Friday, January 10, 2014

የምንናገርበትን የመገናኛ ብዙሃን ማንም እንዲመርጥልን ወይም እንዲወስንልን አንፈቅድም!

የምንናገርበትን የመገናኛ ብዙሃን ማንም እንዲመርጥልን ወይም እንዲወስንልን አንፈቅድም!






January 10, 2014
ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ጥር 1 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የብሔራዊ ደህንነት መረጃ እና የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል የጋራ ኃይል አድርጎ ራሱን የሚጠራ አካል የዜጎችንና የተቋማትን ሕገ-መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ መብት በመጣስ ጥፋተኝነታቸው በፍርድ ቤት ሳይወሰን ወንጀለኛ ሲያደርጋቸውና ስማቸውን ሲያጎድፍ ማየት እየተለመደ የመጣ ተደጋጋሚ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ይህ ከላይ ከተጠቀሱት ሁለት ተቋማት ተውጣጥቶም ይሁን ተቀናጅቶ የሚሰራ አካል በተደጋጋሚ ጊዜ በሽብር ወንጀል ጠርጥሬአቸዋለሁ የሚላቸውን ሁሉ በመክሰስ ወደ እስር ቤት እንዲወርዱ እያደረገ ጉዳያቸው የፍርድ ቤት ውሳኔ ሳያገኝ እንደፈለገ በሚቆጣጠረው ወይም በሚያዘው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት አማካኝነት የፈለገውን ዓይነት ፍረጃና ሥም ማጥፋት ሲያካሒድባቸው ቆይቷል፡፡
ይህ ራሱን ከሕግ በላይ የሰቀለ አካል ያለምንም ገደብ ከሚሰራቸው ተግባራት እንዲታቀብ በሕግ የሚያስቆመው በመጥፋቱ እስካሁን የፈፀማቸውን የማንአለብኝነት ተግባራት እንደጥፋት ሳይሆን እንደ መልካም ሥራ ቆጥሯቸው በተመሳሳይ የሥም ማጥፋትና የፍረጃ ተግባሩ እንዲገፋበት አድርጎታል፡፡ በዚሁም መሰረት ታህሳስ 25 ቀን 2006 ዓ.ም ምሽት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባስተላለፈው የዘጋቢ ፊልም ፕሮፓጋንዳ አሸባሪ ያላቸውን ድርጅቶችና ግለሰቦች አድርሰውታል ያለውን ጥፋት በዝርዝር አቅርቧል፡፡ ፓርቲያችንን በዚሁ ዘገባ ከተጠቀሱት “አሸባሪ” ድርጅቶች ጋር በማገናኘት ስም ለማጉደፍና ለማስፈራራት የተደረገውን መፍጨርጨር አይተናል፣ ሰምተናል፣ ተገርመናል በመጨረሻም አዝነናል፡፡
በዘጋቢ ፊልሙ የቀረቡ ፓርቲያችንን የማይመለከቱ ጉዳዮችን ትተን ከፓርቲያችን ጋር በማገናኘት የተጠቀሰው “ኢሳት” የተባለ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ መንግስት በሽብርተኝነት ከተፈረጀ ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገለትና በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች በተለይም ሰማያዊ ፓርቲ በዚህ የመገናኛ ብዙሃን እንዳንጠቀም የማስጠንቀቂያ ዛቻ ተላልፎልናል፡፡ ይህ አስፈራሪ አካል ራሱን ሕግ አውጭና ሕግ ተርጓሚ በማድረግ የፈለገውን አካል ለመፈረጅ፣ ለመክሰስና ለመፍረድ ሥልጣኑን ከየት እንዳገኘ የማይታወቅ ሲሆን የዚህች ሐገር ዜጎችም ሃሳባችንን የምንገልፅበትንና የማንገልፅበትን የመገናኛ ብዙሃን እየመረጠልንና እየወሰነልን ይገኛል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንዲህ ዓይነቱን የእብሪት መልዕክት ከተራ ርካሽ ፕሮፓጋንዳነት የማያልፍ የሕግና የዲሞክራሲያዊ መብት ገደብን ካለማወቅ የሚመነጭ አስተሳሰብ ነው ብሎ ያምናል፡፡
የገዥው ቡድን ሰዎች ሀሳብን በሃሳብ ማሸነፍ እንደማይችሉ ስለሚያውቁት የቀራቸው አማራጭ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ሃሳባቸውን የሚያሰራጩባቸውን መንገዶች መዝጋት ብቻ መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡ ነገር ግን ማንም አካል በሕግም ሆነ በሞራል ተጠያቂ የሚሆነው የሚያስተላልፈው መልዕክት ይዘት የሌሎችን ዲሞክራሲያዊና ሞራላዊ መብት የሚጋፋ መሆን አለመሆኑ እንጂ ገዥው ቡድን በጠላው ወይም በወደደው የመገናኛ ብዙሃን መልዕክቱን ማስተላለፍ አይደለም፡፡ መልዕክትን የገዥው ቡድን ሰዎች በጠሉት የመገናኛ ብዙሃን ማስተላለፍ በራሱ ወንጀለኛ ወይም ሽብርተኛ ለማድረግ የሚያበቃ ምንም ዓይነት የሕግ መሰረት የለም፡፡ ማንም መልዕክት የሚያስተላልፍ አካል የሚያሰራጨው ሃሳብ የሌሎችን ዲሞክራሲያዊና ሞራላዊ መብት የሚጋፋ ከሆነ መልዕክቱ የተላለፈበት መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ይሁን ሌላ ህጋዊ የተባለ የመገናኛ ብዙሃን መሆኑ ብቻ መልዕክት አስተላላፊውን አካል ከተጠያቂነት ሊያድን እንደማይችልም ለማንም የተሰወረ ይሆናል የሚል እምነት የለንም፡፡
በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ መልዕክቱን የሚያስተላልፍበትን መገናኛ ብዙሃን ማንም አካል እንዲመርጥለት ወይም እንዲወስንለት የማይፈልግ መሆኑን ግልፅ እያደረገ በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠውን ማንም ሰው በመረጠው መንገድ ሃሳቡን የማስተላለፍ መብቱን በመጠቀም በኢሳትም ሆነ እድሉን ካገኘ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አቋሙንና እምነቱን ማስተላለፍ የሚቀጥል መሆኑን ማረጋገጥ ይወዳል፡፡ በዚሁ አጋጣሚም የፓርቲያችንን መልካም ስም በሃሰት ለማጉደፍ የተሰነዘሩ ቃላትን በቀላሉ የማንመለከታቸው መሆኑን ሕግ ባለበት ሐገር ራስን ከሕግ በላይ በማስቀመጥ ማንንም አካል መፈረጅና ስም ማጉደፍ በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን የዘጋቢ ፊልሙ ባለቤቶች እንዲያውቁትና ወደፊትም ተመሳሳይ ድርጊት ከመፈፀም እንዲቆጠቡ እናሳስባለን፡፡
ጥር 1 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ

አቶ ያረጋል አይሸሹምን ጨምሮ 6 ግለሰቦች ከ6 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራተ ተቀጡ

አቶ ያረጋል አይሸሹምን ጨምሮ 6 ግለሰቦች ከ6 እስከ 15 

ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራተ ተቀጡ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 2 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በጨረታ ሂደት የሙስና  ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው 6 ግለሰቦች ዛሬ ከ6 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራተ ተቀጡ።
ተከሳሾቹ አቶ ያረጋል አይሸሹም የቀድሞ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ፣ የክልሉ የትምህርት ቢሮ ሃላፊና የክልሉ ምክር ቤቱ አፈጉባኤ የነበሩት አቶ ሀብታሙ ሂካ ፣ የጌድዮን ደመቀ አማካሪ ድርጅት ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ ጌድዮን ደመቀ፣ አቶ አሰፋ ገበየሁ የአቶ ጌድዮን አማካሪ ፣ አቶ ገዛኧኝ አድገ እና አቶ መክብብ ሞገስ በስራ ተቋራጭነት የሚሰሩ ናቸው።
በ1997 ዓ.ም ከክልሉና ከፌደራል መንግስት በተገኘ የ79 ሚሊዮን ብር በጀት የአሶሳ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ፣ የግልገል በለስ ማሰልጠኛ ኮሌጅና የጣና በለስ ሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ግንባታ ፕሮጀክት እንዲከናወን አቶ ያረጋል አይሸሹም የሚመሩት የክልሉ ካቢኔ ይወስናል።
በግልፅ ጨረታ ወጥቶ ተጫራቾች ተወዳድረው ግንባታው መከናወን ሲገባው ፥ ባልተገባ መንገድ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሽ በፈጠሩት የጥቅም ትስስር ፤ የጌድዮን ደመቀ አማካሪ ድርጅት እንዲያሸንፍ ይደረጋል።
የክልሉ መንግስት የግዥ ስርዓት መመሪያ ከ300 ሺህ ብር በላይ የሆነ ግዥ ሲፈፀም የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ማፅደቅ አለበት የሚል ቢሆንም ፥ ከተከሳሾቹ አቶ  ያረጋል አይሸሹምና አቶ ሀብታሙ ሂካ ከባለሃበቶቹ ጋር በመመሳጠር ጌድዮን ደመቀ አማካሪ ድርጅት ያለግልፅ ጨረታ እንዲያሸንፍና ሶስቱንም ፕሮጀክቶች እንዲሰራ ያደርጋሉ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ከ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ክፍያ ተጫራቹ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን ፥ በ13 ወራት ይጠናቀቃል ተብለው ውል የተገባባቸው ፕሮጀክቶች ከ5 ዓመት በላይ አስቆጥረዋል ፤ ጨረታውን አሸነፈ የተባለው ድርጀትም በህገወጥ መንገድ እንዲያሸንፍ ከመደረጉም በላይ ደረጃው ፕሮጀክቶቹን ለመገንባት የሚያስችል አለመሆኑም በክስ መዝገቡ ተጠቅሷል።
የፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ አቶ ያረጋል አይሸሹምና አቶ ሀብታሙ ሂካን ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል ሌሎች ባለሀብቶችን ደግሞ  በመመሳጠር በዚህ ወንጀል በመሳተፋቸው ከሷቸዋል።
እንዲከሰሱ ካስቻሏቸው ነጥቦች መካከል በ13 ወራት ይጠናቀቃል ተብለው ውል የተገባባቸው ፕሮጀክቶች ከ5 ዓመት በላይ መጓተታቸው ፣ በተጨማሪ 7 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለተቋራጩ መከፈሉ ፣ እነዚህ ባለሀብቶች በተለያየ ጊዜያት ለአቶ ያረጋል አይሸሹምና ለአቶ ሀብታሙ ሂካ ጉቦ መስጠታቸው ፣ የጨረታ መመሪያ ደንብ መጣስና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ይጠቀሳሉ ።
መዝገቡን ሲመረምር የቆየው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ባለፈው ህዳር 11 2006 አቶ ያረጋል አይሸሹም ፣ አቶ ገዛኧኝ አድገና  አቶ መክብብ ሞገስን በአቃቤህግ ከተመሰረተባቸው ክሶች በአንድ ብቻ ጥፋተኛ ናቸው ሲል ፥ አቶ ሀብታሙ ሂካ ፣ ጌድዮን ደመቀና አቶ አሰፋ ገበየሁን በ3 ክሶች ነበር ጥፋተኛ ያላቸው።
በዚህ መሰረት ዛሬ ከሰዓት ችሎቱ የተከሳሾችን የቅጣት ማቅለያ ከግምት በማስገባት አቶ ያረጋል አይሸሹምን በ7 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ20 ሺህ ብር ፣ አቶ ሀብታሙ ሂካን በ15 ዓመት ፅኑ እስራት እና  በ45 ሺህ ብር ፣አቶ አሰፋ ገበየሁን በ15 ዓመት ፅኑ እስራትና 60 ሺህ ብር ፣ አቶ ጌድዮን ደመቀን በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እና 60 ሺህ ብር ፣ አቶ ገዛኧኝ አድገ እና አቶ መክብብ ሞገስን እያንዳንዳቸው በ 6 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ25 ሺህ ብር እንዲቀጡ ወስኗል።
በመዝገቡ በ7ኛ ተራ ቁጥር ተጠቅሶ የነበረው የአቶ ሀብታሙ ሂካ ወንድም አቶ ሀብተገብርኤል ሂካ ህዳር 11 ፣ 2006 ዓ.ም በዋለው ችሎት በብይን በነፃ መለቀቁ ይታወሳል

Thursday, January 9, 2014

የኖረው ወያኔ በራሱ ጦር ካምፕ ውስጥ የተገኘውን አስከሬን መደበቅ ለምን አሰፈለገው?

የኖረው ወያኔ በራሱ ጦር ካምፕ ውስጥ የተገኘውን አስከሬን መደበቅ ለምን አሰፈለገው?
26351fb59e29fb0a1375427042
January 9, 2014
አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚገኘው የክብርዘበኛ ጦር ካምፕ ውስጥ ማንነታቸው ያልታወቁ የ6 ዜጎች አስከሬን ለመንገድ ሥራ በተሠማሩ ቆፋሪዎች አማካኝነት መገኘቱ የሰሞኑ አሳዛኝ ዜና ነው።
አንድ አይነት ቀለም ባላቸው ብርድ ልብሶች ተጠቅልለው ከተገኙ 6 አስከሬኖች የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰለባዎች ታስረውበት የነበረው የእጅ ሰንሰለታቸው እንኳ እንዳልወለቀና ከተቀሩት የአንዱ እጆች ደግሞ የፍጥኝ ወደ ኋላ እንደታሰሩ መገኘታችው ግድያው በቅርብ እንደተፈፀም አንዱ አስረጂ ነው።
በእንዲህ አይነት ጭካኔ የተገደሉ ዜጎች አስከሬን መገኘት በመንግሥት ተብየው አካል ካለመገለጹም በላይ ግቢውን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው 3ኛ ክፈለ ጦርም ሆነ በግብር ከፋይ ገንዘብ የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን እስከዛሬ አንድም ቃል መተንፈስ አለመፈለጋቸው ጉዳዩን እጅግ የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን የሚያስገርምም አድርጎታል። ይባስ ተብሎም በመንገድ ሥራ ቁፋሮው የበለጠ አስከሬን ሊወጣ ይችላል በሚል ስጋት አካባቢው በፖሊስ እንዲታጠር ከተደረገ በኋላ ሥራውም እንዲቋረጥ ተደርጓል።
በፓለቲካ መስመር ልዩነት ምክንያት ደርግ ያለ ርህራሄ የጨፈጨፋቸውን ከመቃብር እያወጣ ዘመድ አዝማድ በማላቀስ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲዳክር የኖረ አገዛዝ በእንዲህ አይነት አሳዛኝ ሁኔታና አጋጣሚ የተገኘውን የጅምላ አስከሬን አይቶ አንዳላየ ለማለፍ መሞከሩ ለምን ይሆን?
አብዛኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ እንደሚያስታውሰው የክብር ዘበኛ ጦር ካምፕ በመባል የሚታወቀው የጃን ሜዳ 3ኛ ክፍለ ጦር ግቢ ድህረ ምርጫ 97 ወያኔ ለጅምላ እስር ቤትነት ከተጠቀመባቸው የማጎሪያ ቦታዎች አንዱ ነበር። ከዚያን ጊዜ በፊትና በኋላም ቢሆን ካምፑ በወያኔ ጠላትነት ተፈረጀ በጸጥታ ሠራተኞች ከታገቱ በኋላ አድራሻቸው እስከዛሬ ተሰውሮ ላሉ በርካቶች በምስጢር እስርቤትነት በማገልገል ላይ ከሚገኙ ወታደራዊ ካምፖች አንዱ እንደሆ ይታወቃል።
ዘመድ አዝማዶቻቸው ይመለሳሉ ብለው ሲጠብቋቸው ሳይመለሱ እንደወጡ የሚቀሩ በርካታ ዜጎች አሉ። በእንዲህ ሁኔታ ወጥተው ከቀሩ መካከል ከሰሞኑ የስድስቱ መቃብር በአጋጣሚ ተገኝቷል። የተገነዙበት ብርድ ልብስ ይነትብና ምንም ዓይነት ብልሽት ሳይደርስበት መገኝቱ ግዲያው በህወሃት ዘመነ መንግስት ስለመፈፀሙ ጥሩ ማስረጃ ነው። ለህወሃት ሰው መግደል ሥራ እንጂ ወንጀል አይደለም። በህወሃት ነፍሰ ገዳይ ይሞገሳል ይሾማል እንጂ አይወቀሰም አይጠየቅም። የስድስቱ ስዎች አስከሬን ሲገኝ መንግስትነኝ የሚለው ህወሃት አይቶ እንዳላየ መሆን ብቻ ሳይሆን ሌሎች አካላትም የሥፍራውን ሚስጢር እንዳያዩ ከልክሏል።በቁጥጥሩ ሥር ያሉ መገናኛ ብዙሃንም ዜናውን እንዳይናገሩ ታግደዋል። ህወሃት ከሚሰራቸው አስገራሚ ወንጀሎች መካከል አንዱይሄው ነው። ይሄ ግድያ በሌላ አካል ተፈፅሞ ቢሆን ኑሮ በረከት ስምዖንና እና ሺመልስ ከማል እየተፈራረቁ ያደነቁሩን ነበር።ይሄ የራሳቸው የእጅ ሥራነውና አይነገርም። የሄንንም የሚናገር እንደ ኢሳት ያለ ነፃ ሚዲያ ካለም ይታፈናል። አሸባሪም እየተባለ ይፈረጃል።
ግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እነዚህ ዜጎች በህወሃት ተግድለው እንደተጣሉ ያምናል። ውሎ አድሮ እውነቱ እስከሚወጣ ድረስ ግን ዜጎች በሙሉ ይሄን ግድ በተመለከተ መረጃ የመሰብሰብና የማሰረጫት ሥራችውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እናሳስባለን። ይሄን ወንጀል የፈፀሙ አካላት መጠየቅ አለባቸው። የዜጎች ደም እንዲሁ በከንቱ ፈሶ መቅረት የለበትም።
ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ጥቅም እንታገላለን የሚሉ የፖለቲካና የስቪክ ድርጅቶች እንዲሁም ለሰው ልጆች የሰብአዊ መብት የሚሟገቱ ሁሉ የተገኘው አስከሬን በአስቸኳይ ተመርምሮ ማንነታቸው ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲገለጽ፤ ተጨማሪ አስከሬን ሊገኝ ይችላል በሚልስጋት የመንገድ ቁፋሮውን ከሰዎች እይታውጪ ለማካሄድ እንዲቋረጥ የተደረገው ሥራ ለህዝብ እይታ ግልጽ በሆነመንገድ በአስቸኳይ እንዲጀመር የመጠየቅ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ግንቦት 7 ያሳስባል::
በዚህአጋጣሚ ወያኔ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜጀምሮ በሱማሌ፣ በጋምቤላ፣ በአዋሳ፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባና ሌሎች የአገራችን ክፍሎች በጠራራ ጸሃይ ካስጨፈጨፋቸው በተጨማሪ በፖለቲካ እምነታቸው ምክንያት ታግተው በየእሥርቤቱ የተወረወሩትንና ከታገቱበት ዕለት ጀምሮ እስከ ዛሬ የደረሱበት ያልታወቁ ወገኖቻችንን ዝርዝር በአስቸኳይ ያሳውቅ ብለን አንመክረውም።እኛ ግን ህወሃት የደበቀውን ወንጀል ሁሉ ህዝብ እንዲያውቀው ለማድረግ ያለምንም ማቅማማት ጠንክረን እየሰራን ነው። መንግስት ነኝ ብሎ በሥልጣን ላይ የሚወጣ ማንኛውም አካል የህዝብ አገልጋይ እንጂ ነፍሰገዳይ እንዳይሆን የጀመርነው ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል።
እንግዲህ ህወሃት በህዝባችንና በአገራችን ላይ የሚፈጽመውን ሰቆቃ ለማስቆም ግንቦት 7 የጀመረውን የነጻነት ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል እያስታወቅን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንዲህ በየቦታው ተገድሎ ከመጣል ራሱን ለመታደግ ሲል የነፃነቱ ትግል አካል እንዲሆን ጥሪያችንን አሁንም ደግመን እናቀርባለን::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

Ethiopia’s Anti-Terrorism Proclamation and the right to freedom of expression

Ethiopia’s Anti-Terrorism Proclamation and the right to freedom of expression


Patrick GriffithAuthor: Patrick GriffithProgramme Attorney, Freedom Now
On Wednesday 17 July 2013, members of the European Parliament’s Sub-committee on Human Rights visited Ethiopia and urged the government to release journalists and opposition activists imprisoned under the country’s Anti-Terrorism Proclamation No. 652/2009 (Anti-Terror Proclamation). The visit is an important reminder that despite widely hailed progress on poverty reduction, the Ethiopian government continues to punish free expression in violation of international law.
Eskinder Nega, an outspoken journalist and blogger who was sentenced to 18 years imprisonment in July 2012, is amongst those arbitrarily detained under the Anti-Terror Proclamation. In early 2011, Nega began writing and speaking publicly about the protest movements then sweeping north Africa. Although initially hesitant to draw direct parallels with Ethiopia, he was clearly supportive of the protesters abroad and critical of his government at home. He also consistently emphasised the importance of non-violence. But despite the clear protection of peaceful free expression under Article 19 of the International Covenant on Civil and Political Rights, to which Ethiopia is a party, the government reacted by prosecuting Nega as a traitor and terrorist.
The government’s imprisonment of Nega and his colleagues – such as fellow journalist Reeyot Alemu and oppositionist Andualem Araige – has drawn widespread criticism from the international community. The African Commission on Human and Peoples’ Rights expressed grave concern about the imprisonment of Ethiopian journalists and activists “for exercising their peaceful and legitimate right to freedom of expression and association”. Five United Nations (UN) special procedure mandate holders issued a joint statement noting their “dismay at the continuing abuse of anti-terrorism legislation to curb freedom of expression in Ethiopia”, and the UN High Commissioner for Human Rights voiced alarm over the climate of intimidation created by the targeting of journalists on “overly broad” anti-terrorism charges.
Eskinder Nega an outspoken journalist and blogger who was sentenced to18 years imprisonment in July 2012
In a detailed opinion, the UN Working Group on Arbitrary Detention, a diverse panel of five independent experts, specifically found Nega’s continued detention a violation of international law. In calling for his immediate release, the UN Working Group held that “the application of the overly broad offenses” against Nega as a consequence of his free expression rendered the detention arbitrary under international human rights standards.
When confronted about the scope and application of the Anti-Terror Proclamation, Ethiopian officials often claim that the offending language was simply pulled from the existing laws of countries like theUnited Kingdom (UK). However, a close examination reveals that while Ethiopia’s Anti-Terror Proclamation borrows some key phrases, it is significantly more expansive – and vague – than the statutes it purports to mirror.
The provision on “encouraging terrorism” is a glaring example. Article 6 of the Anti-Terror Proclamation provides that:
“[w]hosoever publishes or causes the publication of a statement that is likely to be understood by some or all of the members of the public to whom it is published as a direct or indirect encouragement or other inducement to them to the commission or preparation or instigation of an act of terrorism [is subject to between 10 and 20 years in prison].”
Compared with UK’s equivalent piece of legislation, the Ethiopian Anti-Terror Proclamation simply lifts an introductory paragraph while omitting the following seven sections that define and limit the law’s scope. Putting aside the question of whether British law even complies with international human rights standards, the omission of essential limiting provisions on intent, interpretation, and defences under the Anti-Terror Proclamation leaves the remaining language hollow and without any meaningful application.
When “encouragement of terrorism” is combined with the definition of “terrorist acts” under the Anti-Terror Proclamation, the potential for abuse becomes apparent. Tracking language found in the Organisation for African Unity’s Convention on the Prevention and Combating of Terrorism (Convention), Article 3 of the Anti-Terror Proclamation defines terrorism to include “caus[ing] serious interference or disruption of any public service”. Importantly, the Convention defines the intent to disrupt public services—along with intending to influence the government—as part of the mens rea (mental intent requirement). By contrast, Ethiopia’s Anti-Terror Proclamation retains the mens rea of intending to coerce the government, but treats disrupting social services as a component of the actus reus (physical act requirement). By treating the disruption of public services in this way, the Anti-Terror Proclamation significantly expands upon the Convention’s actus reus, which requires that a “terrorist act” physically threaten the safety of people or property. Even assuming, arguendo, that the intent requirement for “terrorist acts” implicitly applies to encouragement also, advocating for peaceful protests—which may be intended to influence policy but that in no way actually endangers people or property—may constitute “encouraging terrorism” under Ethiopian law.
This discussion of the Anti-Terrorism Proclamation may seem semantic, but the result is painfully real for the journalists and activists who face imprisonment for exercising basic rights. It’s time to release them and amend the law.

Wednesday, January 8, 2014

“አንድነት” የፀረ-ሽብር አዋጁን ለማሠረዝ የሚያስችል ድምፅ ማግኘቱን ገለፀ::የህዝብ ፊርማ ይዘን በፍ/ቤት ክስ እንመሰርታለን ብሏል::

“አንድነት” የፀረ-ሽብር አዋጁን ለማሠረዝ የሚያስችል ድምፅ ማግኘቱን ገለፀ::የህዝብ ፊርማ ይዘን በፍ/ቤት ክስ እንመሰርታለን ብሏል:: 

የህዝብ ፊርማ ይዘን በፍ/ቤት ክስ እንመሰርታለን ብሏል::
UDJ SEALየፀረ-ሽብር አዋጁን በመቃወም “የሚሊዮኖች ድምፅ” በሚል መርሃግብር የህዝብ ፊርማ ሲያሠባስብ የቆየው አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ፤ ህጉን ለማሠረዝ የሚያስችል በቂ ድምፅ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ ከ1ሚ. በላይ ፊርማ አሰባስቤአለሁ ያለው ፓርቲው፤ የህዝቡን ፊርማ በመያዝ ክስ እንደሚመሰርት ገልጿል፡፡
ፓርቲው ለ3 ወራት ባካሄደው ፊርማ የማሰባሰብ ዘመቻ የፀረ ሽብር አዋጁን ለማሰረዝ የሚያስችል ድምጽ ማግኘቱን የገለፁት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ፤ አሁንም ድረስ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በኦንላይን እየፈረሙ በመሆኑ አጠቃላይ የፈራሚዎቹን ቁጥር መግለጽ ቢያዳግትም፣ እስካሁን ከ1 ሚሊዮን በላይ ፊርማ መሰባሰቡን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ የተሰባሰበው የፊርማ ብዛት ፓርቲው ከገመተው በላይ ስኬት መቀዳጀቱን ይጠቁማል ያሉት ሃላፊው፤ በአጠቃላይ የተሰበሰበውን የፊርማ ብዛት ፓርቲያቸው በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
“አንድነት” ፓርቲ በፀረ ሽብር ህጉ ላይ ያለው አቋም ሙሉ ለሙሉ ይሰረዝ የሚል እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ዳንኤል፤ የተሰበሰበውን የህዝብ ፊርማ ለፍ/ቤት በማቅረብ፣ ህጉ ከህገመንግስቱ ጋር እንደሚጋጭና የዜጐችን መሠረታዊ መብት እንደሚጥስ በመጥቀስ ክስ እንመሠርታለን ብለዋል። ከፍ/ቤት ቀጥሎም ጉዳዩን ለፌደሬሽን ምክር ቤት እንደሚያቀርቡ የገለፁት ሃላፊው፤ ምንም እንኳ ከዚህ ቀደም በህዝብ ድምፅ ህግ የማሠረዝ እንቅስቃሴ ተሞክሮ ባያውቅም ፍ/ቤቶች እና ምክር ቤቱ የፓርቲውንና የፈራሚውን ህዝብ ጥያቄ ተቀብለው ውሳኔ እንደሚሰጡ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጐችን ድምፅ ዝም ብለን ሜዳ ላይ አንጥልም ያሉት አቶ ዳንኤል፤ የፍ/ቤቶች ገለልተኝነት አጠያያቂ ከመሆኑ አንፃር ጥያቄው ተቀባይነት ባያገኝ እንኳን ህዝቡ የተሣተፈበት የፓርቲው የትግል አካል ተደርጐ ለታሪክ ተመዝግቦ ይቀመጣል ብለዋል፡፡
ህጉ ይሠረዝ የሚል አቋማቸው በመንግስት በኩል “ለሽብርተኝነት ድጋፍ ከመስጠት አይለይም” የሚል ትችት ማስከተሉን ያነሳንባቸው አቶ ዳንኤል በሰጡት ምላሽ፤ “የወንጀለኛ ህጉ አልበቃ ብሎ የፀረ-ሽብር ህግ ራሱን ችሎ የሚያስፈልግ ከሆነም ከውጭ የተቀዳ ሣይሆን ከፍተኛ የህግ ባለሙያዎች የተሣተፉበት እንዲሁም ህብረተሠቡ በየደረጃው ውይይት ያደረገበትና የመላውን ህዝብ ይሁንታ ያገኘ ህግ ማውጣት ይቻላል” ሲሉ የፓርቲያቸውን አቋም አንፀባርቀዋል፡፡ ፓርቲያቸው በስራ ላይ ያለው የፀረ – ሽብር አዋጅ እንዲሠረዝ ጥብቅ አቋም የያዘበትን ምክንያት ሲያስረዱም፤ “ህጉ ከወጣ በኋላ በቀጥታ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን ለማስፈራሪያና ለማጥቂያ በመዋሉ ነው” ብለዋል – ሃላፊው፡፡
የፀረ – ሽብር ህጉን ለማሠረዝ የሚያስችል ድምጽ ማሠባሠብ መቻላችን አገሪቱ አቤቱታ ለማቅረብ ምቹ የዲሞክራሲ ቁመና ላይ መገኘቷን ፈፅሞ አያመለክትም ያሉት አቶ ዳንኤል፤ ፓርቲያቸው የፀረ-ሽብር አዋጁን በተመለከተ ህጋዊ መነሻ ይዞ ለመላ ኢትዮጵያውያን በይፋ የተቃውሞ ጥሪ ያቀረበ ቢሆንም ሠሞኑን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እየተላለፈ በሚገኘው ዘጋቢ ፊልም ላይ “አንድነት ፀረ-ሠላም ለማድረግ መሞከሩ ተገቢ አይደለም” ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡ በ97 ምርጫ ትልቁ የኢህአዴግ አጀንዳ “ኢንተርሃሞይ” እንደነበር ያስታወሱት ሃላፊው፤ በ2002 ምርጫ “ተቃዋሚዎች አጀንዳ የላቸውም” ወደሚል ቅስቀሣ መቀየሩን ጠቁመው፤ ለቀጣዩ ዓመት ምርጫ ደግሞ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን “ፀረ-ሠላም ናቸው” የማለት እንቅስቃሴ ከወዲሁ መጀመሩን ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል ፓርቲው፤ ከዚህ ቀደም ሠላማዊ ሠልፍ እንዳላደርግ እንቅፋት ሆነውብኛል ባላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ፖሊስ ላይ ክሡን ለመመስረት በዝግጅት ላይ እንደሆነ አቶ ዳንኤል ተናግረዋል፡፡ በዛሬው እለት አዲስ በተመረጡት የፓርቲው ሊቀመንበር በኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ይፋ የሚደረገው የፓርቲው ካቢኔ የመጀመሪያ ስራ፣ የፀረ – ሽብር አዋጁን ማሠረዝ እና ክስ የሚቀርብባቸው አካላት ላይ ክስ መመስረት እንደሚሆን ሃላፊው አክለው ገልፀዋል፡፡

MillionsVoice1
- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=6059#sthash.ykRYYNc1.1o60aqWi.dpuf

Tuesday, January 7, 2014

ኮካኮላ የቴዲ አፍሮ ውል እንዲሰርዝ ዘመቻ ተጀመረ

ኮካኮላ የቴዲ አፍሮ ውል እንዲሰርዝ ዘመቻ ተጀመረ


በ 2014 ብራዚል ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ላይ ቴዲ አፍሮ የክብር እንግዳ 

እንዳይሆን አዲስ ዘመቻ በእነ ጃዋር መሃመድ መጀመሩ ተሰማ።


በዓለም ዙርያ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ለተፈናቀሉ ወገኖች እየተረባረቡ ባሉበት በዚህ ፈታኝ ወቅት፤ ጃዋር እና ሜንጫዎቹ ጸረ-ኢትዮጵያዊነት ዘመቻቸውን 

በስፋት ተያይዘውታል። በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ በደረሰን ዜና መሰረት ኮካኮላ 

የቴዲ አፍሮን የአለም ስፖርት ፌዴሬሽን (ፊፋ) ስፖንሰርነት እንዲያነሳ ጠይቀዋል። 

አዲስ አድማ ለመጀመርም ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።


በ 2014 ብራዚል ለሚካሄደው የአለም እግር ኳስ ዋንጫ አፍሪካን ወክሎ እንዲገኝ 

ኮካኮላ ቴዲን የመረጠው መሆኑ ይታወሳል። የአለም ስፖርት ፌዴሬሽን (ፊፋ) 

ወጣቱ ቴዲ አፍሮ አፍሪካን እንዲወክል መምረጡ ዘረኞቹን አስቆጥቶ እንደነበር 

የሚታወስ ነው።


ቴዲ አፍሮ በአለም መድረክ ላይ የሚያቀርበው ኢትዮጵያዊ የሙዚቃ ቃና ሀገራችንን 


እና መላው አፍሪካን የሚያስጠራ ነው።


የሄነከኑ አድማ በኦህዴድ ብርቱ ጥረት የተሳካላቸው እነኚህ ባለ አድማዎች፣ ሰሞኑን 


የደስታ መግለጫቸውን በየድረ-ገጾቻቸው ላይ እየተለዋወጡ እንደሆነ ተገልጿል። 

ሄኒከን ኮንሰርቱን የሰረዘው ከኦህዴድ በተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ ስለመሆኑ ማስረጃው 

አሉ።


እነ ጃዋር በዚህ አላበቁም። በዲሴምበር 8፤ 2013 በተላለፈ የአቶ ቡልቻ ደመቅሳ 


እና ሌሎች ምሁራን ቃለ-ምልልስ ምክንያት የጀርመኑ (ዶቸ ቨለ) የአማርኛ ድምጽ 

ሬዲዮ ጋዜጠኛ ከስራ እንዲነሳም ከአቤቱታ ጋር ቀጭን ትእዛዝ ለቦርዱ አስተላልፎ 

ነበር። የዶቸ ቨለ ቦርድ ላይ ኦህዴድ ተጽእኖ ስለሌለው ይህ ዘማቻ ሊሳካ አልቻለም።


የኮካኮላው ዘመቻ የተነጣጠረው በቴዲ አፍሮ ላይ ሳይሆን በአኢትዮጵያዊነት ላይ 


ስለሆነ በአለም ዙርያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ዝምታውን በመስበር በነዚህ ሰዎች ላይ 

የሶሻል ሚድያ ዘመቻ መክፈት ይገባቸዋል።

Mass Grave Discovered in Addis Ababa

Mass Grave Discovered in Addis Ababa


By Betre Yacob

A mass grave has been discovered in Addis Ababa, the capital of Ethiopia, containing at least 6 bodies of young men, who may have been executed in the past few years.

The identities of the bodies are still remained unclear.

The grave was accidentally found in the area called Ferensay-legasion, inside the barracks of the third army battalion, by road construction workers, who was digging the ground with excavator for road construction.

Witnesses said that the excavator first pulled out two bodies wrapped in blankets and again another four bodies each wrapped in blankets of identical colors. According to witnesses, two of the bodies were still in hand-cuffs and one other had his hands tied behind his back.

So far, authorities have said nothing. But, many are pointing their figures at the EPRDF, the ruling party in Ethiopia.

Witnesses say that the blankets did not lose their original colors and labels and that also indicates the executions were not carried out that long ago.

“It is not doubtful they are victims of the current regime”, a journalist witnessed the event said. “Look! The grave was found in the barracks of the army; on the top of that the blankets didn’t get old; even some of the bodies were in a good condition—they were not totally decomposed.” he explained

Reports indicate that the grave area was immediately fenced off by the army, and the bodies were taken by the federal police.

Ethiopia is one of the nations which are under brutal dictatorial regimes. The ruling party, EPRDF, has frequently been accused by human right organization of mass killings. It is known for arresting, torturing, and killing its opponents.

“It is a grim reminders of the Meles Zenawi era”, A political analyst in Addis Ababa told the Horn Times, East African Website.

“How many more mass graves are we going to uncover in the coming years in this city purged by the regime with unparalleled audacity? It would be the biggest flagrant miscarriage of justice if the ICC chief prosecutor Madam Fatou B let the panicking EPRDF warlords off the hook. It is incumbent up on her to send a team of investigators to Addis Ababa without any delay.

“ This blood curdling discovery has exposed the nation’s festering wounds and further complicated the dreadful ethnic fault line created by the ruling party in May 1991. I personally know that then federal police boss; the snarling evil Workeneh Gebeyhu used the third infantry battalion compound as the headquarters of operations in 2005. He quit the post last year and where is he today? The nation is crying for justice.” he explained.

“EPRDF warlords thought they found a safe spot to store remains of the barbarically executed non-combatant, peaceful protesters. Mass grave right under the nose of the international community and the people of Ethiopia. This crime scene is full of the telltale fingerprints of the dead former ruler Meles Zenawi….” he added.