Wednesday, February 5, 2014

አቶ በረከት ስምኦን ኢህአዴግን በመድብለ ፓርቲ ስም ለርጅም ጊዜ እንዲሄድ ማድረግ እንደሚገባ ገለጹ

አቶ በረከት ስምኦን ኢህአዴግን በመድብለ ፓርቲ ስም ለርጅም ጊዜ እንዲሄድ ማድረግ እንደሚገባ ገለጹ



ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም :-ከሚዲያ ዝግ በመሆን ለኢህአዴግ ካድሬዎችና ሹሞች በተዘጋጀው ውይይት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን  በኢትዮጵያ በልማታዊ አጀንዳ የሚወከለው ኢህአዴግ ብቻ ነው ያሉ ሲሆን፣ ሌሎች ፓርቲዎች ወይ ይህንን የሚጻረሩ ናቸው፣ ወይም ትርጉም የሌላቸው ናቸው ብለዋል።  ኢህአዴግ ለረጅም ጊዜ  በስልጣን ላይ ለማስቀጠል በመድብለ ፓርቲ ስም ይዞ መጓዝ እንደሚጠቅም አቶ በረከት ተናግረዋል።
የመድበለ ፓርቲ ስርአት ለአገራችን ተመራጭ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ሁኔታ ያለው ግን የአውራ ፓርቲ ስርአት ነው ያሉት አቶ በረከት፣ ይህም ስርአት ሁለተኛው ተመራጭ በመሆኑ በአገራችን ለርጅም ጊዜ ይቀጥላል ብለዋል። የአውራ ፓርቲ ስርአት አንድ ፓርቲ በምርጫ እያሸነፈ ለረጅም ጊዜ የሚቀጥል መሆኑንም አቶ በረከት አክለዋል።
አቶ በረከት ይህን የተናገሩት ህዝቡ ሳይሰለች ኢህአዴግን እንዴት ለ50 አመት ተሸክሞ ሊሄድ እንደሚቻል ባስረዱበት ወቅት ነው።

Tuesday, February 4, 2014

የባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት የጋዜጠኞችንና የሚዲያ ነፃነትን ገፏል ሲሉ ጋዜጠኞች ተናገሩ

የባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት የጋዜጠኞችንና የሚዲያ ነፃነትን ገፏል ሲሉ ጋዜጠኞች ተናገሩ

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  :-በሚኒስትሮች በሚመራው የጋዜጠኞች ስልጠና ላይ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት የጋዜጠኞችን እና የሚዲያውን ነፃነት የገፈፈ መሆኑን የስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ ጋዜጠኞች ተናገሩ፡፡ ባህርዳር ከተማ በማካሄድ ላይ ባለው በዚህ የጋዜጠኞች ስልጠና ላይ ” የፕሬስ ነፃነት በሀገሪቱ ሊኖር ባለመቻሉ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ድርጅት ጋዜጠኞች ሳይቀር ተሸማቀው እንዲሰሩ እየተደረገ ያለው የአስራር ስርዓት እስከ መቼ ፍፃሜ ያገኛል?” ብለው ላነሱት ጥያቄ “የሚዲያ አመራሮች ችግር እንጂ የእኛ ችግር አይደለም” ሲሉ የብአዴን ጽ/ቤት ሐላፊና ም/ል ፕሬዚዳንቱ እንዲሁም የአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት የቦርድ ሊቀመንበር አቶ አለምነው መኮነን መልስ ሰጠዋል፡፡
የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋዜጠኞች በገጠማቸው ፖለቲካዊ ጫናና ነፃነት እጦት ሳቢያ  በርካታ ጋዜጠኞች ድርጅቱን የለቀቁ ሲሆን ስርዓቱ አላንቀሳቅስ ያላቸው በርካታ ጋዜጠኞች ወደፊትም ለመልቀቅ በማመቻቸት ላይ መሆናቸው ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
ከጥር 12 ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው በዚህ ስልጠና ላይ የንግድና ኢንዱስትሪ ፣የግብርናና ገጠር ልማት፣የውጭ ጉዳይና ሀገር ውስጥ ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ዋና አጀንዳዎች መሆናቸውም ታውቋል፡፡

Monday, February 3, 2014

ህወሓት ከመለስ ጋርአብሮ ተቀብሯል‬

ህወሓት ከመለስ ጋርአብሮ ተቀብሯል‬

ይህ የያዝነው ወርሓ ለካቲት «የህወሓት ልደት የትግራይ ህዝብ ልደት ነው፣ ህወሓት ብቸኛ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ነው፣ የትግራይ ህዝብ ታሪክ ከደደቢት ይጀምራል፣ የህወሓት አላማና ፍላጎት የትግራይ ህዝብ አላማና ፍላጎት ነው፣ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ሌላ አማራጭ የለውም ዙሪያው ሁሉ ገደል ወይም ጠላት ነው፣ በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብ ህልውና ከህወሓት ህልውና ጋር የተቆራኘና ድርጅቱ ስልጣን ላይ ሲኖር ትግራይም የምትኖር ድርጅቱ ከጠፋ ወይም ስልጣን ላይ ከሌለ ደግሞ የትግራይ ህዝብም አብሮ የሚጠፋ ነው» ...እያሉ በመስበክ በሰማእታት መቃብር ላይ ቆሞው የውሸት ድራማ የሚሰሩበት፣ በትግራይ ህዝብ ደምና አንጡራ ሃብት ላይ የሚነግዱበት፣ በድምሩ «ጆሮውን ቆርጠው የሰጡት ውሻ ሥጋ የሰጡት ይመስለዋል» እንዲሉ የትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ክብሩ፣ ዳር ድንበሩንና ብሄራዊ ጥቅሙን ለባዕድ ሽጠው ሲያበቁ ነፃ አውጥተናሃል!! ልማት አምጥተንልሃል!! እያሉ የሚዘምሩበትና የሚመፃደቁበት የካቲት 11 በዓል እየመጣ ነው። ይህ ዓይነቱ ጭፍን ፕሮፓጋንዳ መርዝ ደግሞ ዛሬ የመጣ ባህል አይደለም። ህወሓት ከተፈጠረበት ቀን አንስቶ እስካሁን ድረስ ለአርባ ዓመታት ያህል ለጀሮ እስከሚሰለች ድረስ በካድሬዎቹ አማካይነት ነጋ ጠባ በዚያች በተቀደሰች ምድር ትግራይ በአሁኑ በሃያ አንደኛ ክፍለ ዘመን የሚሰበክ የደደቢት የአደንቁረህ ግዛ ፍልስፍና መሆኑን ተራ የገጠር እረኛም ሳይቀር ያውቀዋል።

ይሁን እንጂ ህወሓት ከድርጅትነት ወደ ቡድናዊ አምባ ገነንነት፣ በኋላም ከቡድናዊ አገዛዝ ወደ ፍፁም የቤተሰባዊ መዝርፊያና የማፈኛ የግል ኩባንያ ሆኖ ከተሸጋገረ ወዲህ እኖሆ ዓሰርቱ ዓመታት አስቆጥሯል። በመጨረሻም «ጊዜ ዳኛ ታሪክ ምስክሩ ነውና» ድርጅቱ ከባለቤቱ ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ጋር አብሮ ግብኣተ መሬት ገብቷል። ላይመለስ አብሮ ተቀብሯል። አሁን ያለው «በድርቆሽ የተሞላ ህይወት የሌለው የቆዳ ግሳንግስ ወደ(ዓርሲ)» ተለውጦ ባንድ በኩል በአቶ ስብሓት ነጋ «የ80 ዓመት ጎበዝ አለቃ የሚመራ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በኤርትራውያን የሚገፋ አሮጌ ጋሪና በወታደር የሚጠበቅ የደረቀ ሬሳ ሆኖ ቀርቷል» የሚሉ ብዙዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ይህ ምን ያህል እውነትነት አለው? አንድ የፓለቲካ ድርጅት ሞቷል ወይም ህይወት የለዉም ሲባልስ ምን ሲሆን ነው? ህወሓት ከበረሃ ጀግንነት ወደ ዱር አራዊትነት የተቀየረበት ጊዜስ መቼ ነው? እውነት የጥቂት ወሮ-በላና ከሃዲ መሪዎች በረሃ የገቡበትን ቀን የታላቁ የትግራይ ህዝብ ልደት ነውን? የትግራይ ህዝብ ከሌላው ሰማንያ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ምን የተለየ ጥቅም ስላገኘ ነው የአንድ መርሲነሪ የፓለቲካ ድርጅት ልደት የህዝቡን ብሄራዊ በዓል ተደርጎ የሚያከብረው? ለመሆኑ የትግላችን ውጤት ነው እየተባለ የሚነገርለት ሕገ መንግስት እውነት ለትግራይ ህዝብ ይመለከተዋልን? የሚሉና ሌሎች ተዛማጅ ጥያቄዎችን እንድንመልስ ግድ ይለናል።

ወደ ዋናው የጥያቄው መልስና አርእስተ ጉዳይ ከመግባቴ በፊት ግን ለአንባቢዎቼና ለነፃ ሚዲያ ደንበኞቼ በአክብሮት የምጠይቀው በዚሁ ፅሑፍ ዙሪያ በመቃወምም ሆነ በመደገፍ ከቂም በቀል፣ ከስሜታዊ አስተሳሰብ፣ ከጭፍን ደጋፊነት፣ በአጠቃላይ የግለ ስብእና፣ የሃሳብ ነፃነትና ሰብኣዊ መብት በማይጋፋ መልኩ በዋናው ጉዳይ ላይ ያተኰረ ክርክር ወይም ሃሳብ ቢያቀርቡ ለመማማርና በቂ መልስ ለመስጠት ዝግጁ መሆኔን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ እወዳለሁ። ፍርሃትን አስወግዶ የህሊና ባርነትን ሰብሮ በመውጣት የሀገርና የህዝብ ወገን ሆኖ መከራከር፣ ለሃቅ መመስከርና በፅናት መቆም ምንኛ ያኰራል!!! በዘመነ መሳፍንት አንዲት የጎጃም አልቃሽ ““ጎጃሜ ቡዳ ነው ቡዳ ነው ስትሉ ስትሉ አላየህም ወይ ትግሬ እርስ በርስ ሲባሉ «ብላ ተናግራለች» በማለት ከዛሬ አስራ አንድ ዓመት በፊት የህወሓት አመራር ለሁለት ተሰንጥቆ ሲፈረካከስ ያዩ አንድ አዛውንት ያለፉትን የትግራይ ባላባቶችና መሳፍንቶች ታሪክ ከህወሓት ታሪክ ጋር በማነፃፀር እንደዋዛ አጫውተውኝ እንደነበር አስታውሳለሁ። በሌላ መልኩ ደግሞ ስለ ህዝቡ ጀግንነት፣ ጨዋነት፣ ታጋሽነትና አትንኩኝ ባይነት እያስታወሱ የዛሬው ትውልድ ግን ሐሙት የፈሰሰ እንዲሁ ወኔው ተኰላሽቶ መቅረቱ በጣም ያሳዘናቸው መሆኑን በቁጭት ገልፀውልኛል። ነገር ግን በወቅቱ የነገሩኝን ሁሉ ብዙም ልብ አላልኩትም ነበር። በኋላ ግን ስለ ህወሓት የተፃፉ መፃሕፍቶች በተለይም የቀድሞ የህወሓት ታጋይና አታጋይ የነበሩት አቶ አስገደ ገብረ ስላሴ የፃፉትን ጋህዲ በሚል ሶስት ተከታታይ መፃሕፍቶችን ሳነብ «ማየት ማመን ነውና» የትግሉ ባለቤትና የድርጅቱን መስራች የነበሩት ሰዎች እንኳን ሳይቀር የመሰከሩለት ህወሓት ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ተግባሩ ሲመረመር ከላይ አዛውንቱ የነገሩኝ አባባል በትክክል የሚገልፅ መሆኑን ለመረዳት ችያለሁ።

«የህወሓት ታሪክ የርስ በርስ መላላት፣ ህዝብ ለህዝብ የማናቆርና ሀገርን የማፍረስ ታሪክ ነው» ቢባል ከእውነት የራቀ አይደለም። ይህን በሚመለከት ዝርዝሩን ለታሪክ ፃፊዎች ትቼ አንድ ሁለት አብነቶችን ብቻ ልጥቀስ። ህወሓት ከትጥቁ ትግል ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለ40 ዓመታት ያህል የዘለቀው አንድ ገዢ መፈክር ነበረው። እሱም «የቻለ ይሩጥ!! ያልቻለ ያዝግም!! ያበቃለት ይለይለት!!? በትግርኛ (ዝኻኣለ ይጉየ! ዘይካኣለ ይሳለ! ዘብቀዐ ይታኣለ)» የሚል ነው። ከመፈክሩም ጎን ለጎን በድርጅቱ የኪነት ቡድን የተሰራ ከአቶ መለስ መልክ ጋር የሚመሳሰል ፊት ለፊቱ ደግሞ ጣቱን ወደ ሰዎች ቀስሮ የሚያስፈራራ ሥዕል በየስብሰባውና ታጋዮች ባሉበት ሁሉ የሚለጠፍ ነበር።

ስዕሉ በጋሃድ በአደባባይ መውጣት የጀመረው ደግሞ ልክ እነ ዶ/ር አረጋዊ በርሄና አቶ ግደይ ዘርኣፅዮን ከድርጅቱ ተለይተው ከወጡ በኋላና «ማርክሰ ሌኒስት ሊግ ትግራይ (ማሌሊት)» ከተመሰረተ አንድ ዓመት ባልሞላ ውስጥ ነበር። ስዕሉ ያልተለመደ ነገር ስለነበረ ብዙ ታጋዮችን በተለይም ያልተማሩ የገበሬ ልጆች የሆኑትን ታጋዮች ግራ አጋብቷል። አንዳንድ ቦታም ሌሊት በሳንጃ እየቀደዱ ይጥሉት ነበር። ከጊዜ በኋላ ግን ስዕሉ ተለመደ። የሚገርመው ግን በወቅቱ የድርጅቱን የኪነ ጥበብ አባል ሆኖ ስዕሉን ያቀነባበረ ሳኣሊውንም ጭምር ከጥቂት ወራት በኋላ ድርጅቱን ለቆ በመውጣት ዛሬ በስደት ዓለም በህወይት ይገኛል። ስሙን ያልጠቀስኩበት ምክንያት ደግሞ የሱ ፍቃደኝነት መጠየቅ ስላለብኝ ነው። የመፈክሩ ዋና አላማና ስትራተጂም የሚከተሉትን ሶስት ዋና ዋና ነገሮችን ያቀፈ ነው፡-

①..አንደኛ የአቶ መለስ ዜናዊና የአቶ ስብሓት ነጋ ቡድን ተቀናቃኝ ወይሞ ሞጎደኛ ተብለው የሚጠረጠሩትን ያመራር አባላት፣ ምሁራንና የጦሩ አለቆችን (ይህችን ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም) በማለት ቀስ በቀስ የማፅዳት ስልትና ስትራተጂ ነው። ይህንንም ሰሞኑን በኢትዮ- ሚዲያ ድሕረ ገፅ የወጣውን የነ ሙሴ፣ ዶ/ር አታክልት፣ ገሰሰው አየለን ጨምሮ ተኩሉ ሃዋዝ፣ መለስ ካሕሳይ፣ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ፣ ግደይ ዘርኣፅዮንና ሌሎች በሽዎች የሚቆጠሩት የድርጅቱን ከፍተኛና መካከለኛ የአመራር አባላትን ያካትታል።

②... ሁለተኛው የመፈክሩ አላማና ስትራተጂ የትግራይ ብሄረተኝነትንና ብሎም የኢትዮጵያዊነት ስሜትን ከትግራይ ምድርና ከህዝቡ አስተሳሰብ ከስረ መሰረቱ በመፋቅና በማጥፋት በምትኩ በትግራይ ብሎም በሀገራችን የኤርትራ ሻዕቢያዊ አመለካከት የበላይነት እንዲይዝ ማረጋገጥ ነው። በዚሁ ዙሪያ በቅድሚያ የተመቱት የድሮ አስተሳሰብ፣ ሀገራዊ ስሜትና እንዲሁም በኤርትራ ጉዳይና በአገር አንድነት ጉዳይ ላይ የከረረ አመለካከት አላቸው ተብለው የሚገመቱትን ባላባቶችንና የሀገር አዛውንቶችን ናቸው። ቀጥሎም የተመቱት የትግራይ መሁራኖች ናቸው። በኤርትራና በሀገር ጉዳይ ዙሪያ የሚከራከሩና ጥያቄ የሚያነሱ ምሁራን እንደ ኤለክትሪክ ይፈሩዋቸው ነበር። በዚህ መሰረት «ሽዋውያን ተጋሩ» የሚል የቅፅል ስም መለጥፍ ብቻ ሳይሆን በዘፈንም ሳይቀር ቅስማቸው እንዲሰበርና አንገታቸው እንዲደፉ ተደርጓል። በዚህ ምክንያት የቻሉትን ከድርጅቱ ሸሽተው እንዲያመልጡ ያልቻሉት ደግሞ ለእስርና ለግድያ ተዳርጓል። በዚህ ምክንያት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ምሁራን ዛሬም ስለህዝባቸውና ሀገራቸው ጉዳይ ደፍረው ጥያቄ እንዳያነሱ ፍርሃት እንደ ወባ በሽታ በደማቸው ውስጥ ገብቶ እያዩ እንዳላዩ ዝም እንዲሉ ትልቅ ምክንያት የሆነውን ጠባሳ እስካሁን ድረስ አልሻረም። ዛሬ በአረና ትግራይ አባላትና ደጋፊዎቻቸው እየደረሰ ያለው ዱላም ከዚሁ የተለየ አይደለም። ለአንድ የአረና አባል ከአምስት በላይ ሰላዮች በመመደብ ኮቲያቸውን እየተከተሉ መውጫና መግቢያ ያሳጧቸዋል። ዛሬ ትግራይ ለነ ስብሓት ነጋና ሌሎች መሪዎች ታማኝ የሆኑትን የኤርትራ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ድርጅቶች በነፃነትና በልበ ሙሉነት የሚንቀሳቀሱባት በአንፃሩ ከህዝቡ አብራክ የተፈጠሩ ለነ አረና ትግራይና ሌሎች ሀገር በቀል ድርጅቶች ግን በገዛ ሀገራቸው ተሸማቅቀውና በአደባባይ በዱላ እየተመቱ የሚኖሩባት ምድራዊ ሲኦል ሆና ትገኛለች። በመሆኑም ዛሬ ሰፊው የትግራይ ህዝብ ባንድ በኩል የትግራይ ሻዕቢያ በሌላ በኩል ደግሞ የኤርትራ ሻዕቢያ አጣብቅኝ ውስጥ ገብቶ በሁለት አለንጋ እየተገረፈ የሚገኝ ህዝብ ሆኗል። ታዲያ!! ለዘህ ሚስኪን ህዝብ አለሁልህ የሚል ወገን ማን ይሆን?

③.. ሶስተኛው የመፈክሩ አላማና ስትራተጂ በህዝቡ የስነ ልቦናና የአካል ጥቃት በማድረስ በተለይም በትግራይ ምድር ፍርሃት፣ ሽብር፣ ጥርጣሬና ህወከት በማንገስና የህዝቡን ሁለንትናዊ አስተሳሰብ በመቆጣጠርና በማደንዘዝ ፀጥ ረጭ ብሎ እንዲገዛና ለጥቂት መሪዎች ዘላለማዊ ስልጣን አገልጋይ ሆኖ እንዲኖር ለማድረግ ነው። በሌላ አነጋገር ትግራይ ወፍ እንኳን ዞር የማይልባት፣ ሌላው ኢትዮጵያዊ በትግራይ ህዝብ ጉዳይ ላይ እንደማያገባው ተደርጎ መፈናፈኛ በማሳጣት በስመ ልማት እንደፈለጉ የሚግጥዋት የህወሓት የጓሮ አትክልት ሆና እንድትኖር ለማድረግ ነው።

ልበ በሉ!! የትግራይ ህዝብ በጦርነት የደቀቀ ህዝብ ነው። ትግራይ ደርግ፣ ኢዲዩ፣ ጀብሃ፣ ሻዕቢያ፣ ኢሕአፓ፣ ህወሓትና ሌሎች ብረት ያነገቡ ሀይሎች የሚንቀሳቀሱባት ለአስራ ሰባት ዓመታት ያህል የጦርነት አውድማ ሆና ቆይታለች። ዛሬም ህዝቡ ከጥይት ጭኾት አልተላቀቀም። በኤርትራና በኢትዮጵያ በሁለቱም ሀገሮች ድንበር ከሩብ ሚሊዮን በላይ ሰራዊት በመሸገበትና በተፋጠጠበት የጦርነት ደመና ስር ሆኖ ዛሬ ነገ ውጊያ ይጀመራል እያለ በፍርሃት ተውጦ የሚገኝ ህዝብ ነው። በዚህም ላይ በየጊዜው ከያሉበት በታጣቂዎች እየታፈኑ ወደ ኤርትራ ተወስደው ደብዛቸው የማይታወቁ ንፁኃን ዜጎች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። በዚሁ ፍርሃት ቀያቸውንና ቤታቸውን እየለቀቁ ወደ ዓረብ ዓለም የሚሻገሩና ወደ ማሀል ሀገር በመሸሽ የኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞችን በልመና ያጥለቀለቁት የየተኛው አካባቢ እንደሆኑ ማንም ኢትዮጵያዊ ያውቃል። እነዚህ ግጭቶችም እንደ ፓለቲካ መሳሪያና ማስፈራሪያ እየተጠቀሙ «እኛ ከሌለን ያ ሁሉ ጠላት ይመለሳል፣ ሻዕቢያ ተመልሶ ይውጥሃል፣ ኦነግና ትምክሕተኞች ቂማቸው ይወጡቡሃል፣ የሽብርተኞች ዒላማ ትሆናለህ፣ በትግራይ የተተከሉ ፋብሪካዎች ተነቅለው ወደ ማሃል ሀገር ይወሰዳሉ፣ በትግልህ የቀበርካቸው ጠላቶች ከመቃብር ተነስተው ይመጣሉ፣ ወዘተ» እያሉ ነጋ ጠባ ህዝቡን ማሸበርና ማደንቆር የተካኑበት ዋነኛ የአገዛዝ ጥበባቸው ሆኖ ይገኛል።

ወንድሞቼ ሆይ!! 
ታዲያ እንዲህ ዓይነቱ የቆሸሸ ታሪክ ያለው ድርጅት ዛሬ በትግራይ ህዝብና በተለይም በአረና አባላትና ደጋፊዎቻቸው ላይ የአራዊት ስራ ቢሰራ የሚያስገርም አይደለም። ህዝብን ሁሉ ጊዜ ማታለል የማይቻል መሆኑን ያልገባቸውና ጊዜውም ጥሏቸው እየሄደ መሆኑንም የማይቀበሉ እንደ ሾላ ፍሬ ውስጣቸው የበሰበሱ መሪዎች እስከ ህልፈተ ቀናቸው ድረስ «የደንቆ ልቅሶ መልሶ መላልሶ» እንዲሉ ዛሬም የሚናገሩት ቋንቋና የሚሰሩት ስራ ያው በጫካ የለመዱት ዓይነት ነው። ከላይ የተጠቀሰው የመፈክራቸው አላማና ስትራተጂም በትክክል ሲተረጎም «እምቢ ያለ ሰው ጥይት አጉርሰው» ከሚለው የደርግ ስርዓት መፈክርና ተግባር ጋር አንድ ዓይነት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ይስቷል ብዬ አልገምትም። የሚያሳዝነውና የሚያስገርመው ነገር ግን ትግራይን የጥፋትና የመከራ ሞዴል በማድረግ የሚፈፅሙትን ጉድ እንደ ኤይድስ ወረርሽኝ በሽታ ወደ ሌሎቹ ክፍላተ ሀገራትም እየተዛመተ መምጣቱ ነው። በዚሁ ነጥብ ዙሪያ በቀጣዩ ፅሑፌ ተመልሼ እመጣለሁ። 

ቸር ሰንብቱ።

~~ነፃነት አድማሱ~~

ድርቅ ለመታው ፖለቲካ ማዳበሪያ፦

ድርቅ ለመታው ፖለቲካ ማዳበሪያ፦

መመካከር፤ መተቻቸት አእምራችንን ያሰፋዋል የሚል እምነት ስላለኝ የተሰማኝን ለማካፈል ስለሆነ ጽህፏ ለምን እንደ ምትበጅ ሰከን ብላችሁ እንድታነቧት በትህትና አሳስባለሁ፟፦
ኢትዮጵያን የሚጠብቋት ልጆቿ መሆኑ አይታበልም። ሲጠብቋት ግን በዘር፤ በጐሳ በቋንቋ ሳይለያዩ በጋራ መሆን አለበት። በዚህ ሁኔታ አገራችን ታፍራ ተከብራ ኑራለች። አንድነቷን ጠብቃ በቆየች አገራችን ላይ የተደቀነው አደጋ እጅግ ከባድ ነው። የአገራችን ችግር ውስብስብ ሆኖ የጐሳ ፖለቲካን ብሎም ዘረኝነትን መዋጋት ሲቻል ባለፈ ታሪክ ዙሪያ የሚደረገው እሰጥ አገባ ችግሩን እያሰፋው ከመሄድ ውጭ መፍትሄ አይገኘለትም።
በተለይ በአጼ ምኒሊክ ዙሪያ የሚናፈሰው “ወሬ” ልበለው በጣም ትውልዱን እንደሚጐዳ እርግጠኛ ነኝ። ያሳዝናል ቀዳማዊ ኃይለስላሴን፤ ደርግን፤ ወያኔን መውቀስ፤ ሁሌ መውቀስ መቼነው ዋናውን ጠላት ለይተን የምናውቅ? ለእኔ ዋናው ጠላት ዘረኛው ወያኔ/ ኢሕአዴ ነው። መጥኒ ለዚህና ለመጭው ትውልድ?። ውሀ እያሳሳቀ ይወስዳል እንዲሉ የዘር ፖለቲካም እያባበለ ሰዎች ሳይወዱ ከማን አንሸ እልሕ እየተናነቃቸው እንዳንጠፋፋ መስከን ግድ ይላል።
ኢትዮጵያ እንደ አገር ልትፈጠር የቻለችው በአንድ በሄር ወይም ብሄረሰብ ተጋድሎ ሳይሆን አማራው፤ ጉራጌው ትግሬው፤ ሽናሽኑ፤ አገው፤ እስላም ክርስቲያኑ ውዘተ በከፈሉት መራር የሕይወት ዋጋ ነው። በዚህ የተነሳ ኢትዮጵያ ታላቅ አገር ለመሆን በቅታለች። ይሁን እንጂ ከአስተዳደር ድህነት ነፃ የሆነበችበት አጋጣሚ አልታየም። ይህ ለምን ሆነ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይመስለኛል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ካለበት ችግር ተላቅቆ የመብቱ ባለቤት ሆኖ በፈለገበት ቦታ ተዛውሮ የመስራት፤ መንግስትን ሲፈልግ የመሾምና የመሻር የማይገሰስ መብቱ እውን እንዲሆን በስውርና በግልጽ ገዥዎችን ከመታገል የተቆጠበበት ጊዜ የለም። እንዲሁ ከተማሪዎች ጀምሮ እስከ ፖለቲካ ድርጅቶችና ሚዲያዎች ድረስ የተለያዩ የትግል ስልቶች ተካሂደዋል።
ሕዝባቸውን ከጭቆና ነፃ ለማውጣት የተለያዩ ፖለቲካ ድርጅቶች ሕዝባቸውን ለማደራጀትና ለማታገል እንዲሁም የተሟላ ዜና ለሕዝባቸው ለማዳረስ በፈቃደኝነት የተዋቀሩ ሚድያዎች እንደነበሩና አሁንም እንዳሉ ይታወቃል። ይሁን እንጂ የዘር ፖለቲካውን በጋራ መታገል ሲቻል ዛሬ ባለፈ ታሪክ ዙሪያ አጼ ምኒሊክ፤ አጼ ቴዎድሮስ፤ አጼ ዮሐንስ ወዘተ ይህን አደረጉ፤ በሚል አላስፈላጊ ውዝግብ ውስጥ ባልተገባ ነበር። እነዚህ አለኝታዎቻችን እኮ በዘር፤ በጐሳ በቋንቋ፤ በሃይማኖት ሳይከፋፈሉ ኢትዮጵያን አስረክበውናል። በነበራቸው አቅም ሰርተው አልፈዋል። እናም ከሰሩት ሥራ ውስጥ ጠቃሚውን በመውሰድ ጐጅ የሚባለውን ማሻሻል ሲቻል የተጀመረው ትግል ፈር እንዲስት ማድረግ ለማን እንደሚበጅ አንባቢ ፍርዱን ይሰጥ ከማለት ውጭ ሌላ የምለው አይኖረኝም።
ከላይ ይህን ካልኩ ዘንዳ ስው ስለመሆናችን አንዳንድ ነገሮችን ልጠቃቅስ። ሰው መጀመሪያ ሲወለድ ይዞት የሚወለድ የተለየ ዘር ሳይኖረው ሰው የሚለውን ሥም ይዞ ወዚህች ምድር እንደሚመጣ ታሪክ ይነግራል። ሰው ሲወለድ ሰውነቱንና ሕይወቱን ይዞ ብቅ ሲል አማራ፤ ትግሬ ጉራጌ ሽናሽን፤ ወላይታ፤ ኦሮሞ ወዘት ነኝ ብሎ አይደለም። ሰው ከምንም ዓይነት ዘር ወይም ጨቋኝ ቤተሰብ ልውለድ የማለት ምርጫ የለውም። ሰው ጾታውን ቤተሰቡን፤ ቆዳውን፤ ቀለሙን ወይም ዜግነቱን መርጦ አይወለድም። ነገር ግን ይህ እውነተኛ የሰው ልጅ ታሪክ ሆኖ እኛለ አንዳንድ እውቀት አለን የሚሉ ሰዎች ዘርን ለይቶ ያልተወለደን ህብረተሰብ በመለያየት ለዝና፤ ለሥልጣን ሲባል ሰዎች የዘር ሐረግ እየቆጠሩ በጥላቻ እንዲተያዩ በመደረጉ በሰዎች ዘንድ መከባበርና አንድነት ጠፋ። ክፋትና መጨካከን ተስፋፋ። ይህን እሆናለሁ ብለን ባንወለድም ቅሉ ከተወለድና ካደግን እንድናስብበት ከእግዜአብሄር በተሰጠን አእምሮ ከፉና ደጉን የመለየት ኃላፊነት የራሳችን ሆኖ እያለ ለምን እንደማንጠቀምበት ግራ ያጋባል።
በአገራችን ላይ እየደረ ያለው ችግር ለማንም ትውልደ ኢዮጵያዊ ግልጽ የሆነ ይመስለኛል። ችግሩ እንዲወገድ ሁሉም ፓርቲዎች ለዴሞክራሲና ለመልካም አስተዳደር እንደሚታገሉ ፕሮግራማቸውን በወረቀት ላይ አስቀምጠው ሲነግሩን እንሰማለን። ይሁን እንጂ አብዛኞች ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሚጠቅም ሁኔታ እየታገሉ አይደለም። ምክኒያቱም በደጋፊነትም ሆነ ውጭ ሆኖ እንደሚስተዋለው ከሆነ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጥቃቅን ልዩነቶቻቸውን ወደ ጐን በመተው ሳይሆን ከዚህ በፊት የለሉ ቁርሾዎችን እያፈላለጉ እርስ በርስ ሲወነጃጀሉ ይታያሉ። አንዳንዶች ደግሞ ለአንዲት የቆየች ኢትዮጵያ የሚጠቅም ሥራ መስራት ሲጠበቅባቸው ኢትዮጵያን በመበታተን ሥራ በመጠመዳቸው አሳዛኝ መሆኑ አልቀረም። ጠቅለል ባለ መልኩ ሕዝቡን የመብቱ ተጠቃሚ ማድረግ ቀርቶ ራሳቸውን ከድሃ አስተሳሰብ ነፃ አላወጡም ቢባል ቢያንስ ነው።
አንድ የፖለቲካ ድርጅት መሪ ትግል ሲል መጀመሪያ ብዙ መመዘኛዎችን ሊያሟላ ግድ ይለዋል። ይህ ሲባል ቅድሚያ የራሱን ማንነትና ይዞት የተነሳውን ፕሮግራም አበጥሮ ሊያውቅ ይገባዋል። ወደፊት ትግሉን ለመግፋት ደካማና ጠንካራ ጐኖቹን ማለት በትግሉ ጉዞ ላይ የሚሳካና የማይሳካለት መሆኑን አስቀድሞ ማወቅ ይጠበቅበታል። የፖለቲካ ፕሮግራሙ ከሕዝብ ጋር መሄድና አለመሄዱን፤ የደጋፊዎቹን ወይም የአባላቱን ማንነት ማወቅ ያስፈልገዋል።
ከላይ በመጠኑ የተጠቀሱትን ካገናዘበ በኋላ የፖለቲካ ትግሉን የትርፍ ሰዓት ሳያደርግ፤ እውቀትና ጉልበቱን መርምሮ በምን መልክ መጠቀም እንደሚችል ጥርት ባለ ሁኔታ ሊያውቀው ይገባል። ከዚህ በተጨማሪ አንድ ድርጅት ከሌሎች ድርጅቶች ተለይቶ ለስኬት እንደማይበቃ ተረድቶ ተባብሮ ለመታገል ዝግጁ መሆኑን ማመን አለበት። ከዚህ ሳንወጣ ጥንቃቄ ሊደረግበት ያውም እጅግ አስፈላጊ የሚሆነው መሪው ትግል ሲል ለአገርና ለሕዝብ ጥቅም ሲል መሥዋእትነት ሊከፍል እንደሚችል እርግጠና ስለመሆኑ ከሕሊናው ጋር ተሟግቶ ውሳኔ ላይ መድረስ አለበት። ነገር ግን በአቋራጭ ለሥልጣና ለዝና ሲል ትግል መጀመር ያለበት አይመስለኝም።( ይህ የራሴ እምነት ነው) ምክንያቱም የዝና ትግል ለአገርም ሆነ ለሕዝብ ብሎም ለራሱ የሚሰጠው ጥቅም ስለማይኖር ፈጥኖ ይከስማል። ተመልሸ ትግል ልቀጥል ቢልም አይታመንም። ስለዚህ ለስኬቱም ሆነ ለውድቀቱ ቁልፉ መነሻው ይሆናል ማለት ነው።
የፖለቲካ ደርጅት መሪ ለዝና ሲል ትግል መጀመር የለበትም ስል ያለምክኒያት አይደለም። ከዚህ በፊት የታዩት የትግል ዓይነቶች መጀመሪያ የአንበሳነት ባሕሪ አሳይተው ፈጥነው የከሰሙትን ማቢ ማድረግ ይቻላል። ይህ ማለት መጀመሪያ ሲነሱ መድረሻቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ግንዛቤ ስላልነበራቸው ነው ማለት ይቻላል ስለዚህ ከአላማ የለሽ የትግል ሩጫ ለመዳን መጀመሪያ የመሪውን ውሳኔ ይጠይቃል። እንደሚታወቀው አንድ ሰው ወይም ቡድን የፖለቲካ ድርጅት ለመመስረት በጣም ቀላል ነው። እንዲሁ በትግል ሥም ሌሎች እንዲከተሏቸው /አባል እንዲሆኑላቸው/ መጠነ ሰፊ ቅስቀሳ ማድረግም ቀላል ነው። አንዳንድ ሰዎች የፖለቲካ ድርጅቶችን ምንነት ማለት ፕሮጋማቸውን በውል ሳያገናዝቡ ከአገር ፍቅር አንፃር ይሁን በዋህነት አባል ይሆናሉ። የህቡዕ ድርጅት እንደሆነ ይነገራቸውል፤ የሚታዘዙትን ወርሃዊ መዋጮ መክፈል ይጀምራሉ። ይሁን እንጅ የድርጅቱ አካሄድ ያላማራቸው ወጣ፤ ገባ ማለታቸውን እየተመለከትን ነው። በመሆኑም ራሱን ለእውነት ያላነሳሳ ህቡዕ ድርጅት ብዙ ሳይቆይ ባለበት መርገጥ ይጀምራል። የዚህ ዓይነት የፖለቲካ ድርጅት የሚያመላክተው ነገር ቢኖር ድርጅት ፈጣሪዎች ከራሳቸው ጥቅም አንፃር መሆኑን ነው። የዚህ ዓይነት አደረጃጀት መጨረሻው ብዙ ሳይጓዝ ተሸናፊ ስለሚሆኑ በሕዝብና በደጋፊዎች ላይ እምነትን ያሳጣሉ።
የፖለለቲካ ድርጅት መሪዎች እንዲተባበሩ ሕዝቡ ከ20 ዓመታት በላይ ደጋግሞ ቢጠይቃቸውም የሕዝባቸውን ጀሮ ለማዳመጥ ዝግጁ ሆነው አልተገኙም። ሕዝቡም የተባበሩ ጥያቄው ተቃባይነት ባለማግኘቱ ዛሬ ዛሬ ተባበሩ የሚለውን ቀይሮ “ተሰባበሩ፤ ወይም አርፋችሁ” ተቀመጡ፤ የትግሉ አቅጣጫ አልገባችሁም እስከ ማለት የደረሰ ስለመሆኑ ከአንዳንድ ምንጮች መረዳት ይቻላል። መቼም ይህን እውነት ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው መገንዘብ ያዳግተዋል ለማለት አይቻልም።
የኢትዮጵያ ሕዝብ በመረጠው መንግሥት የመተዳደር ፍላጐቱን በ1997 ምርጫ ወቅት አሳይቶ ነበር፡፤ይሁን እንጂ የፈለገውን ግን ሳያገኝ ቀርቷል። ለዚህ በዋናነት የተጠያቂነት ድርሻ ያላቸው የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች መሆናቸው አይካድም። ለዚህ ብዙ ማስረጃ ሳያስፈልግ በቅንጅትና በኅብረት ጊዜ የተደረገውን ተመልሶ ማስታወስ በቂ ነው። ሕዝቡ በተቃዋሚዎች ላይ ያለው እምነት እየተሟጠጠ ተስፋ የመቁረጥ አጋጣሚዎች ሰፍተዋል። ቀጣዩ ምርጫ 2007 እየተቃረበ ሲመጣ ኢሕአዴግ አስቀድሞ እየተዘጋጀ ስለመሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ባንፃሩ ተቃዋሚዎች ለሚቀጥለው ምርጫ ምን ያሕል ተዘጋጅተዋል የሚለውን በውል ለመረዳት የሚያዳግት ነው። ምክንያቱም ተቃዋሚዎች ካለፈ ስህተታቸው ተምረው ምን ያልህ ሕዝቡን አደራጅተዋል? እንዳለፈው ችግር ቢፈጠር ለቆሙለት አላማ መስዋዕት ለመክፈል ቁርጠንነታቸው ምን ያህል ነው? ወይስ እንዳለፈው ቆሳቁሰው ሕዝቡን አጋልጠው ለተወሰነ ጊዜ ታስረው ሲፈቱ ውጭ ለመውጣት? ይህ ጉዳይ ምርጫው ሲደር በእውን የሚታይ ስለሚሆን ይታሰብበት ከማለት ውጭ በእርግጠኝነት ይህ ይሆናል ለማለት ያስቸግራል። ይሁን እንጂ በተቃዋሚዎች ዙሪያ የሚታዩ መጐሻሸሞች መኖራቸው አይካድም። አንድነት ከሌለ ደግሞ የሕዝቡ ተስፋ መጨለሙ አይቀሬ ነው።
ቢሆንም የኢትዮጵያን የቆየ ታሪክ ወደ ኋላ ተስበን ስንቃኝ ሕዝቡ እርስ በርሱ በመተማመን፤ በመመካከር በጋራ ችግሮቹን በመፍታት አገሩን ከጠላት ጠብቆ የቆየ ኩሩ ሕዝብ ነው። ለመሰረቱና ለአንድነቱ ማስረጃ አማራው፤ ከትግሬ፤ ኦሮሞው፤ ከወላይታ፤ ጉራጌው ወዘተ ዘር ሳይለይ ተጋብቶ ተዋልዷል። ኦሮሞ ’ትግሬ፤ አማራ፤ ሶማሊ፤ ወዘተ አጋዥና አጋር ከሆነው ወንድሙ ጋር በሕግ የምትተዳደር የሰዎች መብት እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለማሳደግ አንዱ ብሄር ሌላኛውን ብሄር በጥላቻ ዓይን አይመለከትም ነበር። ዛሬም ቢሆን የምናየው ሕዝቡ አገሩን፤ ኃይማኖቱን ወዳድ በመሆኑ በአንድነቱና በዜግነቱ ስለሚኮራ ለከፋፋዎች በር ላለመስጠት፤ አንድነቱ እንዳይናድ የሚያደርገው ተጋድሎዖ ከፍተኛ ነው። ነገር ግን የአገር አንድነትና የሕዝብ መብት እንዳይረጋገጥ በተፈጠረው የጐሳ ፖልቲካ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ የተረጨውን መርዝ ለመቋቋም አጋዥ የፖለቲካ ድርጅት እንደሚያስፈልገው እየጠየቀ ነው። ለሕዝቡ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ የተለያዩ ተቃዋሚ ድርጅቶችና ስቪክ ማኅበራት መኖራቸው እውነት ነው። ይሁን እንጂ ስንቶች ናቸው ለመስዋእትነት የተሰለፉ የሚለውን በውል ለመለየት አስቸጋሪ ነው።
መሪነን የሚሉ አንዳንድ ግለሰቦች ልዩነቶችን ከማጥበብ ይልቅ በጐሳ ፖለቲካ ምክኒያት አንዱን ብሄር ጨቋኝ አንዱን ተጨቋኝ በሚል የቋንቋ ልዩነት እንዲፈጠርና የሕዝቦች ጭቆና እንዲራዘም፤ ራሳቸውን ከሥልጣን ወንበር ለማውጣት ሲሉ በጋራ የኖረን ሕዝብ በመለያየት አንዱ ብሄር ከሌላውኛው ጋር እንዲጋጭ በማድረግ የወንድማማችነት ባህሪ መልኩን እየቀየር በጥላቻ እንዲተያይ የማይፈነቀል ድንጋይ የለም። ያለው መንግሥት በሕዝብ ምርጫ ሳይሆን በጉልበት መቀመመጡ ሃቅ ነው፡፡ ይህ መሆኑ እየታወቀ ሁሉም ባይባሉ አብዛኛች የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ያላቸውን ልዩነት በማጥበብ በጉሳ ቁንቋ ብሎም በሃይማኖት ሳይወሰኑ ያላቸውን ችግር በሰለጠነ አስተሳሰብ በውይይትና በስልት ኃይላቸውን አስተባብረው ለአገራቸውና ለሕዝባቸው ሲሉ አብረው መስራት ይጠበቅባቸዋል።ይህ ሲባል ተቃዋሚ ብቻ ሳይሆን ያገባኛል የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ የመተባበር ግዴታ ያለበት ይመስለኛል። ይህ ካልሆነ ግን ለጭቆናው መራዘም የሁሉም ድርሻ እንዳለው ማወቅ ያስፈልጋል።
እርግጥ ነው መንግሥት ሥልጣኑን ለማስቀጠል ሲል ተቃዋሚ የሚላቸውን ሁሉ ለመደፍጠጥ የሚችለውን ሁሉ እያደረግ ነው፤ ይህ ደግሞ የሚጠበቅ ነው። ባንፃሩ ተቃዋሚ ነን የሚሉ የፖልቲካ መስመር ዘርግተው በጋራ መንቀሳቀስ የሚጠበቅ ነው። ነገር ግን ከሕዝቡ ውጭ ሆነው ሳያደራጁ ለሥልጣን ሽኩቻ ሲጉሻሸሙና ሲሰዳደቡ ማየት ምን ያህል ዝቅጠት መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል። በሥመ ተቃውሞ ያለ ተስፋ አሮጌውን አመት በአዲስ ዓመት መተካትም አድሮ ጥጃ ማለት ቢያንስ ነው። ይህ ሲባል ሁሉንም ፖለቲካና ስቪክ ማኅበራትን በጥቅሉ ለማጣጣል እንዳልሆነ አንባቢ ልብ ሊል ይገባል። ጠንካራ ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎች አሉ፤ይሁን እንጂ ትግሉ ወደፊት እንዳይገፉ አብዛኞች በለበጃ ሰርጅተው ለመጣል በሚያደርጉት የውስጥ ሴራ ባሉበት ዳዲ እያሉ እንዲያውም እየከሰሙ ማንነታቸው እስከ መረሳት የደረሱ እንዳሉ መታወቅ ያለበት ይመስለኛል።
ኢትዮጵያዊያን ስንባል ከዓለም የተለየ ባህሪ እንዳለን እርግጥ ነው። ብዙ ዝርዝር ውስጥ ሳንገባ አያቶቻችን፤ አባቶቻችንና እናቶቻችን እንደ ዛሬው በጉሳ፤ በሃይማኖት ሳይለያዩ አገራቸውን ከውጭ ወራሪ ሃይል ለመከላከል መተኪያ የሌለ ሕይወታቸውን መስዋታቸው ነው። ስለዚህ በጋራና በአንድነት በመቆማቸው የአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌ ለመሆን የበቁት በዚህ ሁኔታ ይመስለኛል። ብሄራዊ አንድነቷን ጠብቀው ለዚህ ትውልድ የቆየችው በሕዝቡ አንድነት በጀግና ልጆቿ ደምና አጥንት በፀረ-ኮሎኒያሊዝም አቋማቸው ነው።
ከታሪክ እንደምንረዳው ቀደምት መንግሥታት በሕዝብ ላይ ጭቆና ቢያደርሱም የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም አሳልፈው ባለመስጠት በማጠናከረው ነው ያቆዩአት። የማይካድ ነገር ቢኖር በፊውዳሉ ሰረዓት በሥልጣን ይገባኛል የእርስ በርስ ውጊያ ነበር። ነገር ግን የአገራቸውን አንድነት፤ ታሪካቸውን ለማናጋት እንዳልነበር ታሪኮቿ ይነገሩናል። በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘር በሃይማኖት በጾታ ወዘተ ሳይለያይ ተጋብቶ ተዋልዶ አብሮ የኖረ ሕዝብ ነው፡፤ መከራውንም ደስታውንም በጋራ ተካፍሎ ይህችን አገር ለኛ አስረክቧል። በእኛ ዘመን በተፈጠረው የጉሳ ፖለቲካ ምክንያት አገርና ሕዝብ ተጉድቷል፡፤ በሚፈጠረው የዘር ፖለቲካ የአገሪቱ አንድነት የሕዝብ መብት በከፍተኛ ደረጃ ተናግቷል። ብዙዎች ታሰረዋል፤ ተሰደዋል ከስራቸው ተፈናቅለዋል፤ ከቀያቸውም የተፈናቀሉ መኖራቸውም ሃቅ ነው፡፤
በአገራችን ሰላምና መረጋጋት ሊመጣ ከተፈለገ ሁሉም ብሄር-ብሄረሰቦች ለፍትህ ሲሉ በጋራ ከቆሙ ትክክለኛው እኩልነትና አንድነት እውን ይሆናል። ከነዚህ ከቀደምት ከአባቶቻችን የምንማረው ነገር ቢኖር የአገርና የሕዝብ ችግር የሚፈታው በጉሳ ፖለቲካ ጥላቻን በማናፈስ እንዳልሆነ ልብ ልንለው ይገባል። በአገራቸን ለውጥ እንዲመጣ ከተፈለገ የግድ እርቀ ሰላም አስፈላጊ ነው። ኢትዮጵያ የእምነት መፍለቂያ ብልህና አዋቂ ሰዎች ስላሏት ይቅር መባባል የሚከብድ አይሆንም። አንዳንዶች በኢትዮጵያ ውስጥ ፈረንጆች በኢሕአዴግ ላይ ተጽኖ አድርገው ሰላም ሊያመጡ እንደሚችሉ ሲናገሩ ይደመጣሉ። ይህ በጣም የተሳሳተ ስሌት ነው፡፤ ከዚህ በፊት ፋሽስት ጣሊያን አገራችን በወረረበት ጊዜ ጃንሆን የውጭ አገር ፈረንጆችን እርዳታ በጠየቁ ጊዜ ምን መልስ እንደተሰጣቸው ማወቅ ያስፈልጋል። ፈረንጅ “ሰላቶ” ከራሱ ጥቅም ባሻገር ለኢትዮጵያ ጥቅም ያስባል ብሎ መገመት መጃጃል ይሆናል። በፈረንጅ ከማመን በራስ ሕዝብ ላይ በመተማመን የአገሩን ሰርዶ በአገሩ በሬ እንዲሉ መድሃኒቱ የራስ ሕዝብ ነው።
አንዳንድ ፖለቲከኞች የውጭ ዲፕሎማሲ እንደሚጠቅም ያምናሉ፤ ይህን እኔም እጋራዋለሁ። ይሁን እንጂ ከተሞክሮ አንፃር እውነታዎች ሲዳሰሱ አውሮፓና አሜሪካ 20 ዓመት መቀመጥ ብቻውን ለውጥ ይመጣል ብሎ ለመገመት ያዳግታል። ስለሆነም ትክክለኛ ለውጥ እንዲመጣ ከተፈለገ ለአገራቸውና ለሕዝባቸው ሲሉ የወንበር ጥም ሳያጠቃቸው አገራቸው ገብተው ሕዝባቸውን መታደግ አለባቸው። ሌላው የጠላቴ ጠላት በሚል በዋናነት ለአገራችን ውድቀትና ለባሕር በራችን መዘጋት ኤርትራ መሆኗ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከቶም የሚረሳው አይደለም። ስለሆነም ገና አማራጭ የለም በማለት ከኤርትራው ኢሳይያስ አፈወሪቂ ጋር ተባብሮ ኢትዮጵያን እታደጋለሁ ማለት የሚቻል አይመስለኝም። ከኢትዮጵያ ሕዝብ መረጃ እንዳገኘሁት ከሆነ በኤርትራ በኩል በሚደረገው ትግል ነፃ እወጣለሁ የሚል እምነት የለውም። እንዲያውም ወሬውን መስማት አይፈልግም። እውነቱ ይህ ነው። ከዚህ ቀደም የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንዲሉ በኤርትራ በኩል ከተቻለ ጥሩ ነው የሚል አመለካከት ነበረኝ። ግን ኢሳይያስን ማመን ጉም መጨበጥ ስለሚሆን በበኩሌ የኤርትራ ጉዳይ አያምረኝም።
በመጨረሻም፦ መንግሥት በዘረኝነት ሥልጣን ከአንዱ ወደ ሌላ እንዳይሸጋገር ቆርጦ መነሳቱ አሊ አይባልም። በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝብ ሳይወክላቸው አንዳንዶች እንገነጠላለን የሚል መርዝ እየረጩ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ስለዚህ ዘረኝነትና መገንጠል በዚህ ዓለም ላይ ለማንም አልበጀ። የሚያዋጣው ለችግር መፍትሄው ይቅርታ ነው። ቀጣዩ ትውልዱ ከዚህኛው ትውልድ የተሻለ እንዲሆን ከዚህ በፊት የነበረውን ጐጅ አስተሳሰብ በተሻለ ሁኔታ ሰርቶ ለሚቀጥለው ትውልድ የማስረከብ ኃላፊነት ያለበት ይህ ትውልድ ይመስለኛል። ለዚህ ተግባራዊነት ደግሞ የእያንዳንዱን ቆራጥ ውሳኔ ይጠይቃል። በብልሹ አስተዳደር ምክኒያት በራሱ አገር ኑሮ ላለመሞት የተሻለ አገር ፍለጋ መሄድ ተገቢ ቢሆንም ለችግሩ መፍትሄይ አይሆንም። ውጭ ሆኖ ትግል በታሪክ አልታየም።
ከዚህ ላይ ለእያንዳንዳችን የሚሆን ጥሩ ምሳሌ አለ። ማዘር ትሪስ እንዳለችው በዚህ ዓለም ላይ የበሽታዎች ሁሉ በሽታ ለማንም ሰው ምንም አይነት መፍትሄ የማይሰጥ ሰው ሆኖ መኖር ነው ያለችው ሊያነቃቃን ይገባል።
የሰው ልጅ የአንድን ሰው ችግር ለማቃለል እንደ ተፈጠረ አድርጐ ራስን ማየት መጀመር ወቅት አሁን ነው። የምሁር ማንነቱና መታወቂያው ለለውጥ ጥሩ ፈር ቀዳጅና ለችግሮች መፍትሄ ሰጭ ሲሆን ነው። መፍትሄ ሰጭ ካልሆነ ግን አልቻልኩም ብሎ ለሌላ ሰው መስጠት ይጠበቅበታል እንጂ መፍትሄ አልባ ሙጭጭ ማለት የለበትም። ስለሆነም ሁሉም ተቃዋሚዎች የታሪክ ሰው መባል ከፈለጉ የሕዝቡን ጀሮ ማዳመጥ አለባቸው። ለአገርና ለሕዝብ ሲባል እርቅ አድርገው ፕሮግራማቸውን አቻችለው ውጤት ሊያመጣ በሚያስችላቸው የትግል ስልት ላይ ወደፊት መገስገስ ይጠበቅባቸዋል። ሕዝቡም በተስፋ ከጐናቸው ይቆማል። ለሙሉ ፖለቲካ ሥራቸው አባላትም ደመዝ ሊከፍሉ እንደሚችሉ ከተሞክሮ መረዳት ይቻላል። ገና ለገና ላም አለችኝ በሰማይ ወተቷን አላይ እንዲሉ አውሮፓና አሜሪካ ተቀምጦ ፈረንጅ በኢሕአዴግ ላይ ተጽዕኖ ያደርጋል ብሎ የመጠበቅ ተስፋ መቆም አለበት። ፈረንጅ እኮ ጥቅሙን እንጂ የኢትዮጵያ መፈራረስ ደንታው አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ እምነቱ ትግሉ አገር ቤት መሆኑን ነው። ከዚህ ዘረኛ መንግሥት ለመላቀቅ መስዋዕት ግድ ይላል። ከዚህ ውጭ ሩቅ ሆኖ በሪሞት ኮንትሮል ትግል መምራት ከዚህ በፊት በታሪ አልታየም።
ስለዚህ ተቃዋሚዎች ሕዝቡን የማያዳምጡና የማይተባበሩ ከሆነ ሦስት አማራጭ እንዲኖራቸው ማስገደድ የሚያስፈልግ ይመስለኛል። አንደኛው ምርጫ ከሕዝባቸው ጐን ሆነው እያደራጁ እንዲያታግሉ፤ ሁለተኛው ምርጫ ይህን ማድረግ የማይችሉ ከሆነ አርፈው መቀመጥና ትግሉን ለሚችል ተቃዋሚ ቦታውን መልቀቅ ይሆናል፤ ሦስተኛው ምርጫ ኢንተርኔት ላይ ለሚያደርጉት ትግል ድጋፍ መንፈግ፤ ገቢያቸው እየነጠፈ ስለሚሄድ ባሉበት ደርቀው እንዲቀሩ ማድረግ።
ስለዚህ ያላቸው ምርጫ የራሳቸው ይሆናል ማለት ነው። ለዛሬ በዚህ አበቃሁ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!!!!

ኦሞት ኦባንግ – የታዳኝ አዳኝ ድራማ

ኦሞት ኦባንግ – የታዳኝ አዳኝ ድራማ

ኢህአዴግም በበኩሉ እያደናቸው ነው
Wanted omot obang olum



  • “ሁሉም ከህግ አያመልጡምና ዜጎች መረጃ በመሰብሰብ የቤት ስራችሁን ስሩ” ኦባንግ ሜቶ
  • ኦሞት ኦባንግ በዓለም ዓቀፍ ተቋማት ለፍርድ እንዲቀርቡ እየታደኑ ነው
ሰሞኑን አገር ጥለው መኮብለላቸው የተደመጠው የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦሞት ኦባንግ በተለያዩ የዓለም ዓቀፍ ተቋማት ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነ ታወቀ። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ፍትህ የተዛባባቸው ዜጎች ሁሉ መረጃ በማሰባሰብና ለድርጅታቸው በመላክ የዜግነት የቤት ስራቸውን እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። አቶ ኦሞትን ፍትህ ደጅ ለማቆም ከ19 ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በኅብረት እየሰሩ መሆናቸውም አመልክተዋል። በሌላም በኩል ኢህአዴግም “ነገር ሳይበላሽ” እያደናቸው እንደሆነ ተሰምቷል፡፡
በ2003 በጅምላ ለተጨፈጨፉና በሺህ ለሚቆጠሩ የአኙዋክ ተወላጆች መሰደድ ከመለስ ቀጥሎ ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሚባሉት አቶ ኦሞት፤ ሳምንት በፈጀ ግምገማ ከክልሉ ሊቀመንበርነታቸው መነሳታቸውና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው መመደባቸው ይታወሳል። “እውነተኛው ወያኔ” እየተባሉ የሚጠሩት አቶ ኦሞት ምንም እንኳ በሚኒስትርነት ደረጃ ቢመደቡም በሙስና ተወንጅለው እንደሚታሰሩ ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡ አይዘነጋም።
በሰኔ 10፤2005 ዓም (June 17, 2013) የጎልጉል ዘገባ ላይ እንደተጠቀሰው ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ አላግባብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ እንዲሁም በክልሉ የሚፈጸሙትን የተጭበረበሩ የበጀት አፈጻጸሞችንና ምዝበራዎችን የሚያጋልጡ ሰነዶችን በሚስጥር ተደራጅቶ ለኢህአዴግ የድርጅት ቢሮ ቀርቦ ነበር። የክልሉ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ ከፍተኛ ምስጢር ያላቸውን ሰነዶች በመያዝ ከመታሰራቸው በፊት መሰወራቸውን የጠቆመው ዘገባ “የቢሮ ሃላፊው ይዘው የተሰወሩት መረጃ አቶ ኦሞት የፈረሙባቸው ከፍተኛ የገንዘብ ሰነዶችና ሙስና የተከናወነባቸው የኮንስትራክሽንና የተለያዩ መረጃዎች ይፋ የሚያደርጉ ነበሩ። በወቅቱ “መረጃዎቹ አንድ ቀን ህዝብ ፍርዱን ይሰጥ ዘንድ ይፋ ይሆናሉ” ተብሎም ነበር። የመረጃ ምንጫቸውን ባይጠቅሱም አቶ ኦባንግ “ኦሞትን በተመለከተ ከበቂ በላይ መረጃ አለን፤ ህግ ፊት እናቀርበዋለን፤ በንጹን ደም ተጨማልቆና ህዝብ ላይ ግፍ ፈጽሞ መሰወር አይቻልም” በማለት በስልክ ለጎልጉል ተናግረዋል። አቶ ተስፋዬ ኢሬሳበድንገት ምሳ እየተመገቡ ከመርዝ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው በድንገት ማለፉ ይታወሳል።
ከታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ ም ጀምሮ ሟቹ አቶ መለስ በላኳቸው አስገምጋሚዎች ለሳምንት በተካሄደ አውጫጪኝ አቶ ኦሞት “የአኙዋክ ተወላጆችን አስጨፍጭፈሃል” የሚል መነሻውና ዓላማው ግልጽ ያልሆነ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። በወቅቱ ግምገማው ላይ የነበሩ እንዳሉት አቶ ኦሞት “እኔ በዚህ ጉዳይ ተጠያቂ ከሆንኩ መሳሪያና ወታደር የሰጠኝ መለስም ይታሰራል” በማለት መልስ ሰጥተው ነበር።
በወቅቱ አቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመሩት ድርጅት /አኢጋን/ አቶ መለስን በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ችሎት ተጠያቂ ለማድረግ ያቀረበው ማመልከቻ ተቀባይነት ያገኘበትና አቶ መለስ ላይ ክስ እንዲመሰረት ውሳኔ የተደረሰበት ዜና የተሰማበት ነበር። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የጋምቤላ ምንጮች “አቶ መለስ አቶ ኦሞትን በጭፍጨፋው ተጠያቂ በማድረግና ርምጃ በመውሰድ ራሳቸውን ጲላጦስ ለማድረግ የወጠኑት አካሄድ እንደሆነ የፌዴራል ሰዎች ነግረውናል። ኦሞትም በሙስና በዘረጋው መዋቅር እስከላይ ድረስ ዘመድና ተቆርቋሪ ስላበጀ መረጃው ደርሶት ነበር” ብለዋል። /በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የተመሰረተው ክስ መለስ ቢሞቱም እስካሁን ክፍት ነው/
Wanted omotበሌላም በኩል ወቅቱ በክልሉ ኢህአዴግ ለልማት በሚሰጠው ርዳታ ዜጎችን ለማፈንና ረግጦ ለመግዛት የሚያስችለውን ሃይል ያደራጅበታል በሚል ተቆርቋሪዎች መረጃ አስደግፈው ባቀረቡት ክስ ዓለም ባንክ አጣሪ የላከበት ነበር። ከዚሁ ጋር ተያይዞ መሬታቸውን፣ የትውልድ ቀያቸውን በአንጋቾች የተነጠቁ ምስኪን ዜጎች ድምጽ ዓለም አቀፍ ትኩረት አግኝቶ ኢህአዴግን ክፉኛ የተፈታተነበት ነበር። ለዚህ ይመስላል ኢህአዴግ በግምገማ በርካታ የክልሉን ሃላፊዎች ወረዳ ድረስ በመዝለቅ በሙስና ሰበብ ሲያባርርና ሲያስር፣ አቶ ኦሞትን ወደ ፌዴራል በማዛወር በቅርብ ይከታተላቸው ነበር። አቶ ኦሞት ወደ ፌዴራል ሲዛወሩ “የቤንሻንጉል ጉምዝ ፕሬዚዳንት በነበሩት አቶ ያረጋል አይሸሹ ላይ የተደረገው ይፈጸምባቸዋል” ተብሎ አስቀድሞ ተተንብዮ ነበር።
ለአብነት ከላይ በተዘረዘሩት መነሻዎችና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ሳቢያ የአቶ ኦሞትና የህወሃት ግንኙነት ማክተሙን የሚናገሩት ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች፣ “ቀደም ሲል ህወሃትን ሲያገለግሉ ኖረው መጨረሻቸው እስር እንደሆነው አራት የቀድሞ የክልሉ መሪዎች፣ ወይም እንደ አምስተኛው ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ ስደት እጣ ፈንታቸው ይሆናል” የሚል ቅድመ ትንበያ ነበር።
አቶ ኦኬሎ አኳይ በአኙዋክ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን የጅምላ ጭፍጨፋ አስመልክቶ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ክልሉን ወክለው የተዛባ መረጃ እንዲሰጡ ታዘው ነበር። በአቶ አባይ ጸሃዬና ገብረአብ በርናባስ መመሪያ መሰረት ግጭቱ በጎሳ ላይ የተመረኮዘ የርስ በርስ እንደሆነ፣ በግጭቱ 59 ሰዎች ብቻ ሲሞቱ አንድ ቤት መቃጠሉን እንዲናገሩ የተሰጣቸውን መመሪያ ያልተቀበሉት አቶ ኦኬሎ ህይወታቸው አደጋ ላይ በመውደቁ አገር ጥለው መሰደዳቸው ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ በተደጋጋሚ ገልጸው ነበር። ይሁን እንጂ አቶ ኦኬሎ አኳይ በስደት ሆነው በይፋ በዚህ ጉዳይ መግለጫ ለመስጠት አለመድፈራቸው ብዙዎችን ግራ ያጋባ ጉዳይ ሆኗል።
ኦሞት የት ናቸው?
አቶ ኦሞት የክልሉ የደህንነት ሃላፊና ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ባገለገሉበት ወቅት ፍጹም ታማኝ ስለነበሩ በ2005 የተሰጣቸው የክልል መሪነት ስልጣን ለህወሃት ለሰሩት ውለታ የተከፈለ ወሮታ እንደሆነ ተደርጎ ነው የሚወሰደው። በዚሁ መነሻ ይመስላል አብዛኛው የጋምቤላ ተወላጆች ለአቶ ኦሞት የከፋ ጥላቻ እንደነበራቸው የሚናገሩ ክልሉ ተወላጆች፣ ኦሞት ከአገር ኮበለሉ መባሉ አያስገርማቸውም።
አሁን ጥያቄው ኦሞት ከኢህአዴግ አፍንጫ ስር እንዴት አመለጡ? አሁን የት ናቸው? መጪው እጣ ፈንታቸውስ? የሚለው ነው። አዲስ አድማስ ባለፈው ቅዳሜ እትሙ አቶ ኦሞትን የግምባር ዜና አድርጎ ሲያቀርብ አገር ጥለው መኮብለላቸውን የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ማረጋገጣቸውን አስነብቧል። አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል እንደገለጹት አቶ ኦሞት ከሁለት ወር በፊት ለስልጠና አውሮፓ ሲመጡ በነበራቸው ቪዛ ከሁለት ሳምንት በፊት ዓርብ ቀን አገር ጥለው እንደወጡ መረጃው አላቸው።
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ከ19 የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ እየሰሩ መሆናቸውን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ ሜቶ “ኦሞት መለስ በህይወት እያለ ቢኮበልል መልካም ነበር። አሁን ከኦሞት የምንፈልገው ችሎት ፊት በወገኖቹ ላይና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ፣ ቶርቸር፣ እስር፣ ዝርፊያ፣ የመሬት ንጥቂያ፣ ወዘተ አስመልክቶ እንዲናዘዝ ነው” ብለዋል። ኮብላዩ አቶ ኦሞት የት እንደሚገኙ ተጠይቀው “አሁን እዚህ ነው የሚባልበት ደረጃ ላይ አይደለንም። ግን መሰወር የሚችል አይመስለኝም። በደም ተጨማልቆ በስደት ተበዳይ መስሎ መኖር አይቻልም። የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ከመለስ ጋር በተመሰረተው ክስ ላይ ኦሞት የተካተተ መሆኑ መዘንጋት የለበትም። እኛ እንኳ ዝም ብንል ፍትህ በርዋን አትዘጋም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ጎልጉል ባሰባሰበው መረጃ አቶ ኦሞት አገር ጥለው የወጡት ከሁለት ሳምንት በፊት ሲሆን አንድ ሳምንት ቢዘገዩ ኖሮ እስር ቤት ይገቡ ነበር። አስቀድሞ በደረሳቸው መረጃ መሰረት አቶ ኦሞትን እስር ቤት እንዲወረወሩ የሚያዘው የአስር ማዘዣ የሚቆረጥበት ግምገማ ተዘጋጅቶ ነበር። እሳቸው አስቀድመው አገር ጥለው በመውጣታቸው ግምገማው ተስተጓጉሏል። ግምገማው የዓለም ባንክ አጣሪ ቡድን በትላንትናው ዕለት ኢትዮጵያ ሲገባ በሙስናና በሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ ኢህአዴግ ርምጃ በመውሰድ ዝግጅት አጠናቆ ለመጠበቅ የሚረዳው ነበር። ግን አልሆነም።
በጋምቤላ በኢቨስትመንት ስም መሬት ወስደው ከሚሰሩት መካከል 70 ከመቶ የሚሆኑት የቀድሞ የህወሃት ታጋዮችና የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው አቶ ኦሞት የሚደረግባቸውን ክትትል አልፈው አገር ሊወጡ እንደቻሉ ግምት አለ። አሁን “ባለሃብት” የሚባሉት እነዚህ ክፍሎች ባላቸው መዋቅር ሳቢያ አቶ ኦሞትን ሊታደጓቸው እንደሚችሉ ከግምት በላይ የሚናገሩ አሉ።
አቶ ኦሞት ሆላንድ ገብተዋል የሚሉም አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ አውሮፓ ሊገቡ አይችሉም በማለት ግምቱን የሚያጣጥሉ አሉ። እነዚህ ክፍሎች ወደ ማሌዢያ ሄደዋል የሚለውን ምንጭ ይደግፋሉ። በስፋት እንደሚነገረው ከሆነ አቶ ኦሞት ኤዢያ እንደሚሄዱ የሚያጠናክሩ ምልክቶች አሉ። አብዛኛው የኢህአዴግ ባለስልጣኖች በማሌዢያ ባንኮች ገንዘብ አላቸው። አቶ ኦሞትም በተመሳሳይ የማሌዢያ ባንክ ተጠቃሚ ናቸው ተብሎ እንደሚገመት የሚቀርቧቸው ይናገራሉ። በተመሳሳይ በኢንቨስትመንት ስም የተወዳጇቸው ባለሃብቶች በኤዢያ ከለላ ሊሆኗቸው ስለሚችሉ የመጀመሪያ ምርጫቸው ኤዢያ እንደሚሆን ይስማማሉ።
ለጎልጉል ማንነታቸውን ሳይገልጹ መረጃ የሰጡ የኢህአዴግ ሰው እንዳሉት “ኦሞት ርቆ አልሄደም ይያዝል” በማለት ግምታቸውን ሰጥተዋል። ጉዳዩን በቅርብ እንደሚከታተሉ የገለጹት እኚህ ሰው “ኦሞት ብዙ ጉዳዮችን እንዳያበለሽ ጥንቃቄ ሲደረግ ነበር። እንዴት ለጊዜውም ቢሆን ተሰወረ?” የሚለው መነጋገሪያ መሆኑን ግን አልሸሸጉም። ኦሞት በወቅቱ የፈጸሙትን ከ400 በላይ የአኙዋኮችን ጭፍጨፋ፣ የተሳተፉበትን ሙስና፣ የመሬት ነጠቃ፣ ግድያ፣ ወዘተ የወንጀል ምስጢር በማውጣት ኢህአዴግን አሳጥተው ፍርድ እንዲቀልላቸው መደራደሪያ ከማድረጋቸው በፊት ኢህአዴግ የራሱ አደን አጠናክሮ እንደሚገኝ ተጨማሪ ዘገባዎች አሉ፡፡
አቶ ኦባንግ ሜቶ የኦሞት መሰወር አያስጨንቅም ባይ ናቸው። ኦሞትን ፍትህ አሳድዳ ትይዘዋለች የሚሉት አቶ ኦባንግ ትኩረታቸው ወንጀል የተፈጸመባቸው በሙሉ መረጃ በመሰብሰብና ወደ ጋራ ንቅናቄው በመላክ እንዲተባበሩ የመነሳሳታቸው ጉዳይ ላይ ነው። ህወሃቶች ወንጀል አሰርተው፣ መጨረሻ ላይ ፍትህ ወዳድ ለመምሰል በወንጀል ያጨማለቋቸውን ሰዎች ህግ ፊት አቅርበው እንደሚያስፈርዱባቸው ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “ሌሎች ከዚህና ከቀድሞው ተሞክሮ ተማሩ። ኦሞትን ፍትህ አደባባይ ለማውጣት የሚሰራው ስራ ወንጀለኞችን ለመፋረድ የምናደርገውን ትግል አንድ ርምጃ ያሳድገዋል። እንደ ኦሞት ያሉት ወንጀለኞች ካሉበት ይለቀማሉ። ይህንን ማድረግ አቅም አለን። በደም ተጨማልቆ በስደት መኖር አይቻልም። ሌሎችም ካሁኑ ንስሃ ግቡ፤ ህብረተሰባችሁን አስቀድሙ” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ህወሃትም ሆነ ኢህአዴግ በራቸውን መክፈታቸው ወይም ለውጥ እንዲመጣ እንዲፈቅዱ የሚገደዱበት ዘመን መቃረቡን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “ነጻ ውጡና ህዝባችሁን ነጻ አውጡ፣ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ለወንጀለኞች ቦታ የላትም፣ ትፋረዳቸዋለች” ሲሉ በድጋሚ ህዝብ በወንጀለኞች ላይ መረጃ በማሰባሰብ የቤት ስራውን በወጉ እንዲሰራ ጠይቀዋል።

የቢሮ ኃላፊው በሙስና ላይ ምስክር ሳይሆኑ ተገደሉ

“ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ”
food
June 17, 2013 07:55 am By  3 Comments (Edit)
በነበራቸው የስራ ሃላፊነት በድብቅ መረጃ ሲያሰባስቡ ቆይተው ለመንግስት ካጋለጡ በኋላ ራሳቸውን ደብቀው የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሣ ምሳ እየተመገቡ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ። አቶ ተስፋዬ ሰኞ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ከኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ቀጠሮ ይዘው ነበር።
በቅርቡ ወደ ፌደራል መንግስት የተዛወሩት የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኡሞት ኦባንግ፣ ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ አላግባብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ እንዲሁም በክልሉ የሚፈጸሙትን የተጭበረበሩ የበጀት አፈጻጸሞችንና ምዝበራዎችን የሚያጋልጡ ሰነዶችን በሚስጥር በማደራጀት ለኢህአዴግ ያቀረቡት አቶ ተስፋዬ አሟሟታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ ከፍተኛ ምስጢር ያላቸውን ሰነዶች በመያዝ ከመታሰራቸው በፊት መሰወራቸውን፤ “የቢሮ ሃላፊው ይዘው የተሰወሩት መረጃ አቶ ኦሞት የፈረሙባቸው ከፍተኛ የገንዘብ ሰነዶችና ሙስና የተከናወነባቸው የኮንስትራክሽንና የተለያዩ መረጃዎች ናቸው። መረጃዎቹ አንድ ቀን ህዝብ ፍርዱን ይሰጥ ዘንድ ይፋ ይሆናሉ” በሚል ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ በ (ጥቅምት 19፤2005/October 29, 2012) መዘገቡ ይታወሳል
ቀደም ሲል የጋምቤላ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ከላይ የተጠቀሰውን የሙስና ወንጀል በማጋለጣቸው ጋምቤላ መኖር ሳይችሉ ቀርተው ራሳቸውን ሸሽገው ለመኖር ተገደው እንደነበር የሚያውቋቸው ለጎልጉል አስረድተዋል።
“አቶ ተስፋዬ ሙስናን በማጋለጣቸው በፍርሃቻ ራሳቸውን ደብቀው ሊኖሩ አይገባም” በማለት ኢህአዴግ ከለላ እንደሚሰጣቸው ቃል በገባላቸው መሰረት ከተሸሸጉበት የወጡት አቶ ተስፋዬ ሰንጋተራ ትንሳዔ ሆቴል ከጋምቤላ ልጆች ጋር መገናኘት ይጀምራሉ።
ባለፈው ሳምንት ከፌዴራል የጸረ ሙስና ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ ከያዙ በኋላ ኮሚሽነሩ በድንገት ለለቅሶ ወደ ጎንደር በመሄዳቸው ቀጠሮው ለሳምንት ይራዘማል። ለሰኞ (ሰኔ10፤2005) አዲስ ቀጠሮ ይይዛሉ።
በስልክ ያነጋገርናቸው ትንሳዔ ሆቴል አካባቢ እንደነበሩና ለጉዳዩ ቅርበት እንዳላቸው የሚገልጹ የጋምቤላ ተወላጅ የስራ ሃላፊ እንዳሉት አቶ ኦሞት ኦባንግ ለአቶ ተስፋዬ ስልክ ደውለው ነበር። አቶ ተስፋዬ ህይወታቸው ከማለፉ ሁለት ቀን በፊት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኦሞት በስልክ ተማጽንዖ አቅርበው ነበር።
አቶ ኦሞት “እውነት ነው ጸረ ሙስና ኮሚሽን ቀጠሮ የያዝከው?” በማለት ይጠይቃሉ
“አዎ! እውነት ነው” በማለት አቶ ተስፋዬ መልስ ይሰጣሉ።
አቶ ኦሞት መልሰው “እንግዲያውስ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከመግባትህና ከማነጋገርህ በፊት ሁለታችን መገናኘት አለብን። የምንነጋገረው ነገር አለ” የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ። አቶ ተስፋዬ ስለ ስልክ ልውውጡ እንደነገሯቸው የተናገሩት እኚሁ ሰው፣ አቶ ኦሞት በስልክ ደጋግመው በመደወል ያቀረቡትን የ”እንነጋገር” ጥያቄ አቶ ተስፋዬ አልቀበልም ይላሉ።
ጋምቤላ ስራቸውን ለቀው ራሳቸውን ደብቀው የኖሩት በእርሳቸው ምክንያት መሆኑን፣ ፍትህ እንደሚፈልጉ፣ አሁን ለመነጋገር ጊዜው እንዳልሆነ፣ ዘርዝረው ለአቶ ኦሞት መናገራቸውን ያወሱት የጎልጉል ምንጭ፣ ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው አቶ ኦሞት በንዴት ተዛልፈው ነበር።
ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው እንግዲህ አቶ ተስፋዬ ትንሳዔ ሆቴል ሰዎችን በመላላክና በመታዘዝ ከሚኖር አንድ የጋምቤላ ሰው /አቶ ተስፋዬ የሚረዱት በምግባር ጉዳይ የሚታማና ጸበኛ የሚባል ሰው ነው/ አብረው ተቀምጠው ምሳ እየበሉ ሳለ አቶ ተስፋዬ አረፋ ይደፍቃቸዋል። ወዲያው ከተቀመጡበት ተንሸራተው መሬት ይወድቃሉ። ቀጥሎም ሰውነታቸው ይዝልና ኮማ ውስጥ ይገባሉ። ከአፋቸው እየተዝለገለገ የሚወጣው ፈሳሽ በመጨመሩና የተለያየ ርዳታ ቢደረግላቸውም ሊተርፉ ስላልቻሉ ሆስፒታል ተወስደው ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።
አቶ ተስፋዬ ሆስፒታል ከመድረሳቸው በፊት እንደሞቱ የሚናገሩት የጎልጉል ምንጭ አሟሟታቸው ከመርዝ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተናግረዋል። አቶ ተስፋዬ በሙስና ወንጀል ላይ ያሰባሱትን መረጃ ለተለያዩ አካላት የበተኑ ስለሆነ እሳቸውን በመግደል ማድበስበስ እንደማይቻል አስታውቀዋል። አቶ ተስፋዬ ሙስና ካጋለጡ በኋላ መሰወራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው። በተያያዘ በጋምቤላ ኢንቨስትመንት ላይ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ውስጥ ከ70በመቶ በላይ የሆኑት የህወሓት የቀድሞ ታጋዮች የነበሩና የክልል አንድ ተወላጆች መሆናቸው የአቶ ተስፋዬን አሟሟት ይበልጥ ውስብስብ እንዳደረገው አስተያየት እየተሰጠ ነው፡፡
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ “የአቶ ተስፋዬ ሞት አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው። ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ” በማለት ስለ አቶ ተስፋዬ ሞትና አሟሟት መረጃ እንደደረሳቸው አስታውቀዋል።
“አቶ ተስፋዬ ለእውነት ሲል ሞቷል። ኢህአዴግ ውስጥ በርካታ የወንጀል መረጃ ያላቸው ወገኖች አሉ። እንዲህ ያሉ ዜጎች በየትኛውም ዘመን አይረሱም። የቀን ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ስማቸውና ታሪካቸው ከጨዋነታቸው ጋር ተመልሶ ህያው ይሆናል። ሌቦችና ነፍሰገዳዮች ወደ ህግ ሲያመሩ፣ እንደ አቶ ተስፋዬ አይነቶቹ የመጪው ትውልድ ታላቅ ምሳሌ ሆነው እየተወደሱ ህያው ሆነው ይኖራሉ” የሚል አስተያየት የሰጡት አቶ ኦባንግ፤ አቶ ተስፋዬ ያሰባሰቧቸው የሙስናና ተመሳሳይ ወንጀሎች ማሳያ ሰነዶች እጃቸው ላይ ስላለ አቶ ተስፋዬን በመግደልና በማስገደል ወንጀል ማድበስበስ እንደማይቻል ተናግረዋል።
የአቶ ተስፋዬ የቀብር ስነስርዓት ጋምቤላ መፈጸሙን ለመረዳት ተችሏል። ቤተሰቦቻቸውን በማግኘት ሆስፒታሉ ስለ አሟሟታቸው የሰጠውን አስተያየት ጠይቀን ለመረዳት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካልንም።

Sunday, February 2, 2014

የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት በአሁኑ ሰዓት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ከአገር ኮበለሉ

የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት በአሁኑ ሰዓት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ከአገር ኮበለሉ 

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩትና በአሁኑ ሰዓት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት የተከበሩ አቶ ኡመድ ኡባንግ፤ ከአገር መኮብለላቸውን ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ 
አቶ ኡመድ ኡባንግ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከሃገር መውጣታቸውን የጠቆሙት ምንጮች፤ ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለሱ ለሚቀርቧቸው ሰዎች መናገራቸውን አመልክተዋል። 
የሚኒስትር ዴኤታውን መኮብለል በተመለከተ የጠየቅናቸው የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም፤ አቶ ኡመድ በስራ ገበታቸው ላይ እንደሌሉ ማረጋገጣቸውን ገልፀው መስሪያ ቤታቸው ለተለየ ተልዕኮ እንዳላሰማራቸውና ፈቃድ ሳይጠይቁ ከስራ ገበታቸው እንደቀሩ ተናግረዋል፡፡
ሚ/ር መስሪያ ቤታቸው ጉዳዩን እያጣራ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል፡፡ 
አቶ ኡመድ ከጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንትነት የተነሱት በክልል መንግስቱ የስራ አፈፃፀም ላይ ለአንድ ሳምንት ከዘለቀ ግምገማ በኋላ ሲሆን፤ ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናትም በዚሁ ግምገማ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል፡፡
AddisAdmass

ኢህአዴግ ሚኒስትሮቹን የግንባሩን ስራ እንዲያከናውኑ መደበ

ኢህአዴግ ሚኒስትሮቹን የግንባሩን ስራ እንዲያከናውኑ መደበ

ጥር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም :-ኢህአዴግ ፓርቲውን እንዲመሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ሌሎች ሁለት ሚኒስትር ዴኤታዎችን ባለፉት ወራት መሾሙን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቆሙ፡፡
ኢህአዴግ የመንግስት መዋቅርን ከፓርቲው መዋቅር ጋር አደበላልቆ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተደጋጋሚ ወቀሳዎችና ትችቶች እየቀረቡበት የቆየ ሲሆን በዚህ መልኩ ግልጽ የሆነ አደረጃጀት በመያዝ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮችን ሲመድብ ከአቶ መለስ ሞት በሃላ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሎአል፡፡
ቀደም ሲል የግንባሩ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመናብርት የግንባሩንና የአባል ፓርቲዎችን የሚመሩበት ሁኔታ የተለመደ ሲሆን የአሁኑ አደረጃጀት ግን ለየት የሚያደርገው በሚኒስትር ዴኤታ ማእረግ ጭምር በመንግስት ሃላፊነት ላይ የተመደቡ ሹማምንት ከነጥቅሞቻቸው ወደ ፓርቲው ሃላፊነት ተመድበው የመምጣታቸው ጉዳይ ነው፡፡ ሰዎቹ አብዛኛውን ጊዜያቸውን በፓርቲው ስራዎች እንደሚያጠፉ የጠቆሙት ምንጮቻችን ይህም ከመጪው ምርጫ ጋር በቀጥታ የተያዘ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የኢህአዴግ ጽ/ቤትን በበላይነት የሚመሩ ሲሆን አቶ ደስታ ተስፋው እና አቶ አማኑኤል አብርሃም በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ በጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ሆነው ግንባሩን በተለያዩ ሃላፊነቶች እንዲመሩ ተመድበዋል፡፡ እነዚህ ሹማምንት በመንግስት ገንዘብ፣ ነዳጅና ጊዜ የፓርቲ ስራዎችን ማከናወናቸው ፖለቲካዊ ሙስና መሆኑን ስለጉዳዩ ያነጋገርናቸው ወገኖች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢህአዴግ የተማሩ አባሎች የሉትም በሚል የሚደርስበትን ትችት አስተባብሎአል። ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ያልቻለው የተማሩ አባላትና ተሿሚዎች ስለሌሉት ነው በሚል ከተቃዋሚዎችና ከሌሎች ወገኖች የሚቀርብበትን ተደጋጋሚ ትችት ሃሰት ነው ብሎአል፡፡
በጠቅላ ሚኒስቴር ቢሮ የሕዝብ ተሳትፎና አደረጃጀት ሚኒሰትር ዴኤታና የኢህአዴግ ጽ/ቤት የህዝብና የውጪ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ደስታ ተስፋው ለመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ የዛሬ ዕትም በሰጡት መግለጫ በአሁን ወቅት የመልካም አስተዳደር ችግር አለባቸው የሚባሉት ስላልተማሩ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ መድረስ አያግባባም ካሉ በሃላ በአሁኑ ወቅት የኢህአዴግ አባላት የትምህርት ደረጃቸውን እያሻሻሉ ነው ብለዋል፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎች አጀንዳ አድርገው የሚያቀነቅኑት በፍጹም የተሳሳተ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በአባላት መካከል ውድድር ቢካሄድ የኢህአዴግ አባላት በትምህርትና በብቃት እንደሚበልጡ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
አንድ የኢህአዴግ ተሹዋሚ ሲያጠፋ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ወደሌላ ቦታ ማዛወር ሁኔታ እንዳለ ለቀረበላቸው ጥያቄም ሲመልሱ በኢህአዴግ ውስጥ አንድ ቦታ ብቁ ሆኖ ያልተገኘ ሌላ ቦታ ሄዶ እንዲሰራ እንደሚደረግ አምነዋል፡፡“በኢህአዴግ ድርጅት ውስጥ ባለው አሰራር መሰረት እያንዳንዱ ግለሰብ ተግባር ይሰጠዋል፡፡  የተሰጠውን ተግባር እንዴት እንደፈጸመ ይገመገማል፡፡በግምገማ ውጤቱ ስራውን በብቃት የፈጸመ አባል ተመስግኖ ለቀጣይ ስራ እንዲዘጋጅ ይደረጋል፡፡በአንጻሩ ደግሞ ድክመት የታየበት አባል እንዲያስተካክል የተለያዩ ተግባራት ይከናወናሉ፡፡ለምሳሌ ያህል ሂስ ይደረጋል፣እንደየሁኔታው በማስጠንቀቂያም ይታለፋል፡፡ የተመደበበት የስራ ቦታ ከብቃቱ ጋር የማይመጣጠን ሆኖ ከተገኘ ከቦታው ተነስቶ የሚችለው ስራ መደብ ላይ ይቀየራል ”ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት ትልቅ ችግር አድርጎ የሚያየው የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብን ነው ያሉት አቶ ደስታ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እየተባባሱ አለመምጣታቸውን፣እንዲያውም ወደመልካም አስተዳደር በጉዞ ላይ ነን በማለት እርስ በርሱ የተምታታ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡