,” Mr. Allen noted. He also said that there is nothing called “Rotary Club of Australia” as the girl said because there are 1300 Rotary clubs in the country.
Bruce Allen.jpg
“We only have money for a whole rage of humanitarian programs. But we will never ever get involved to this extent. It is a lot of money and there is no Rotary Club in Australia that could afford to do that.There is a key point here. She is saying that half the money came from the Rotary Club and half the money is coming from the Australian government. There is no way any Rotary Club in Australia could afford to pay that amount of money,” he said.
So many puzzled Ethiopians took to social media to vent their anger and express their doubts on how the person in charge of Ethiopia’s foreign relations is unaware of unlikely global developments as well as the legal implications of corrupting the morals and psychology of a child by involving her in such an orchestrated web of lies and deceptions never heard of in the history of schools anywhere in the world without making any effort to verify such claims.
by 37 percent in a bid to reduce the cost of the national expenditure. From $A 225 million the previous year, the Government of Australia cut its aid to Africa to just 133 million AUD.What makes the story even more ludicrous and bizarre is the fact that during the 2013/14 budget year Australia cut its foreign aid to Sub-Saharan Africa
During the same budget year, Rotary Foundation gave grants totalling $14.2 million to support 265 projects worldwide in the areas of disease prevention and treatment that he foundation dispersed  totalling only $6.5 for education and literacy to support 66 projects around the world,  according to its annual report.
Meanwhile, the Baden Powell College administration declined to give any official statement. But a school source, who spoke on condition anonymity, told Addis Voice that the school officials are very upset and disappointed to be dragged into this kind of scandalous scam.
“Because the issue involves a minor and is also under investigation by the police, we are not authorized to make any public comments,” the source said. The motto of the school is “Looking Forward, and Staying Ahead.” It is not now clear if Mr. Jaleta Ahmed and his daughter are looking forward to returning to Australia to face the music or would rather stay in Ethiopia despite being caught in dangerous web of lies and scandals.
for  more  info  visit http://addisvoice.com/

Monday, March 2, 2015

የአማራ ክልል ከተሞች ልማትና ግንባታ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርን ከኃላፊነቱ አነሳ

‹‹ውሳኔው ፖለቲካዊ ነው›› አቶ አዲሱ ጌታነህ
የአማራ ክልል ከተሞች ልማትና ግንባታ የሰማያዊ ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን ተወካይ እንዲሁም የምዕራብ ጎጃም፣ ምስራቅ ጎጃምና አዊ ዞን የምርጫ ግብረ ኃይል አባል የሆነውን አቶ አዲሱ ጌታነህን ‹‹ማኔጅመንቱን ያውካል፣ የስራ ተነሳሽነት የለውም›› በሚል ከኃላፊነቱ ማንሳቱን በደብዳቤ አሳውቋል፡፡
ይሁንና መስሪያ ቤት ጥቅምት 23/2007 ዓ.ም በብቃቱ መሰረት በኃላፊነት እንደመደበው በደብዳቤ የገለጸ ሲሆን አሁን የተወሰደው እርምጃ ከወቅቱ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ መሆኑን አቶ አዲሱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
‹‹ባህርዳር ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ኃይል እየተፈጠረ ነው፡፡ በተለይ የአንድነት መዋቅር ሰማያዊን ከተቀላቀለ በኋላ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ይህንም ተከትሎ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች ጋር ያደረግናቸው ውይይቶች ብአዴንን አስደንግጦታል›› ያለው አቶ አዲሱ መስሪያ ቤቱ የወሰደበት እርምጃ ፖለቲካዊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የምዕራብ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ መዋቅር በአካባቢው ህዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል፣ እንዲሁም ምርጫ ቦርድ ከዕጩ ምዝገባ ጋር በተያያዘ የሚፈጥራቸውን ችግሮች ለሚዲያ በማጋለጥ ላይ መሆኑ ከኃላፊነት ለመነሳቴ አንድ ምክንያት ነው ሲል ገልጾአል፡፡
የአማራ ክልል ከተሞች ልማትና ግንባታ የቦርድ አባላት የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል የባህርዳር ከተማ ከንቲባ አቶ ላቀ አያሌው፣ የክልሉ ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ያለው አባተ፣ የክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ኃላፊ አቶ አየነው ይገኙበታል፡፡

አበበ ገላው የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን የ20 ሚሊዮን ዶላር ቅጥፈት አጋለጠ

dr_tedros_adhanom
ቴድሮስ አድሃኖም ያራገቡት የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት የፈጠራ ወሬ መሆኑ ተረጋገጠ * የአውስትራሊያ መንግስት እና የሮተሪ ፋውንዴሽን በሪቱ ጃለታን አናውቃትም ገንዘብም አልሰጠንም አሉ
በአበበ ገላው
(አዲስ ቮይስ) ሰሞኑን የህወሃት መራሹ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአንድ የአውስትራሊያ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ውድድር አሸናፊ በመሆን እና አስደናቂ ውጤት በማምስመዝገብ 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በማሸነፍ ያገኘችውን ገንዘብ ለልማት ለማዋል ኢትዮጵያ ትገኛለች የተባለችን የ14 አመት ልጅ በመገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ ድረ ገጾች ከማስተዋወቅ አልፈው በቢሯቸው ከልጅቷ ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።
ሚኒስትሩ በሪቱ ጃለታ አህመድ ገና በለጋ እድሜዋ ይህን ያህል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለልማት በማዋሏ ለኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ ለዲያስፖራው አርአያ መሆኗን በይፋ አውጀው ነበር። ወጣቷ የሽልማት ገንዘቡን በሙሉ አባቷ አቶ ጃለታ አህመድ በተወለዱበት በምስራቅ ሀረርጌ፣ ጋራ ሙለታ፣ ትምህርት ቤት ልታሰራበት ማቀዷን ለጋዜጠኞች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝታ ከሚኒስትሩ ጋር በጋራ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ ያደረገች ሲሆን ገንዘቡ የተገኘው ከፊሉ ከአውስትራሊያ መንግስት፣ ከፊሉ ደግሞ ከአውስትራሊያ የሮተሪ ክለብ መሆኑን ይፋ አድርጋ ነበር።
tewedros
ይሁንና ሸልማቱን አዘጋጀ የተባለው ባደን ፓወል ኮሌጅ በመባል የሚጠራው የመንግስት ትምህርት ቤት ስለጉዳዩ ምንም የሚያውቀው ነገር ባለመኖሩ ግራ በመጋባት ጉዳዩን ለምርመራ ወደ ፖሊስ መምራቱን ለማረጋገጥ የቻልን ሲሆን የአውስታራሊያ መንግስት እና ሮታሪ ፋውንዴሽን በበኩላቸው ለአዲስ ቮይስ በተናጠል በሰጡት መግለጫ እንዳረጋገጡት ለታዳጊዋ ምንም አይነት ገንዘብ አለመስጠታቸውን እንዲሁም ስለ እርሷም ሆነ ስለተባለው ውድድርና ሽልማት ሰምተው እንደማያውቁ አረጋግጠዋል።
የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይና ንግድ ሚኒስቴር በጹሁፍ በላከልን መግለጫ አንደገለጸው የአውስትራሊያ መንግስት በኢትዮጵያ ጋራ ሙለታ ትምህርት ቤት ለማሰራት 10 ሚሊዮን ዶላር ሰጠ መባሉን አስተባብሏል። ሚኒስቴሩ አክሎም በኢትዮጵያ ለትምርት በቀጥታ ድጋፍ ባይሰጥም ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገሮች ጋር ተጠቃሚ በሆነችበት አለም አቀፍ የትምህርት የጋራ ትብብር (Global Education Partnership) በኩል ድጋፍ እንደሚሰጥ ጠቁሞ ኢትዮጵያ በትብብሩ በኩል በሚሰጠው የገንዘብ እርዳታ ተጠቃሚ ነች በማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጄና ሃንድ አክለው ገልጸዋል።
Bruce Allen
በአውስትራሊያ የሮታሪ ፋውንዴሽን ስራ አስኪያጅ የሆኑት ብሩስ አለን በበኩላቸው ስለ ተሸላሚዋም ልጅም ይሁን ስለሽልማቱ ከዚህ በፊት ሰምተው እንደማያውቁ አስገንዝበው ድርጅቱ የተባለውን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ እንኳን ለልጅ ሊሰጥ ለራሱም የበጎ አድራጎት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ በቂ ገንዘብ እንደሌለው አስረግጠው ተናግረዋል። ስራ አስኪያጁ አክለው እንደገለጹትም ባለፈው አመት የበጀት አመት ሮተሪ በ አውስትራሊያ ያሰባሰበው ገንዘብ መጠን 5.6 ብቻ መ ሆኑን ጠቁመው 10 ሚሊዮን ዶላር ለልጅቷ በሽልማት መልክ ሰጠ መባሉ በጣም የሚያሳዝን ክስተት መሆኑን ገልጸዋል። ባለፈው አመት ሮታሪ ኢንተርናሽናል በአለም አቀፍ ለትምህርት ነክ እንቅስቃሰዎች የሰጠው ገንዘብ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በቻ የበረ ሲሆን ይህም ገንዘንብ ለ66 ፕሮጄክቶች መከፋፈሉን ለማወቅ ተችሏል።
ከዚህ በፊት በአለም ላይ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቀውን ይህን “ታልቅ ውድድር” እና የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አዘጋጀ የተባለው የአውስትራሊያው የመንግስት ትምህርት ቤት1800 ተማሪዮችና 180 ሰራተኞች የሚሆኑ ያለከፍያ በበጎ አቃድ የሚሰሩ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን አመታዊ በጀቱ 12 ሚልዮን የአውስትራሊያ ዶላር ነው። ይህም ማለት የትምህርት ቤቱ አመታዊ በጀት ለ14 አመቷ ልጅ ሰጠ ከተባለው ሽልማት በ8 ሚሊዮን ዶላር የሚያንስ ሲሆን የሽልማት ገንዘቡን ትምህርት ቤቱ እንዴት እንዳሟላው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ይሁኑ ተሸላሚዋ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ማብራሪያ አልሰጡም።
ሌላው አስገራሚ ጉዳይ በሪቱ ሽልማቱን አገኝ በተባለው ያለፈው የበጀት አመት የአውስትራሊያ መንግስት በገዘብ እጦት ምክንያት ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገሮች የሚሰጠውን እርዳታ መጠን ከ225 ሚሊዮን በ37በመቶ በመቀነስ ወደ 133 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በመቀነሱ በአለም አቀፍ ደረጃ ሲተች የበነረ ሲሆን የበጀት ቅነሳ ያደረገው ለልጅቷ ለመስጠት አለመሆኑን ግን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።
ይሁንና ይህ ጉዳይ በዙዎች ዘንድ ሆን ተብሎ ለስውር አልማ የዋለ የህወሃት ውስብስብ ተንኮል ጋር የተያያዘ ነው በማለት ጥራጣሪያቸውን በስፋት በመግለጽ ላይ ይገኛል ።
Source; .zehabesha